Ethio Health Tips

Ethio Health Tips

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethio Health Tips, Health/Beauty, Addis Ababa.

06/09/2021

ቴምር በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች አሉት።
1) ስብና ኮልስትሮል፡ ከየትኛውም የኮልስትሮል ዓይነቶች የጸዳና በጣም
አነስተኛ የስብ መጠን ያለው መሆኑ ክብደት መቀነስ ለሚፈልጉ ተመራጭ ነው፡፡
2) ፕሮቲን፡ ቴምር በፕሮቲንና አስፈላጊ ማዕድናት የበለጸገ መሆኑ ለሰውነት
እጅጉን ጠቃሚ ያደርገዋል፡፡
3) ቫይታሚን፡ በቫይታሚን የበለጸገ ነው ቴምር፡፡ ከቫይታሚን ዓይነቶች ቢ1፣
ቢ2፣ ቢ3፣ ቢ5፣ ኤ1 እና ሲ ንም አካትቶ ይዟል፡፡
4) ሀይል እና ጉልበት፡ ቴምር ቀላል የማይባል የሀይል ክምችት ስላለውም ንቁና
በሀይል የተሞላን እንድንሆን ያስችለናል፡፡
5) ፖታሲየምና ካልሲየም፡ ቴምር የፖታሲየም ክምችቱ ከፍተኛ ነው፡፡ ይህም
በልብ በሽታ እንዳንጠቃና አካላችን ውስጥ ያለው የኮልስትሮል መጠን
እንዲቀንስ ይረዳል፡፡ ቴምር በአንጻሩ አነስተኛ የሶዲየም መጠን ነው ያለው፡፡
ብዙ ፖታሲየምና ትንሽ ሶዲየም ደግሞ ለጤናማ የነርቭ ስርዐት ወሳኝ ነው፡፡
6) ብረት፡ ቴምር በብረትና በፍሎሪን የበለጸገ መሆኑ ደግሞ ብረቱ የብረት
ማዕድን እጥረት ላለባቸው ሰዎች፣ ፍሎሪኑ ደግሞ ጥርስን ከመበስበስ
ይከላከላል፡፡
7) ድርቀት፡ ለድርቀትም ቢሆን ውሀ ውስጥ የተነከረ ቴምር መመገብ ፍቱን
እንደሆነ ይታወቃል፡፡
ሰውነትን ማጽዳት፡ በአልኮል መጠጣት ሳቢያ ሰውነት ውስጥ
የሚከማቸውን መርዛማ ኬሚካሎች ከሰውነታችን ውስጥ በማስወገድም
ይረዳል።
9) ካንሰር እና የዓይን ችግር፡ የዓይን ህመም ችግርንና የሆድ ነቀርሳ (ካንሰር)ን
ለማከምም ብቃት እንዳለው ይታወቃል ፡፡
10) (የቆዳ ችግር) ቴምር የቆዳ ችግሮችን በማስወገድም መልካም ዝና አለው፡፡
ጸጉርን በማፋፋት የጸጉር መሳሳትንም ይከላከላል፡፡
በርከት ያሉ ቪታሚኖችን እና ሚኔራሎች በመያዙ ለጤናችን በርካታ ጠቀሜታዎች
እንዳሉት ይነገርለታል።
ሀይል ሰጪ፣ ፋይበር፣ እንዲሁም ካልሺየም፣ አይረን፣ ፎስፈረስ፣ ሶዲየም፣
ፖታሲየም፣ ማግኒዚየም፣ እና ዚንክ ሚኔራሎች በቴምር ውስጥ የሚገኙ በመሆኑ
ቴምርን ለጤና ጠቃሚ ያደርጉታል።
ስለዚህም ቴምርን አዘውትረን መመገብ ለጤናችን ከሚሰጠው ጠቀሜታዎች
ውስጥም፦
11.የሆድ ድርቀትን ይከላከላል።
ቴምር በባህሪው የማለስለስ ባህሪ ስላለው ምግብ በአንጀታችን ውስጥ በቀላሉ
እንዲዘዋወር በማድረግ የሆድ ድርቀት ለመከላከል ይረዳል። ለዚህም ይረዳን
ዘንድ ቴምሩን በውሃ
ውስጥ ዘፍዝፈን በማሳደር ጠዋት ላይ መመገብ ይመከራል።
12.ለአጥንት ጤንነት እና ጥንካሬ
በቴምር ውስጥ የሚገኙት ሚኔራሎች ለአጥንታችን ጥንካሬ እና ጤነነት እጅጉን
ጠቃሚ እንደሆኑ ይነገራል። ቴምር እንደ ሴሌኒየም ማንጋኒዝ፣ ኮፐር እና
ማግኒዚየም ማእድናትን በውስጡ በመያዙም ለአጥንት ጤናማ እድገት እና
ጥንካሬ ጠቃሚ ነው።
13.ደም ማነስን ይከላከላል
ቴምር በውስጡ በያዘው ከፍተኛ የምግብ ማእድናት ንጥረ ነገሮች ክምችት
የደም ማነስ ችግር ላለባቸው ሰዎች እጅጉን ጠቃሚ ነው።
14.አለርጂን ይከላከላል
ቴምርን ከሌሎች ለየት የሚያደርገው አለርጂን ለመከላከል የሚረዳውን ሰልፈር
ንጥረ ነገር በውስጡ በመያዙ ነው። ስለዚህም ቴምርን አዘውትረን የምንመገብ
ሰዎች ለተለያዩ አይነት አለርጂዎች የመጋለጥ እድላችን እጅጉን እንዲቀንስ
እንደሚያደርገው ይነገርለታል።
15.ለነርቭ ጤንነት
በቴምር ውስጥ የሚገኙት ቪታሚኖች የተስተካከለ እና ጤናማ የነርቭ ስርዓት
እንዲኖረን ስለሚያደርግም ለጤናችን ጠቃሚ ያደርገዋል።
16.ለልብ ጤንነት
ቴምር ለልባችን ጤንነት በርካታ ጠቀሜታዎች ስላሉት ተመራጭ ያደርገዋል።
ቴምር የልብ ጤንነትን ይጎዳል የሚባለውን የኮሌስቴሮል መጠን የመቀንስ
እቅም ስላለው ለድንገተኛ የልብ ህመም እንዳንጋለጥ በመርዳትም ለልባችን
ጤንነት

29/07/2021

ለማመን በሚከብድ አጭር ጊዜ ውስጥ፣ 10ሳሜ በወገብ ዙሪያ የተከማቸ
ቦርጭ የሚያጠፋ በቤት ውስጥ የሚዘጋጅ ውህድ ይዘን መተናል።
ይህ አስደናቂ ውህድ ለማዘጋጀት ቀላል ሲሆን፣ 10ሳሜ የሚሆን ቦርጭ
ለማጥፋት የሚወስደው ጊዜ አራት ቀን ብቻ ነው።
ውህዱን ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉ ግብዐቶች
👉ዝንጅብል
👉አረንጓዴ ሚንት ቅጠል በተለምዶ ናና የሚባለው ቅጠል
👉ኩኩምበር ወይም ክያር በመባል ይታወቃል
👉ሎሚ
👉8 ብርጭቆ ውሃ
የውህዱ አዘገጃጀት
በመጀመሪያ ሎሚውን በደንብ ማጠብ እና ለሁለት ቦታ መቁረጥ። ከዛ በጎድጓዳ
ሰሃን ውሃ ጨምሮ የተቆረጠውን ሎሚ ውሃው ውስጥ መጨመር ።
ኩኩምበሩን መላጥ እና ከታትፎ ውሃው ውስጥ መጨመር ፣ ከዛ ከ 8 እስከ 12
የሚሆኑ አረንጓዴ የሚንት ቅጠል እና ተልጦ በትንንሹ የተከተፈ ዝንጅብል
መጨመር ።
ሁሉንም ከደባለቅን በኋላ ፍሪጅ ውስጥ ማሳደር፣ (በረዶ ቤት አይደለም ።)
በአንዴ መጨረስ ስለሚከብድ ቀስ እያሉ፣ ቁርስ ምሳ መክሰስ ወይም በየተወሰነ
ሰዓት ልዩነት ውህዱን መጨረስ ያስፈልጋል።
ማሳሰቢያ፣ ውጤቱን በደንብ ለማየት ቢያንስ ለ 4 ቀን መጠጣት ያስፈልጋል።
እንዲሁም አመጋገብ ማስተካከል እና የአካል እንቅስቃሴ ብንጨምርበት ደግሞ
ገራሚ ለውጥ እናገኛለን።
መልካም ጤንነት!!!

16/06/2021

የሽንትዎ ቀለም ስለሰውነትዎ ጤና ምን ይነግርዎታል?
ሽንት ኩላሊት ደምን አጣርቶ የሚያስወጣው ክፍል ሲሆን 95%
ውሀ 5% ኤሌክትሮላይቶች እና ቆሻሻዎች ናቸው ።
ጤናማ እና በቂ ፈሳሽ በሚዎስዱበት ጊዜ ሽንትዎ ብዙ የጎላ
ቀለም በሌለው እና ነጣ ያለ ቢጫ ቀለም መካከል ነው፡፡በቂ
ፈሳሾችን በማይወስዱበት ጊዜ ሽንትዎ ይበልጥ የተከማቸ ሲሆን
ወደ ጠቆር ያለ ቢጫ ወይም የዓምበር ቀለም ይለወጣል ፡፡
ከዚህ በተጨማሪ የሽንት ቀለም እና መጠን እየዎሰዱ ያሉትን
የውሀ መጠን ፣ ምግብ ፣ ቫይታሚን ጠቋሚ ነው።
የተወሰኑ ምግቦች ፣ አንቲባዮቲኮች ፣ የህክምና ሁኔታዎች እና
ቀለሞች እንዲሁ ለጊዜው የሽንት ቀለም ይቀይራሉ ፡፡ ከዚህ
ቀጥሎ የተለያዩ የሽንት ቀለም አይነቶች እና ምክንያቶች እናያለን

1. በጣም ነጭ ከሆነ ከመጠን በላይ ውሀ እየጠጡ እንደሆነ
ያመለክታል ። ይህም የተለያዩ በደም ውስጥ የሚገኙ ንጥረ
ነገሮችን በተለይም ፓታሽየም እና ሶድየም መጠናቸው
እንዲያንስ ያደርጋል ይህም የልብ ጡንቻን ይጎዳል ።
2. ጥቁር ቢጫ - ይህም በቂ ውሀ እየወሰዱ እንዳልሆነ ወይም
ኬቶን በሽንት ውስጥ መኖር ሊሆን ይችላል ። በቂ ውሀ
አለመውሰድ ደግሞ ለኩላሊት ጠጠር ፣ የሰውነት ፈሳሽ መቀነስ
፣ የኤሌክትሮላይት መዛባት ያስከትላል ። ኬቶን የሚፈጠረው በቂ
የሆነ ስኳር (glucose ) ሳያገኝ ሲቀር እና ቅባት (fat)
ለሴሎች ጉልበት ሲጠቀም ነው ። ይህም በሽንት መልክ
ይወጣል ። ከፍተኛ የኬቶን መጠን አደገኛ የስኳር በሽታ ጉዳትን
(DKA) ተከትሎ ሊመጣ ይችላል ። አነስተኛ መጠን ከሆነ
ለረጅም ጊዜ ካልተመገብን ሊከሰት ይችላል ።
3. ደማቅ ቢጫ - ከበቂ በላይ ሰው ሰራሽ ቫይተሚን ቢ
እየወሰዱ ከሆነ
4. ቀይ- ይህ የሚፈጠረው ደም በሽንት ውስጥ ሲኖር ነው ።
ይህም በኩላሊት ጠጠር ፣ የኩላሊት እና የሽንት ፊኛ ኢንፌክሽን
፣ የፕሮስቴት እጢ ካንሰር ፣ የኩላሊት ካንሰር ፣ ከባድ ስፓርት
5. ጥቁር ብርቱካናማ / ቡናማ - የጉበት ችግር ያመለክታል ።
የጉበት ፣ የሀሞት ቀረጢትና የቱቦዎች ችግር ተከትሎ የቢሊሩቢን
በደም ውስጥ መብዛት ጋር ተያይዞ የሚከሰት ነው።
6. ሀምራዊ - አነስተኛ ደም በሽንት ውስጥ ሲኖር ወይም ቀይ
ስር ከበላን
7. ሰማያዊ - የካልስየም መብዛት /hypercalcemia
7. አረፋ ካለ - ፕሮቲን በሽንት ውስጥ መኖር ፤ ይህም የኩላሊት
ቁስለት ፣ የኩላሊት ጠጠር ፣ የልብ እና የኩላሊት መድከም ፣
የተለያዩ የካንሰር አይነቶች
8. ብዙ የሚሸኑ ከሆነ - በሽንት ውስጥ የስኳር መኖር ነው ፤
ይህም የስኳር በሽታ ያመለክታል ።
መልካም ጤና!!!

06/05/2021

የማር ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች 👉የካንሰርና የልብ ህመም ይከላከላል
የተፈጥሮ ማር ፍላቮንድና አንቲ ኦክሲዳንት(antioxidant) በውስጡ ይዟል
እነዚህ ነገሮች በካንሰርና የልብ ህመም የመጠቃት እድልን ይቀንሳሉ።
👉የአንጀት መቁሰልን ይከላከላል
ማር አንጀታችን በባክቴሪያ ሲጠቃና በተለያዩ ምክንያቶች እንዳይቆስል
ይከላከላል
👉ማር ፀረ ባክቴሪያና ፀረ ፈንገስ ነው
ማር ፀረ ባክቴሪያ ባህሪ አለው ምክንያቱም ንብ
ማር ውስጥ ሀይድሮጂን ፐር ኦክሳይድ (hydrogen per oxide) የተባለ
ኢንዛይም ትጨምርበታለች።
👉የአትሌቶችን ብቃት ይጨምራል
በድሮ ጊዜ የሚገኙ አትሌቶች ብቃታቸውን ለመጨመር ማርን ይጠቀሙ ነበር
ይህ ተግባር በአሁኑ ዘመናዊ አትሌቲክስ የተረጋገጠ ሲሆን የግላይኮጂን መጠን
በማመዛዘን ጉልበት እንዲያገኙ ያደርጋል።
👉ማር ሳል እና የጉሮሮ መቆጣትን ይቀንሳል
ቀይ ማር ለሳል በጣም ጠቃሚ ነው። ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ በ110
ህፃናት ላይ በተደረገው ጥናት መሰረት እኩል መጠን ያላቸው ቀይ ማር እና
ዴትሮሜትሮፌን(detromethorphan) ተመሳሳይ የሆነ በምሽት ከሚነሳ ሳል
እኩል የማስታገስ አቅም ያላቸው ሲሆን ሰላማዊ እንቅልፍ እንዲኖረን ያደርጋል።
👉ማር በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ይቆጣጠራል
ማር ምንም እንኳን አነስተኛ መጠን ያለው ስኳር ቢኖረውም ሰው ሰራሽ ከሆነው
ስኳር ጋር ግን ተመሳሳይ አይደለም። የፍሩክቶስ ና ግሉኮስ ጥሩ የደም የስኳር
መጠንን ቅንጅት ይቆጣጠራል። በተጨማሪም አንዳንድ የማር አይነቶች
አነስተኛ/ዝቅተኛ የስኳር መጠን ስላላቸው የደም የስኳር መጠን እንዳይዋዥቅ
ያደርገዋል።
👉ማር የሰውነት ቁስለትንና ቃጠሎን ይፈውሳል
ማርን በውጨኛው የሰውነት ክፍላችን ላይ ከሲልቨር ሰልፋዲያዚን(silver
sulfadiazine) አብረን መጠቀም ፍቱን መድሀኒት ነው። በማር ውስጥ ያሉት
ቀላል ስኳሮችና የፀረ ባክቴሪያ ባህሪው ቁስል ቶሎ እንዲድን ያደርገዋል።
👉ስነ ህይወታዊ ባህረ
አንዳንድ የማር አይነቶች የተለመድ የማይጓድ ባክቴሪያዎችን ይዘዋል እነሱም 6
የሚሆኑ የላክቶ ባሲላይ ዝርያዎችና 4 የቢፊዶ ባክቴሪያ ናቸው በመሆኑም ማር
ዘርፈ ብዙ የሆነ ህመምን የመፈወስ ጥበብ እና ባህሪያት አካቷል።
👉ለቆዳ ውበት
የማር የፀረ ባክቴሪያ በዋነኛነት ለቆዳ ተስማሚ እና ጠቃሚ ነው። ከሌሎች
ጋርም በመሆን ቆዳን የማለስለስና የማርጠብ ከፍተኛ አቅም አለው።
መልካም ጤና!!!!

04/05/2021

የፓፓያ ጥቅሞች
👉የሞቱ የቆዳ ሴሎችን ለማስወገድ ይረዳል፡፡
👉 የቆዳ ድርቀትን ይከላከላል፡፡
👉 ጥሬ ፓፓያ ፊትዎን ለ 25 ደቂቃ በመቀባት ፊት ላይ የሚገኙ ጥቃቅን ያበጡ
ነጠብጣቦችን በቀላሉ ማስወገድ ይችላሉ፡፡
👉 ፓፓያን በቀጥታ ቆዳዎን በመቀባት ወይም በመመገብ የሚያምር ለስላሳ
ቆዳን መጎናፀፍ ይቻላሉ፡፡
👉 የተፈጨ ፓፓያ የተሰነጣጠቀ ተረከዝን ለማከም ይጠቅማል፡፡
👉 ተፈጥሮአዊ የሞቱ ሴሎችን ከቆዳ ላይ ማስወገጃ መንገድ ነው፡፡
👉 የቆዳን ተፈጥሮአዊ ቀለም ለመመለስ ይረዳል፡፡
👉 ለሆድ ትላትል ህክምናነት ይጠቅማል፡፡
👉 በቆዳ ላይ የሚታዩ የእርጅና ምልክቶችን ለመቀነስና ለማከም ይረዳል፡፡
👉 ጥቁር ነጠብጣቦችን ለማስወገድ ይረዳል፡፡
👉 ራሰ በራነትን ይከላከላል፣ የፀጉር እድገትንና ጥንካሬን ይጨምራል፡፡
መልካም ጤና!!!

ስለ ስኳር በሽታ ይህን ያውቃሉ || Ethio Health Tips 25/04/2021

https://youtu.be/XeUlbdRB4uo

ስለ ስኳር በሽታ ይህን ያውቃሉ || Ethio Health Tips Ethio Health Tipsስለ ስኳር በሽታ ይህን ያውቃሉ በቪዲዮው እንደተማራቸሁ ተሰፋ እናደርጋለን የተለያዩ ጥያቄዎች ወይም አስተያየቶች ካሏቹ comment ላይ አስቀምጡልን የተለያዩ ጤና ነክ ጉዳዮችን እ...

25/04/2021

የኩከምበር የጤና ጥቅሞችን
1. የመገጣጠሚያ ህመም ስሜትን ያስታግሳል
2. የኮሌስትሮል መጠንን ይቀንሳል
3. ክብደት ለመቀነስ ይረዳል
4. የምግብ መፈጨት ሂደትን ያግዛል
5. የእራስምታት ህመምን ይከላከላል
6. ካንሰርን የመዋጋት አቅም አለው
7. ለፀጉሮ ወዝን ይሰጣል
8. ለደም ግፊትና ለስኳር ህመምተኞች ጠቃሚ ነው።
መልካም ጤና!!!!

09/04/2021

የሚከተሉት 5 ቀላል መንገዶች ጥርስን በቤት ውስጥ ለማንጣት ይረዳሉ።
1. በመጋገርያ እርሾ(Baking soda) መቦረሽ:-
የመጋገርያ እርሾ(Baking soda-sodium bicarbonate) በተፈጥሮው ጥርስ
የማንጣት ይዘት ያለው መሆኑን የተለያዩ ጥናቶች ያሳያሉ።
በዚህም የመጋገርያ እርሾ ንጥረ ነገር ያላቸው የጥርስ ሳሙናዎች ጥርስን
ለማንጣት ውጤታማ ናቸው።
አጠቃቀም:- አንድ መለክያ እርሾ ከሁለት መለክያ ውሃ ጋር በማዋሃድ መቦረሽ።
2. ሃይድሮጅን ፔሮክሳይድ/( Hydrogen peroxide )
ሃይድሮጅን ፔሮክሳይድ ሌላው ጥርስን ለማንጣት የሚጠቅም እና አፍ ውስጥ
የተከማቹ ባክትርያዎችን ለማጥፋት የሚረዳ ነው።
በገብያ ላይ ያሉ ጥርስን ለማንጣት የሚጠቅሙ ምርቶች
(Whitening products) ጠንካራ የሃይድሮጅን ፔሮክሳይድ ይዘት ያላቸው
ሲሆን በቤት ውስጥ የምንጠቀመው ግን አነስተኛ ይዘት ያለውን (3 % /1.5%
hydrogen peroxide) ነው።
አጠቃቀም:- እፍን በመጉመጥመጥ አልያም ከመጋገርያ እርሾ ጋር በማዋሃድ
ጥርስን መቦረሽ።
3. የተፈጥሮ ጨው እና የመጋገርያ እርሾ
(Paste of sea salt and baking soda)
አንድ መለክያ እርሾ እና ግማሽ መለክያ ጨው አነስ ባለ ውሃ ጋር በማዋሃድ
በለስላሳ የጥርስ ብሩሽ ለ2 ደቂቃ መቦረሽ
4. በሙዝ የውስጥ ልጣጭ መፈግፈግ (Banana peel rub):
በውስጠኛው የሙዝ ልጣጭ ጥርሳችንን ለሁለት ደቂቃ ቀስ አርገን ከፈገፈግን
በኋላ በጥርስ ብሩሽ መቦረሽ።
የሙዝ ልጣጭ ውስጥ ያሉት ከፍተኛ የ ማግኒዚየም ፖታሲየም እና ማንጋኒዝ
መእድናት ወደ ጥርሳችን በመዋሃድ ጥርሳችን ይበልጥ ነጭ እንዲሆን
ያግዙታል።
5. ጥርስዎት መልኩን እንዳይቀይር አስቀድሞ መጠንቀቅ
ለመከላከል:-
👉 እንደ ቡና፣ ሶዳ መጠጦች፣ ቀይ ወይን እና ሌሎች ቀለም ያላቸው መጠጦች
ከተጠቀምን በኋላ ጥርሳችንን መቦረሽ
👉 የስኳር ይዘት ያላቸውን ምግቦች መቀነስ
👉 እልፎ አልፎ ጥርስ የላይኛው ክፍል ሲሸረሸር(Enamel erosion) ቢጫ
ቀለም ያለው የታችኛውን የጥርስ ክፍል ስለሚያጋልጥ የጥርሳችንን ቀለም
ይቀይረዋል።
ስለሆነም የካልሲየም ንጥረ ነገር ያላቸውን ምግቦች እንደ ወተት፣ቅቤ፣ብሮኮሊ
በመጠቀም የጥርሳችንን ጥንካሬ እና እንፀባራቂነት መመለስ እንችላለን።
መልካም ጤና!!!

April 1, 2021 05/04/2021

https://youtu.be/7FZcRWq3SLE
don't forget subscribe 👆👆👆

April 1, 2021

02/04/2021

ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ የድንገተኛ ልብ ህመም ምልክቶች።
👉ጭንቀት
ይህ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ የልብ ህመም ምልክት ነው፡፡ ድንገተኛ የልብ
ህመም ከመከሰቱ በፊት ፍርሀት ፍርሀት የማለት ስሜት ሊኖር ይችላለ፡፡
👉የደረት መጨምደድ
ደረት ላይ የመጨምደድ ስሜት እጅግ የተለመደ የልብ ህመም ምልክት ነው፡፡
ከልብ ህምም ጋር ያልተያያዘ የደረት መጨምደድ በሌሎች ምክንያቶች ሊከሰት
የሚችል ቢሆንም በአብዛኛው የልብ ህመም መገለጫ ነው፡፡ ደረቶን በመጫን
የመሸምቀቅ ወይም የመጨምደድ ሲሜት ሲሰማዎ ወደ ህክምና በመሄድ
ሀኪምዎን ማማከር ተገቢ ነው፡፡
👉ሳል
የማያቆም ሳል የሚያስቸግሮ ከሆነ እንዲሁም በሚያስሉ
ግዜ ደም የተቀላቀለበት አክታ ካሎት ወደ ህክምና ቦታ በመሄድ መመርመር
ያስፈልጋል፡፡
👉ማዞር
ድንገተኛ የልብ ህመም የማዞር ስሜር እንዲኖር ያደርጋል ከዛም ባለፈ እራስን
እስመሳት ሊደርስም ይችላል
👉ድካም
ከሌላው ግዜ በተለየ መልኩ የድካም ስሜት መሰማት በቀጣይ ቀናት ውስጥ
ድንገተኛ የልብ ህመም ለመከሰት ምልክት ሊሆን ስለሚችል ሃኪሞን ማማከር
ይኖርቦታል፡፡
👉ማቅለሽለሽ ወይንም የምግብ ፍላጎት መቀነስ
ማቅለሽለሽ እና የምግብ ፍላጎት መቀነስ አልፎ አልፎ የድንገተኛ የልብ ህመም
መከሰት ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡
👉በሌሎች የሰውነት ክፍሎች ላይ የሚከሰት ህመም
ድንገተኛ ልብ ህመም ከመከሰቱ አስቀድሞ የህመም ስሜት የሚጀምረው
ከደረት ከዛም ወደ ትከሻ(የግራ ትከሻ) ወደ ክንድ ፤ ጀርባ ፤ አንገት ፤ መንገጭላ
አካባቢ ነው፡፡ ጨጓራ አካባቢ የማቃጠል ስሜትም ሊከሰት ይችላል፡፡
👉ትንፋሽ ማጠር
በቀላል አንቅስቃሴ ከፍተኛ የሆነ ትንፋሽ ማጠር የሚከሰት ከሆነ ከሳንባ ህመም
በተጨማሪ የልብ ህመም ምልክት ሊሆን ስለሚችል ችላ ሊባል አይገባም፡፡
👉ማላብ
በተቀመጡበት በላብ መስመጥ የድንገተኛ የልብ ህመም ምልክት ሊሆን
ስለሚችል ትኩረት ሊሰጡት ይገባል፡፡
👉የሰውነት እብጠት
የልብ ስራ በሚስተጓጎልበት ግዜ በሰውነታችን ውስጥ ፈሳሽ እንዲከማች
ያደርጋል፡፡ ይህም የሰውነታችን የተለያዩ ክፍሎች እንዲያብጡ ያደርጋል (እግር ፣
ቁርጭምጭሚት እና ሆድ አካባቢ) ፡፡ ፈጣን የሆነ ሰውነት ክብደት መጨመርም
እንዲታይ ያደደርጋል፡፡
👉የልብ ምት መጨመር ወይም የተዛባ የልብ ምት
የልብ ምት መጨመር ከማዞር ፣ የድካም ስሜት ከመሰማት እና ትንፋሽ ከማጠር
ጋር ተያይዞ ከመጣ ድንገተኛ የልብ ህመም ምልክት ሊሆን ስለሚችል ወደ
ሀኪም መሄድ ተገቢ ነው፡፡

19/02/2021

የሆድ መንፋት(abdominal bloating)
መንስኤዎች
👉የምግብ አለመስማማት
👉የምግብ አለመፈጨት
👉የአየር በሆድ ውስጥ ከመጠን በላይ መከማቸት
👉የአንጀት ኢንፌክሽን
👉 ሴቶች ላይ ደግሞ ከማህፀን ጋር የተያያዙ ችግሮች
👉የሆድ ድርቀት
👉የሀሞት ጠጠር
👉የተለያዩ የአንጀት ካንሰር
መፍትሄዎች
👉ለችግሩ መንስኤ የሆኑትን የጤና ችግሮችን መታከም
👉መንስኤዎቹ ቀለል ያሉ ከሆኑ ደግሞ የሚከተሉትን ማድረግ
👉በቂ ውሃ መጠጣት
👉ቀለልያሉምግቦችንመመገብ
👉የዝንጅብል ሻይ መጠጣት
ማሳሰቢያ፦ይህን ችግር በጣም ቀለል አድርገን ልንመለከተው አይገባም ምክንያቱም የተለያዩ በሽታዎች ምልክት ሊሆን ስለሚችል!!!
መልካም ጤና!!!

Photos 24/12/2020
Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Address


Addis Ababa