Ethio Freedom

Ethio Freedom

Share

የአንድ ነገር መጨረሻ የአዲስነገር መጀመሪያ ነው::
አዳዲስ ሀሳቦችን እንመካከራለን::
የሰውን ልጅ የሚኖረው ለዓላማው የሚያኖረው ከፈጣሪው የተሰጠው ተስፋ ነው

Photos from Ethio Freedom 's post 19/10/2025

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ኡመር ኢድሪስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የቀድሞው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ኡመር ኢድሪስ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተገለፀ፡፡

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ባጋጠማቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ወደ አኼራ ሄደዋል ሲል የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ጠቅላይ ምክርቤቱ በመግለጫው፤ "የሀገራችን ዋርካ እና የሁሉም አባት የነበሩት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ህልፈታቸው የመላው ሀገራችን ህዝብ ሀዘን ነው" ብሏል፡፡

"ሀገራችን ታላቅ አባት አጥታለች" ያለው ምክርቤቱ፤ "እኚህን ታላቅ አባት ላበርክቷቸው ሀገራዊና ሃይማኖታዊ አስተዋፆ በሚመጥን መልኩ ስርዓተ ቀብራቸው በመንግስት ደረጃ ኢስላማዊ ስነ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከናወን ጠቅላይ ምክር ቤቱ ኃላፊነቱን በመውሰድ የሚፈፅም መሆኑን" ጠቁሟል፡፡

ለቤተሰቦቻቸው እና ለመላ ኢትዮጵያ ሙስሊሞች መጽናናትን ይስጣችሁ።

20/09/2025

የአውግቸው ተረፈን “ወይ አዲስ አበባ” ሳነብ አንድ የሚያስቀኝ ክፍል አለ፡፡ ከጎጃም ገጠር የመጣው አውግቸው አንድ ቀን አራዳ ሲዘዋወር “አንድ ረዥም ሕንጻ” ያያል፡፡ እዚያ ሕንጻ ሥር ቆሞ ሽቅብ ሲያየው፣ ሕንጻው “ዘመም እያለ ወጥቶ” ሊወድቅ የደረሰ ይመስለዋል፡፡ ከዚያ “ወግድ ሊወድቅ ነው” እያለ ሩጫውን ተያያዘው፡፡ ሩጦ ሩጦ ከደከመው በኋላ ነበር ሕንጻው እንዳልዘመመና እንደማይወድቅ የገባው፡፡ ለካስ ሊወድቅ የደረሰው በረሃብ የተሰቃየው ራሱ አውግቸው ነበረ፡፡

አንዳንዴ ዋሽንግተን ፓርኪንግ ሎት ውስጥ ተቀምጠው “መንግሥት ሊወድቅ ነው” የሚሉትን ሰዎች ስሰማ አውግቸው ተረፈ ትዝ ይለኛል፡፡
ከሥር ሆኖ፣ ቀና ብሎ ማየት፣ እንዴት ከባድ ነገር ነው፡፡ ራስ ያዞራል።
ከዳኒኤል ክብረት ገፅ የተወሠደ

Photos from Ethio Freedom 's post 18/09/2025

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መመረቅን ምክንያት በማድረግ "በህብረት ችለናል!" በሚል መሪ ቃል ሕዝባዊ የድጋፍ እና የደስታ መግለጫ ሰልፍ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እየተካሄደ ይገኛል።

የትዕይንቱ ታዳሚዎች በሰጡት አስተያየት ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያዊያን የህብረት ውጤት ነው ሲሉ ገልጸዋል።

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የዘመናት ቁጭት ማብቂያ የአብሮነት እና የአንድነት ውጤት ነው፡፡

17/09/2025

አቶ ጌታቸው ረዳ ስለ ጠ/ሚኒስትሩ መጽሐፍ ምን አሉ?

"ጠ/ሚኒስትሩ እንኳንም ሀሳብ ተኮር መጽሐፍ ፃፉ"
‹‹ከረጅም ጊዜ እውቀት አጠር ትንተና ዘመን በኋላ ወደዚህ እውቀት ተኮር ትንተና በመቀላቀሌ ደስተኛ ነኝ፡፡ መጽሐፉ ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ አገሪቱ አላት የሚላትን ችግሮች የዳሰሰ፣ ከዚያም የመፍትሄ አቅጣጫዎችን የጠቆመ በዝርዝር የዳሰሰ በመሆኑ ጊዜ ወስደን ልንነጋገርበት የሚገባ ትልቅ ዶክመንት ነው፡፡

የመጀመሪያውን የመደመር መፅሐፍ አቃቂር ለማውጣት አንብቤዋለሁ፤ ሁለቱ ግን በተፈጠረው ችግር አምልጠውኛል፤ ይኸኛውን ግን እንደዚያ አይደለም ያየሁት፤ ስለዚህ...ሌሎቹንም ፈልጌ ማንበብ አለብኝ፡፡
በ40 አመቱ ግለ ታሪክ ፅፎ አገር አስተምራለሁ የሚል ሰው ባለበት አገር፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እንኳንም ግለ ታሪክ አልፃፉ፡፡ እንኳንም ሀሳብ ተኮር መጽሐፍ ፃፉ።"

17/09/2025

ኢትዮጵያውያን በዘር ሳንከፋፈል በጋራ ስንቆም፤ መፍጠር፣ መፍጠን፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም መዝለል እንችላለን፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Photos from Ethio Freedom 's post 15/05/2025

የወንጂ ስኳር ፋብሪካ የዛሬ ሰባ ዓመት ነበር በጥሩ መሠረት ላይ የተገነባው። ግን ከዘመን ጋር ካልተጓዙ መቅደም ብቻውን መብለጥን አያመጣም። ቀድሞ የበቀለን ጆሮ በኋላ የመጣ ቀንድ ሊቀድመው ይችላል። እየፈጠኑና እየፈጠሩ ዘመኑን ካልቀደሙት፣ ጊዜው ራሱ ይቀድማል።

ወንጂ ስኳር ፋብሪካ የዛሬ ሦስት ዓመት ለሠራተኞቹ ደሞዝ መክፈል ተስኖት ነበር። ዕዳ እንደ መርግ ተጭኖት ነበር። በተሠራው የሪፎርም ሥራ፣ ዛሬ ከ1500 ኩንታል የቀን ምርት ወደ 7000 ኩንታል በቀን ለማደግ ችሏል። ከዚህም ባሻገር ለ14 ዓመታት ከሥራ ውጭ የነበረው የብዙዎች ትዝታ፣ ደስታ ከረሜላ እንደገና መመረት ጀምሯል።

በሌማት ትሩፋት በቀን 3000 ሊትር ወትት እና 20 ሺ ዕንቁላል ማምረት የሚችል ሥራ ተሠርቷል። ግቢው እና መስኩ ለዓይን ይማርካል።

ወንጂ ዘንድሮ የፈተናውን ዘመን አልፎ፣ በዘጠኝ ወር ውስጥ 8.7 ቢልየን ብር ገቢ አስገብቷል።

ይሄ ጠንካራ የሪፎርም ውጤት በሌሎቹ ፋብሪካዎች እንደሚደገም ይጠበቃል። ከሠራን ነገን እንቀድመዋለን።

08/11/2023

don't complain

29/10/2023

እንዴት አደራችሁ
የመኖር አካል ሁን! ለመኖር የወደፊቱን የገና ለገና ውጥን አትጠብቅ ወይም ወደ ኃላ በትዝታ ምናብ አትጓዝ ህይወት ወደ ፊትም ወደ ኃላም አትጓዝም አዕምሮ እንጂ ህይወት ዛሬ አሁን ናት!! ኦሾ

28/09/2023

ኦሾ እንዲህ ይላል
"ራስህን ከመንጋ ወገን አታድርግ ፣ ከሀይማኖት ፣ ከቤሄር እና ከዘር ወገን አታድርግ።

ራስህን ከስነ-ፍጥረት ወገን አድርግ። # ሁሉም ቀርቦልህ ለምን ራስህን በትንሽ ነገር ትገድባለህ

12/09/2023

ዛሬ መስከረም 1 2016 ዓ.ም የማይሆን ሆነ የማይታሰብ ታሰበ የማይደረግ ተደረገ ይሆናል ያልነው ቀርቶ የማይሆነው ሆነ ምድርም አየች ታዘበችም ታሪክም መዘገብች እኛም የታሪክ አካል ሆን :: ምንም እንኳ ዓለም ተገማች አለመሆኗን እና ተለዋዋጭ መሆኗን ባምንም ሰው ከሰው ጋር ያውም የኔ የምልው አጥቼ ዘመኔን ጀምሬያለሁ:: በሰው ተከቦ ብቸኛ መሆን በዘመኔ የገነባሁት የኖርኩለት ድንገት ቢፈርስ ተስፋዬ ተሟጦ የመኖር ትርጉም ባጣም የሆነው የሚሆነው ይህ ነው የኔ እጣ ፋንታ :: እንግድህ ተስፋ ልዝራ ተስፋ መቁረጥን ለማጨድ :: ስለሆነው ስለሚሆነው እጣፈንታዬ ይህ ክህነ እኔም አልኩኝ ከጉልበቴ በርከክ ከወገቤ ጎንበስ ብየ ፈጣሪ ይመስገን የመቻልን ጉልበት የመሆንን ፅናት ስጠኝ :: ስለሆነው ስለሚሆነው ከኔ ፈቃድ ይልቅ አንተ ያልከው ይሆን ዘንድ መረዳትን ትግስትን እና የታዛዥነትን ፅናት ስጠኝ :: ካጣውት ነገር የሰጠኸኝ ይበልጣል :: ክብር ምስጋና ለልዑል እግዚአብሄር ይሁን::

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address


Addis Ababa