Hailu Buge
finance manger
11/09/2023
እንኳን ለ2016 አዲስ ዓመት አደረሳችሁ‼️
በፈጣሪ ቸርነት 2015ን አልፈን ወደ አዲሱ ዘመን ደርሰናል። ኢትዮጵያ በውጣ ውረድ ውስጥ እያሸነፈች ተጉዛለች።
ጽኑ መርሕ፣ ብርቱ ሕዝብና የማይሸነፍ አምላክ ስላለን እዚህ ደርሰናል።
ብዙ ነገሮችን አሳክተናል፤ አያሌ ፈተናዎችን በድል ተወጥተናል፤ እልፍ መሰናክሎች ቢደረደሩም ጠንካራ መሰረት ሆነውን አልፈዋል።
የተሳኩልን ሁሉ የኅብረ ብሔራዊ አንድነታችን ውጤቶች ናቸው።
የተፈተንባቸው ደግሞ በመለያየት የተነሣ የመጡ ናቸው። በቀጣዩ ዓመት ፈተናዎቻችን እጅግ ቀንሰው፤ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን ከአልማዝ ጠንክሮ፤ የኢትዮጵያን ሰላምና ደኅንነት በጽኑ መሠረት ላይ እናጸናዋለን።
ልማትና ብልጽግናዋን ወደሚመጥናት ደረጃ እናሻግረዋለን።
አዲሱ ዓመት የኢትዮጵያ ብልጽግና ዓመት እንዲሆን እመኛለሁ።
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ጳጉሜን 6 ቀን 2015 ዓ.ም
15/08/2023
ቀናነት ቀና ያለ አስተሳሰብ ውጤት ነው፡፡ ቅንነት በተንኮል ያልታጠፈ፣ በምቀኝነት ያልተቆለመመ፣ በራስወዳድነት ያልተንጋደደ ሃሳብና ምግባር ነው፡፡ የተንጋደደ ማንነት ቀጥ ያለ ሰውነትን አያስገኝም፡፡ ገዳዳ አስተሳሰብ ሕይወትን ያንጋድዳል፡፡ አንዴ ከአስተሳሰብህ ከተጣመምክ በስራህ መቼም ቢሆን ቀጥም ቀናም አትልም፡፡ የጎበጠ ማንነት፣ አንገት የደፋ ሕሊና ቀጥ ብሎ መቆም አይችልም፡፡ በሌሎች የሚዘወር ጭንቅላት የራሱ መሪ የለውም፡፡ በትንሹ ተፈትኖ የወደቅ በትልቁ ሊታመን አይችልም፡፡ ሲያስብ የተሳሳተ ምግባሩም ሆነ ተግባሩ የተሳሳተ ነው የሚሆነው፡፡ ሰው የዘራውን ያንኑ ነውና የሚያጭደው!
ታላቁ የጥበብ ሰው ሩሚ፡-
‹‹የመበላሸትን ወይም የመበከልን ተፈጥሮ ተረዳ፡፡ አንዴ ቁልፍህ ከተጣመመ ወይም ከታጠፈ መቼም ቢሆን ቁልፍህ አይከፍትም፡፡›› ይላል፡፡
እውነት ነው! ራስህን መረዳት ስትጀምር አካሄድህን ታጤናለህ፣ አስተሳሰብህን ትገመግማለህ፣ የምትከተለውን ትመረምራለህ፤ ከፊትህ ያለውን በደንብ ማየት ትጀምራለህ፡፡ መሪህን ትመነጥራለህ፣ ዓላማህን ቀስ ብለህ ትሾፈዋለህ፤ ግብህን ታልማለህ፡፡ መድረሻህን ገና መንገድ ሳትጀምር ወጪና ኪሳራውን ቀድመህ ታሰላዋለህ፡፡፡፡ እየተራመድክበት ያለው “የሕይወት መንገድ አዳላጭ ነው፤ ወይስ ወስዶ ወስዶ ከገደል አፋፍ የሚያደርስ ነው” የሚለውን ለማወቅ አንተነትህን፣ መንገድህንና ዓላማህን መረዳት ይጠበቅብሃል፡፡
የመንገድህን መበላሸት፣ የዓየርህን መበከል፣ የአካሄድህ ግራገብነትን የምትረዳው ራስህንና ዓለሙን ስትረዳ ነው፡፡ የመበላሸት ተፈጥሮን ማወቅ ራስን ከብልሽት ማዳን ነው፡፡ የመኪና መነፋነፍ የብልሽት ምልክት ነው፡፡ የአስተሳሰብ መዛነፍም ውድቀትን ጠቋሚ ነው፡፡ ከብልሽቱ ዓለም ለመውጣት አስተሳሰብን መጠገን ግድ ይላል፡፡ ሊሰምጥ ጫፍ የደረሰ ሰውነትን መታደግ ከምንም በላይ አኩሪና አርኪ ነው፡፡ በሃሳብ ባህር ቀዝፎ፤ በህይወት ውቅያኖስ ተንሳፎ፣ በቀና አስተሳሰቡ ታንኳ የሕይወት ወጀቡንና የኑሮ ሞገዱን የሚያልፍ እሱ በአስተሳሰቡ የጠነከረ፤ ከኑሮው ልምድ የቀሰመ ነው፡፡
ከራሱ ጋር የመነጋገር ልምድን ያዳበረ ጠማማ አስተሳሰቡን ተረድቶ ወደቀናው አስተሳሰብ ይሸጋገራል፡፡ ከራስህ ጋር ለመወቃቀስ ከራስህ ጋር መግባባት ይኖርብሃል፡፡ ወቀሳን የሚቀበል ጭንቅላት ካልፈጠርክ የራስህ ከሳሽ ራስህ ትሆናል፡፡ ከወቀሳ ይልቅ ክስ ውጤቱ ጥሩ አይደለም፡፡ ክስ በመጨረሻ ፍርድ አለው፡፡ ወቀሳ ግን ለራስህ ይቅርታ እንድታደርግለት ነጭ ነጩን ነግሮ ምክር ይለግስሃል፡፡ ወቃሹም ተወቃሹም ራስ ለራስ ነው፡፡
የሚዛናዊነት፣ የአስተዋይነትና የብልህነት ቁልፍ ከታጠፈ ደግ ነገር ሁሉ ላይከፈት ተቆልፎ ይኖራል፡፡ ልብ ከተከረቸመ ቀናነትም ይጠረቀምበታል፡፡ አዕምሮ ከተዘጋ መልካም አስተሳሰብም የተዘጋ ይሆናል፡፡ ሕሊና በምክንያት መውደድና መጥላት ካልቻለ እንደጋሪ ፈረስ በማንም ደመነፍስ ይሾፈራል፡፡ ቁልፍ የሌለው ቤት ለሌባ እንደሚመች ሁሉ ቁልፍ አስተሳሰብ የጎደለውም የማንም ግብስብስ ሃሳብ መጫወጫ ይሆናል፡፡
የሕይወት ጋኑን የሚከፍት ቁልፍ ቅን አስተሳሰብና ምክንያታዊነት ብቻ ነው፡፡ ጋኑ አዕምሮ ነው፤ ቁልፉም አስተሳሰብን ይወክላል፡፡ ብዙ ተመሳስለው የሚሠሩ ቁልፎች ወይም ሃሳቦች አሉ፡፡ የቁልፉን ጋን የሚከፍተው ግን አንዱ ቁልፍ ብቻ ነው፡፡ ያ ቁልፍ የሕይወትህን መስመር፣ የአንተነትህን ጎዳና በርግዶ የሚከፍት ነው፡፡ አዎ ቁልፉ ስሪቱ ከአመለካከትህ ነው፡፡ ጥሬ ዕቃው የበሰለ ሃሳብህ ነው፡፡ በቀላሉ በማንም የማይከፈት ቁልፍ ለማድረግ ግን ማስተር ቁልፍ ያስፈልግሃል፡፡ ስትፈልግ የምትከረችመው፤ ሲያሻህ የምትበረግደው፡፡
24/07/2023
አንተ ሰልረዳኝ ሁሉን አለፈኩ የኔ ጌታ በሕይ ውተ ዘመን ሁሉ ላከበር አደል ሰለሰጣኝ አመሰግናለሁ:: ሁሉ ባንት ይ ቻላል የኔ ጌታ !!!
10/07/2023
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Kara Qore
Addis Ababa