Ethio news
ፈጣን ዜና ከፍለጉ ፎሎ ያርጉ
������
#🅕︎🅞︎🅛︎🅛︎🅞︎🅦︎_🅤︎🅢︎
abussinia bank ቀረታ ተነሳበት
በጣም ነው ያሳቀኝ �
jon daniel
03/12/2025
" ' የቁጥጥር ሰራተኞቹ ይደራደራሉ፣ አላግባብ ደረሰኝ ቆርጠንም እያለ ይቀጡናል ' የሚለውን የግብር ከፋዩን ቅሬታ ለመፍታት ነው ይህ ቴክኖሎጂ የመጣው " - ገቢዎች ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት በከተማ ደረጃ ለመሰብሰብ ያቀደው 350 ቢሊዮን ብር ነው።
ቢሮው ይህንን ገቢ ለመሰብሰብ እንዲችል የሌብነትና ብልሹ አሰራሮች ለመከላከልና የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍና ለማጎልበት ፣ ይረዳሉ ያላቸውን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች በማልማት ወደ ተግባር መሸጋገሩን በዛሬው ዕለት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጿል።
ገቢዎች ቢሮ ይፋ ያደረገው የቦዲ ዎርም የካሜራ ቴክኖሎጂ የቁጥጥር ባለሙያዎችን የቁጥጥር ስራዎቻቸውን በድምፅና በምስል በመቅረፅ ከዋና መስሪያ ቤትና ከቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ለመከታተል የሚያስችል ነው፡፡
ቴክኖሎጂው እያንዳንዱ በቡድን የሚንቀሳቀሱ የቁጥጥር ባለሙያዎች በየትኛው አካባቢ ቁጥጥር እየካሄዱ እንደሚገኝ ፣ ከግብር ከፋዮች ጋር የሚያደርጓቸው ንግግሮች በድምፅና በምስል ከዋና መስሪያ ቤቱ ለመከታተል ያስችላል።
በካሜራ የተደገፈው የቁጥጥር ስራው በአሁኑ ሰአት መርካቶ አንድ እና ሁለት፣ በቦሌ እና ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተሞች የተጀመረ ሲሆን በሚቀጥሉት ቀናት በሌሎች ክፍለ ከተሞችም የሚጀመር ይሆናል ተብሏል።
280 ካሜራዎች በሦስት በሦስት በተዋቀሩ የቁጥጥር ባለሞያዎች አማካኝነት የቁጥጥር ስራውን ያከናውናሉ የተባለ ሲሆን ባለሞያዎቹ ከተሰጣቸው ቦታ ውጪ መንቀሳቀስም ሆነ ከቡድናቸው መነጠል አይፈቀድላቸውም።
ስለ ቴክኖሎጂው ማብራሪያ የሰጡት የገቢዎች ቢሮ ሃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ በቁጥጥር ስራው ወቅት የቢሮው ሰራተኞች በቡድን እንጂ በተናጠል አይንቀሳቀሱም ብለዋል።
አቶ ቢንያም " ሰራተኞቹ የቁጥጥር ስራውን የሚያከናውኑት በቡድን ሆነው ነው አንድ በከተማዋ ውስጥ የሚሰራ የቁጥጥር ሰራተኛ ለብቻው የሚያደርገው ቁጥጥር አይኖርም ሦስት ሰራተኞች በጋራ ሆነው ነው የሚያደርጉት " ነው ያሉት።
" ከሦስቱ በአንዱ ላይ ካሜራ ይገጠማል ፣ሦስቱ በጋራ ይንቀሳቀሳሉ ይቆጣጠራሉ፣ ለእያንዳንዱ ቡድን የተሰጠው አካባቢ አለ ከዛ አከባቢ ውጪ መንቀሳቀስ አይችሉም በሚወጡበት ጊዜ ካሜራው ወደ ዋናው መስሪያ ቤት ጥቆማ(Signal) ይልካል በቀላሉ ሰራተኞቻችን ላይ ቁጥጥር የምናደርግበት ስርዓት ነው ያለው " ሲሉም አክለዋል።
ሃላፊው በሦስት በሦስት ቡድን ተደራጅተው በተዘጋጁት ቡድኖች ላይ ከ 280 በላይ ካሜራዎች ሲገጠሙ ከ 800 በላይ የሚሆኑ የቁጥጥር ሰራተኞችን እንደሚሸፍን ገልጸው የሰራተኞችን ቁጥር በመጨመር በተመሳሳይ የካሜራውም ቁጥር እየተጨመረ እንዲሄድ መታቀዱን ገልጸዋል።
የገቢዎች ቢሮ ሃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ በዝርዝር ምን አሉ ?
" በከተማችን የሚካሄደው የቁጥጥር እና የህግ ማስከበር ስራ ለሌብነት ለብልሹ አሰራር የተጋለጠ ነው የቁጥጥር ሰራተኞቹ ይደራደራሉ፣ አላግባብ ደረሰኝ ቆርጠንም እያለ ይቀጡናል የሚለውን የግብር ከፋዩን ቅሬታ ለመፍታት ነው ይህ ቴክኖሎጂ የመጣው።
ይህ ቴክኖሎጂ በእኛ ቁጥጥር ሰራተኞች እና በግብር ከፋዩ መካከል የሚደረጉ ግንኙነቶችን ግልጽነት እንዲኖረው ለማድረግ የመጣ ነው።
ከእዚህ በኋላ ማንኛውም ነጋዴ በእኛ ቁጥጥር ሰራተኞች ያለአግባብ ተቀጥቻለሁ፣ ኢ ፍትሃዊ በሆነ አግባብ ተቀጥቻለሁ ለሚል ቅሬታ ግልጽ የሆነ መልስ የምንሰጥበት ስርአት የሚዘረጋ ነው።
በቁጥጥር ሰራተኞቻችን ዩኒፎርሞቻቸው ላይ የሚገጠም ፣የሚሄዱበት ቦታ መገኛቸውን የምንከታተልበት፣ የቁጥጥር ሰራተኛው ከተፈቀደለት አካባቢ ውጪ በሚወጣ ጊዜ ምልክት የሚሰጠን፣ ለቁጥጥር በሚሰመ
ኃይል
08/04/2023
#አሁን
" ኢፍጣራችን ለወገናችን " በሚል መሪ ቃል የዘንድሮው ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጧር ስነስርዓት በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በዚሁ ዝግጅት ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምዕመን ተገኝቶ ስነስርዓቱን እየታደመ ነው።
https://t.me/ethionews45
07/04/2023
#ነዳጅ
" ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት #በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈፀማል " - የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን
ከሚያዚያ 16 ጀምሮ አዲስ አበባ ውስጥ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገልጿል።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ገልጾ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት #በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም አሳውቋል።
በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ ማሳሰቢያ ተላልፏል።
የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ጀምሮ #በአስገዳጅነት እንደሚተገበር ተጠቁሟል።
ኢትዮ ቴሌኮም በበኩሉ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በ " ቴሌ ብር " ውጤታማ ስራ ሲሰራ መቆየቱን ገልጿል።
ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በ " ቴሌ ብር " ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አመልክቷል።
የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ ቴክኖሎጂ መገንባቱንም አስረድቷል።
የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር ደግሞ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ያለ ሲሆን በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን ይፈታል ብሏል።
ከዚህ በተጨማሪ መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ሲል አሳውቋል።
#ኢዜአ
https://t.me/ethionews45
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
አዲስ አበባ
Addis Ababa
08/12/2025