Awoke Ethiopia
ተመስገን አምላኬ እንጅ ሌላ ምን ልበል
09/04/2026
የኢሕአፓ ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ!
ያስቀመጥናቸው ቅድመ-ሁኔታዎች ቢሟሉ ኖሮ ኢሕአፓ ዐይኑን ሳያሽ በምርጫው ተሳትፎ የኢትዮጵያን ሕዝብ ከቀጣይ መከራና ዕልቂት ለመታደግ ኢትዮጵያንም ከተደቀነባት የመፍረስ አደጋ ለማዳን የበኩሉን አስተዋጽዖ ያበረክታል ሙሉ ዝግጅትም አድርጎ ነበር። ነገር ግን ገዥው ብልጽግና ፍላጎቱ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ማካሄድ ሳይሆን ዛሬም ከቻለ አታሎ፣ አጭበርብሮና ሸውዶ፣ አለዚያም አፍኖና ጨፍልቆ “ተመርጫለሁ ዕወቁልኝ” ለማለት ነው።
በጦርነት፣ መፈናቀል፣ የንጹሀን የጅምላ ግድያ እና እስር የኢትዮጵያ መልኮች በሆኑበት ወቅት የሚካሄድ ምርጫ ለስርኣቱ ንጹሃንን በጅምላ መግደልህን፣ ማሰደድህንና ማሳደድህን፣ ዜጎችን በፖለቲካ አመለካከታቸው ምክንያት በግፍ ማሰርህን ቀጥል ብሎ መፍቀድናየህዝቡንም ስቃይ ከማስቀጠል የዘለለ ትርጉም አይኖረውም፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ በሰራዊት ታጅቦ ምርጫ ለማድረግ መታቀዱም ብልጽግና ለቀጣይ አምስት አመታት በሃይል በስልጣን ላይ ለመቆየት ያለውን ፍላጎት የሚያስረግጥ ነው፡፡
የትግራይ ሕዝብ ለሁለተኛ ጊዜ የማይወከልበት፣ የአማራ ሕዝብ ብልጽግና በጀመረው ጦርነት ወላፈን እየተገረፈ በሚገኝበት እና የማይወከልበት፣ በኦሮሚያ ክልል ውስጥም በርካታ አካባቢዎች ለአመታት በጦርነት እየተማገዱ ባሉበት እናፖለቲካዊ መፍትሔባልተቀመጠበት የሚካሄድ ምርጫ ትርጉሙ እጅግ አደገኛ እና የአገር አንድነት ከመሰረቱ እንዲናጋ የሚያደርግ ነው እንላለን፡፡
የንጹሃንን ጭፍጨፋ እንዲቆም፣ የኑሮ ውድነቱን የዜጎችን ህይወት እያመሰቃቀለ ስለሆነ በአስቸኳይ ርምጃዎች እንዲገታ፣ የንጹሃን ዜጎችን እስር፣ ማንነት ተኮር እስሮች፣ ወከባዎችና ግድያዎች እንዲቆሙ፣ የዜጎች መፈናቀል፣ ከመኖሪያቸው መፈናቀና መባረር እንዲቆም፣ ሙስና ዓድላዊነትና አግላይነት እንዲወገዱ፣ አምባገነንነት ከሕዝቡ ትከሻ ለማስወገድ የሚሻ ኢትዮጵያዊ በሙሉ ኢሕአፓ አርብ ሚያዚያ 30 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ፣ መቐለ፣ ባህርዳር፣ ጎንደር፣ ሀዋሳ፣ አሶሳ፣ አዳማ እና አምቦ፣ ድሬዳዋ እና ሀረር ከተሞች በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ተገኝቶ በታላቅ መከራ ውስጥ እያለፈ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጎን እንደሚቆም በተግባር እንዲያሳይ ጥሪ እናቀርባለን፡፡
ብልጽግና ንጹሃንን መግደል እና ማሳደዱን በአስቸኳይ ያቁም!
ሁሉን አቀፍ ሃቀኛ ድርድር ይደረግ!
የፖለቲካ እስረኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ ይፈቱ!
የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ - ኢሕአፓ
መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ ፤ ኢትዮጵያ
04/04/2026
👍👍👍👍👍👍👍
04/04/2026
ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ይምረጡ
29/03/2026
ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በሚካሄደው ምርጫ የብልፅግና ፓርቲ 'የተለያዩ ቦታዎች ላይ ባለመወዳደር ተፎካካሪዎች እንዲገቡበት ክፍት አድርጌላቸዋለሁ' ማለቱን አረጋግጠናል። ይህ ዋጋ ያለው የሕዝብ ድምጽ ሳይሆን የእኔ ችሮታ ነው የሚል አስተሳሰብ አሁንም በብልጽግና ቤት እንዳልጠፋ እና ሕዝብ ምን ያህል እንደተናቀ አንዱ ማሳያ ነው። ይህ ድርጊት ድርጊት ብቻ ሳይሆን የስልጣን ባለቤትነት የሕዝብ ነው የሚለውን መሰረታዊ መርሕ መጣስ እና ምርጫው ከዴሞክራሲያዊነት በእጅጉ የራቀ መሆኑን ማሳያ ጭምር ነው።
29/03/2026
የትምርህት ሚኒስቴር ትምህርት ነክ መረጃዎች
29/03/2026
With AWi Injibara – I just got recognized as one of their top fans!
23/03/2026
TikTok · 𝙰𝚛𝚎𝚐𝚊 Check out 𝙰𝚛𝚎𝚐𝚊’s post.
21/03/2026
የሮበርት ሙጋቤ አባባሎች የትኛው ተመቻቸው
1. "ድህነት ወንጀል አይደለም፣ ነገር ግን በጣም አስቸጋሪ የሆነ ቅጣት ነው።"
2. "ከሌላ ሰው ገንዘብ ተበድረህ ሀብታም ለመምሰል አትሞክር፤ ምክንያቱም ያበደረህ ሰውዬ ሲያይህ የራሱን ብልጽግና እንጂ ያንተን ስኬት አይመለከትም።"
3. "አልጋህ ላይ ተኝተህ ጸሎት ብቻ በማድረግ ሚሊየነር መሆን አትችልም። እግዚአብሔር አብርሃምን 'ሂድ' ነው ያለው እንጂ 'ተኛ' አላለውም።"
4. "ዲግሪ መያዝ ብቻውን ስኬት አይደለም። ዲግሪው በኪስህ ሆኖ ጭንቅላትህ ባዶ ከሆነ፣ ያ ዲግሪ የአምስት ደቂቃ ኩራት ብቻ ነው የሚሰጥህ።"
5. "እድል ማለት ዝግጅት እና አጋጣሚ ሲገናኙ ነው። ዝግጁ ካልሆንክ እድሉ መጥቶ ሲያንኳኳ አንተ ተኝተህ ይሆናል።"
6. "መሪ መሆን ማለት ሰዎችን ማዘዝ ብቻ አይደለም፤ ሰዎቹ ወዴት መሄድ እንዳለባቸው ማሳየትም ጭምር ነው።"
የሙጋቤ "የገንዘብ ፍልስፍና" ማጠቃለያ
ሙጋቤ ብዙ ጊዜ አፍሪካውያን በራሳቸው ሀብትና ንብረት ላይ እንዲተማመኑ ይወተውቱ ነበር። የምዕራባውያንን እርዳታ ከመጠባበቅ ይልቅ "የራሳችሁን መሬት እረሱ፣ የራሳችሁን ስራ ፍጠሩ" የሚል ጠንከር ያለ መልዕክት ነበራቸው።
በነገራችን ላይ በሙጋቤ ዘመን ዚምባብዌ ከፍተኛ የገንዘብ ግሽበት (Inflation) አስተናግዳለች። ይህ ደግሞ ብዙ ሰዎች በሳቸው ስም ስለ ገንዘብ የሚቀለዱባቸው ቀልዶች እንዲበራከቱ ምክንያት ሆኗል።
ሙጋቤ ራሳቸው ሰባት ዲግሪዎች የነበሯቸው ምሁር ነበሩ። ስለዚህ ስለ ትምህርት ያላቸው አመለካከት ጥልቅና አንዳንዴም ተሳላቂ ነበር።
7. "ትምህርት ማለት አእምሮህን በሌሎች ሰዎች ሀሳብ መሙላት ብቻ አይደለም፤ ያንን ሀሳብ ተጠቅመህ የራስህን ዓለም መለወጥ መቻል ነው።"
8. "ፈተና ላይ የምታገኘው ውጤት የወደፊት ህይወትህን አይወስነውም፤ ነገር ግን በትምህርት ቤት ያሳየኸው ስነ-ምግባር ማንነትህን ይገልጻል።"
9. "ብዙ ዲግሪ ኖሮህ በሀገርህ ውስጥ ያለውን ችግር መፍታት ካልቻልክ፣ ዲግሪህ ለቤትህ ግድግዳ ጌጥነት ብቻ ነው የሚያገለግለው።"
ሙጋቤ የምዕራባውያን ጣልቃ ገብነትን ክፉኛ የሚቃወሙና አፍሪካውያን በራሳቸው እንዲቆሙ የሚወተወቱ መሪ ነበሩ።
10. "አፍሪካ ለአፍሪካውያን ናት! የእኛን መሬትና ሀብት እንዴት እንደምንጠቀምበት ሌላ ሰው እንዲነግረን አንፈልግም።"
11. "ነፃነት ማለት ባንዲራ መቀየር ብቻ አይደለም፤ የሀገርህን ኢኮኖሚና የወደፊት እጣ ፈንታ በእጅህ ማስገባት ማለት ነው።"
12. "አፍሪካውያን ካልተባበርን፣ እንደ ግለሰብ ተራ በተራ እንሰበራለን። እንደ ዱላ ስብስብ ከታሰርን ግን ማንም ሊሰብረን አይችልም።"
20/03/2026
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ የመጀመሪያ ሳምንት ሂደት ምን ይመስላል ?
- እስካሁን በመራጭነት የተመዘገቡ
9ሚሊዮን +
- በዲጂታል አማራጭ የተመዘገቡ
600 ሺ +
- የመራጮች ምዝገባ የጀመሩ ጣቢያዎች
46,757
- የመራጮች ምዝገባ ያልጀመሩ ጣቢያዎች
6,395
- የታሸጉ የምርጫ ጣቢያዎች
1
- የተቃጠለ ምርጫ ጣቢያ
1
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መጋቢት 4 ቀን 2018 ዓ/ም
Click here to claim your Sponsored Listing.
Contact the business
Website
Address
Addis Ababa