Mamush Garbo Galgale
College Dean
አዲስ ሕይወት ዉስጥ በመግባት ኑሮ ለመጀመር ዝግጅት ላይ ነኝ
31/03/2023
አስገራሚው የአፍሪካ ካርታ ቅርጽ ያለው ዶኔ ኤላ አባ (ሃይቅ) በኢትዮጵያ
መገኛ ቦታ፡ ጋሞ ዞን ምዕራብ ዓባያ ወረዳ ዶኔ ቀበሌ
26/02/2023
“ለድኻ የሚራራ ለእግዚአብሔር ያበድራል፤ ስላደረገውም ተግባር ዋጋ ይከፍለዋል።” — ምሳሌ 19፥17
እስቲ ይህንን ዘር፣ ኃይማኖት፣ ቋንቋ ሳይለይ የሚተጋ ሰውን በሰውነቱ ብቻ የሚያከብር በጎ አድራጊ ወጣት መርቁት!🙌
አቢዬ እጅህ ዘወትር ከላይ ይሁን የምትሰጠው አትጣ፤ እግዚአብሔር ብድራትህን ይክፈል😍
17/01/2023
እውቀትን በጥበብ!!!
“አዋቂ ሰው ምን እንደሚናገር ያውቃል፣ ጥበበኛ ሰው ግን መቼ መናገር እንዳለበት፣ እንዴት መናገር እንዳለበት እና ነገሩ ሊነገር የሚገባው መሆኑንና አለመሆኑን ጠንቅቆ ያውቃል” - ካልታወቀ ምንጭ
የሕይወታችሁ አብዛኛው አበሳ እንዲቀንስ ከፈለጋችሁ የምትናገሩትን ነገር ማወቃችሁ ብቻ በቂ እንዳልሆነ አምናችሁ መቀበል የግድ ነው፡፡
“ጥሬ” እውቀት እንደ አፈር በበዛበት የመገናኛ ብዙሃን ዘመን ውስጥ ነን ያለነው፡፡ ከዚህ በፊት ቀድተን ውስጣችን ካጠራቀምነውም (Save ካደረግነው) ሆነ እዚያው በዚያው እየቀዳን (Copy-Paste በማድረግ) መርጨት የምንችለው እውቀት እጅግ ብዙ ነው፡፡
ይህ እድል በራሱ ምንም ችግር ባይኖረውም እውቀት ብቻውን ረጅም ርቀት እንደማያስኬደን ማስታወስ ግን ጠቃሚ ነው፡፡
ከዛሬ ጀምሮ አዲስ ጎዳናን መጀመር እንችላለን፡፡ ይህ ጎዳና በእውቀት ላይ ጥበብን የጨመረ ጎዳና ነው፡፡ ይህንን ጎዳና መጓዝ ስንጀምር አንድን መረጃ ስላገኘን፣ አንድን ነገር ስላነበብንና አንድን ቀድሞ የማናውቀውን እውቀት ስላወቅን ብቻ አንናገረውም፡፡ በእውቀታችን ላይ ጥበብን ገዢ የማድረግንም ልምምድ እናዳብራለን፡፡
ማንኛውንም ሃሳብ ከመሰንዘራችን በፊት የሚከተሉትን ጥያቄዎች የመጠየቅ ልማዱ ይኑረን . . .
1. ይህንን ነገር መናገር አስፈላጊና ተገቢ ነው?
2. ይህንን ነገር ለመናገር ትክክለኛው ጊዜ ነው?
3. ይህንን ነገር በምን መልኩ ነው መናገር ያለብኝ?
https://t.me/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
" ኢየሱስም ደግሞ በጥበብና በቁመት በሞገስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ያድግ ነበር።
በነገር ሁሉ መከናወን ይሁንላችሁ!!
"
(የሉቃስ ወንጌል 2:52)
09/01/2023
1. ስኬትህ የምታደርገው ነገር ነፀብራቅ ነው
ከቀደመው ማንነታችን የተሻልን ለመሆን ጥረት ባደረግን ቁጥር በዙሪያችን ያሉ ነገሮች ሁሉ የተሻሉ መሆን ይጀምራሉ።
~ የተሻለ ሰው መሆንህ በዙሪያህ ያሉትን ነገሮች ሁሉ ማለትም የአኗኗር ዘይቤህን፣ ቤተሰብህን፣ ጓደኞችህን፣ ማህበረሰብህን የሚጠቅም ተዘዋዋሪ ተጽእኖ ይፈጥራል።
2. የምናብ ሰው ሁን
" አለምን የማየው እንዲከሰት ከምፈልገው ነገር አንፃር እንጂ ከሚታየው ነገር አንፃር አይደለም።"
~ ሰዎች ዓለምን እንዳለች መቀበልን ቢመርጡ ኖሮ ታላላቅ ፈጠራዎች አይከሰቱም ነበር።
~ ታላላቅ ስኬቶች እና ፈጠራዎች ‘አይቻልም’ የሚል አስተሳሰብን ችላ በማለት ይጀምራሉ።
3. በራስህ መንገድ ላይ አተኩር
ሌሎች ሰዎች ተጽእኖ ሊያሳድሩብህ ይችላል፤ ነገር ግን የሌላ ሰው ህይወት መኖር ከጀመርክ ግራ የተጋባ ሰው ትሆናለህ።
~ ምክር መቀበል እና ከሌሎች መማር ምንም ችግር የለውም፣ ነገር ግን የምትሄድበት መንገድ ከአንተ ፍላጎት እና ዝንባሌ ጋር የሚስማማ መሆኑን አረጋግጥ።
4. አሰልቺውን ተመሳሳይ ህይወት ስበረው
እያንዳንዱ ቀን ከቀጣዩ ቀን ጋር ተመሳሳይ በሚሆንበት ጊዜ ሰዎች በየቀኑ በሕይወታቸው ውስጥ የሚከናወኑትን መልካም ነገሮች ለይተው ማወቅ ስለሚያቅታቸው ነው።
~ ምስጋና በእያንዳንዱ ቀን ውስጥ ጥሩውን የማግኘት ልምምድ ነው።
5. ፍርሃት ከሚያጋጥምህ ማንኛውም እንቅፋት የበለጠ ትልቅ እንቅፋት ነው።
~ ፍርሃትህን አትፍራው ብትፈራውም ከማድረግ አታፈግፍግ!
6. አሁንን ተቀበል
ሁልጊዜ አሁን ባለህ ነገር ላይ ማተኮር ከቻልክ ደስተኛ ሰው ትሆናለህ።
~ ባለፈው መኖር እና ያለፈው ህይወትህ አንተን እንዲገልፅ መፍቀድ ወይም ስለወደፊቱ መጨነቅ ምንም ፋይዳ የለውም።
7. ወስን
አንድ ሰው ሲወስን፣ መጀመሪያ ውሳኔውን ሲወስን አያውቃቸው ወደነበሩ ቦታዎች የሚወስደው ኃይለኛ ፍሰት ውስጥ እየገባ ነው።
~ ድርጊት በውሳኔህ ላይ ከመተማመን የሚመነጭ ነው። አጥር ላይ መቀመጥ የትም አያደርስም። ስለዚህ ወስን! የውሳኔ ሰው ሁን!
8. ሁልጊዜ እርምጃ ውሰድ
" ለመማር አንድ መንገድ ብቻ ነው ያለው፤ ይህም ተግባር ብቻ ነው""
9. እንደገና መነሳትህን ቀጥል
" የሕይወት ምስጢር ሰባት ጊዜ ወድቆ ስምንት ጊዜ መነሳት ነው።"
ምክንያቱም ስምንተኛው ጊዜ የአንተ ግኝት ሊሆን ይችላል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Ariba Minch
Addis Ababa
0948