Abbaa Jale

Abbaa Jale

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Abbaa Jale, Health/Beauty, Addis ababa, Addis Ababa.

15/04/2025

ብልፅግና የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ዕድገት ለማረጋገጥ የሚስራ ፓርቲ ነው‼️
****

ብልፅግና ፓርቲ እንደ አንድ የፖለቲካ ተቋም መዳረሻ ግቡን የኢትዮጵያንና የኢትዮጵያውያንን ሁለንተናዊ ብልፅግናን ማረጋገጥ አድርጎ የተደረጃ ሀገራዊ ፓርቲ ነው፡፡

ብልፅግና ፓርቲ የኢትዮጵያ ብልፅግና ማለት የጥቂቶች ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያውያን ዜጎች እንደሆነና መሆንም ይገባዋል ብሎ በሚገባ ያምናል፡፡

የኢትዮጵያ ብልፅግና ማለት ውስን ዜጎች ወይም ጥቂት ቡድኖች ብቻ የሚበለፅጉበት ሳይሆን ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ የመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ፓርቲ ነው፡፡

በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልፅግና እውን ሊሆን የሚችለው እንዲሁ የሚገባው በሁሉም አቅጣጫ ከዳር እስከ ዳር የሚገኙ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ አቅም ተሳታፊ በመሆን የበኩላቸውን ድርሻ ሲያበረክቱ እንደሆነ ብልፅግና ፓርቲ በሚገባ ይረዳል።
www.kolfeprosperityparty.org.et


https://heylink.me/KolfeProsperity/

Photos from Prospertiy Party Kolfe Keraniyo Sc Branch - ብልፅግና 's post 07/04/2025
07/04/2025
07/04/2025

የመደመር ትውልድ ታሪካዊ አሻራችን ለሉዓላዊነታችን !

የሀገራችን ሉዓላዊነት ምልዑ የሚሆነው ሁለንተናዊ ብልፅግናችን ሲረጋገጥ ነው።

ህብረ ብሔራዊ አብሮነታችን ሲጠናከር ፣ የወንድማማችነት እና የእህትማማችነት ሀገራዊ እሴቶቻችን ሲጎለብቱ ፣ የሀገረ መንግስት ግንባታችን መሰረት ሲፀና ፣ የምንመኛት የታፈረች እና የተፈራች ሉዓላዊት ሀገር ዕውን ትሆናለች።

የእርስ በእርስ ግጭቶች እና ጦርነቶች በታሪክ አጋጥመውን ለነበሩ የውጭ ጣልቃ ገብነቶች ሁሉ እንደ ምክንያትነት ይጠቀሳሉ።

ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብቷ እንዳትጠቀም ሌት እና ቀን ለሚሰሩ ታሪካዊ ጠላቶቻችን የእርስ በእርስ ግጭቶቻችን ሰርግና ምላሻቸው ነው ።

የውስጥ ባንዳ እና የውጭ ባዳ ሀገራችንን ለማድማት ከሚጠብቁት ምቹ ሁኔታ መካከል የውስጥ መከፋፈል ዋናው ነው፡፡

ሀገራዊ ለውጡ እውን ከሆነ ወዲህ አወንታዊ ሰላም ለመገንባት እየተደረገ የሚገኘው ሁለንተናዊ ርብርብ የሀገራችንን ተጋላጭነት ለማስቀረትም ፋይዳው የጎላ ነው።

ድህነት የሀገራችን ሉዓላዊነት እንዲሁም የህዝባችን ደህንነታ ዋነኛው ጠላታችን ነው፡፡ ሁለንተናዊ ብልፅግናችን ካላረጋገጥን አስተማማኝ እና ዘላቂ ሰላማችን ጥያቄ ውስጥ መግባቱ አጠያያቂ አይሆንም።

በአዲስ አስተሳሰብ ፣ በዳበረ የስራ ባህል ቀን እና ሌት በመስራት አዲስ አበባን የኢትዮጵያ ብልፅግና ተምሳሌት ፣ ኢትዮጵያን ደግሞ የአፍሪካ ብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ እየተደረገ የሚገኘው ብርቱ ትግል ግቡ ድህነት ከደቀነብን የህልውና አደጋ በማውጣት የኢትዮጵያን የማንሰራራት ዘመን ማብሰር ነው።

ህዝባችን በየጊዜው በከፈለው መስዋዕትነት ዳር ድንበራችንን አስጠብቆ የሀገራችንን ሉዓላዊነት ባለማስደፈር ለአፍሪካዊያን ጭምር አኩሪ ታሪክ መፃፍ ችሏል፤ የከፈልነው የደም መስዋዕትነት ግን ብቻውን አንገታችን ቀና አድርገን እንድንጓዝ አላስቻለንም።

እጆቻችንን ለልመና እየዘረጋን ፣ ለመኖር የሚያስፈልጉ መሰረታዊ ፍላጎቶቻችንን ጭምር ሳናሟላ ፣ በኋላቀር ፖለቲካ ተቸክለን ፣ የዓለም ጭራ እስከመሆን ደርሰን የተሟላ የሀገር ሉዓላዊነት አለን ልንል አንችልም።

ኋላቀር የፖለቲካ ባህላችን ያስከተለውን ታሪካዊ ስብራት ለመጠገን የለውጡ መንግስት ዘርፈ ብዙ እርምጃዎችን ወስዷል።

ከትናንት ወደ ዛሬ የተሸጋገሩ ችግሮቻችን የሚፈቱት በፅንፈኝነት አስተሳሰብና ተግባር ሳይሆን ወደ መካከለኛው መንገድ በመቀራረብ መሆኑ ላይ ፅኑ እምነት የያዘው ብልፅግና ፓርቲ አካታች የሆነ የፖለቲካ ስርዓት እየገነባ ይገኛል።

ሉዓላዊነታችን የተሟላ የሚሆነው ዘመኑ የሚጠይቀውን መስዋዕትነትም መክፈል ስንችል ነው ፤ አሁን ላይ ከመደመር ትውልድ የሚጠበቀው መስዋዕትነት የላብ መስዋዕትነት ነው፡፡

ላብአችንን ጠብ አድርገን ሌት እና ቀን በመስራት ብልፅግናችንን ስናረጋግጥ እኛም ሆነ ቀጣዩ ትውልድ የሚኮራባት የታፈረች እና የተከበረች ሀገር መገንባት እንችላለን።

የመደመር ጉዟችን መዳረሻው ሁለንተናዊ ብልፅግናን ማረጋገጥ ነው፡፡ የሰላሙን ጉዳይ በይደር አቆይቶ ልማት ላይ ማተኮር ወይም ደግሞ ልማትን ወደ ጎን ትቶ ሰላምን አረጋግጣለሁ የሚል እሳቤ የመደመር ትውልድ መለያ አይደለም።

አንዱን ጥሎ አንዱን አንጠልጥሎ ሳይሆን ልማትም ሰላምም መሳለመሳ መጓዝ የሚችሉ እንጅ የሚቃረኑ ስላልሆኑ ለሁለቱም ተገቢውን መስዋዕትነት በመክፈል ሁለቱንም እናረጋግጣለን።

በአንድ እጃችን እየተዋጋን ሌላኛውን እጃችን ከልማታችን ሳንነቅል ተደቅኖብን የነበረውን የህልውና አደጋ በመቀልበስ ፈጣን ዕድገታችንን ማስቀጠል የተቻለውም ከለውጡ በኋላ በመጣው የተለወጠ አስተሳሰብ መሆኑን ልብ ይሏል።

የሀገር ልዕልና የሚረጋገጠው ድህነትን ድል በማድረግ ነው ሲባልም የአባት የእናቶቻችን የሀገር ዳር ድንበር የመጠበቅ አኩሪ መስዋዕትነት በመዘንጋት አይደለም ፤ እኛ ሰላማዊ ስለሆነን ብቻ ሰላማችንን ማረጋገጥ ስለማይቻል ከውስጥም ከውጭም ሊኖሩ ለሚችሉ ትንኮሳዎች ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት ደግሞ የመከላከያ ሰራዊታችንን አስተማማኝ አቅም መገንባታችንን እናጠናክራለን።

ከለውጡ ጀምሮ መከላከያ ሰራዊታችን የኢትዮጵያን ህብረ ብሔራዊ መልክ እንዲላበስ አካታችነቱ ላይ ሰፋፊ ስራዎች ተሰርተዋል ፤ ተጨባጭ ውጤቶችም ተመዝግበዋል።

ሰራዊታችን ዘመኑ በደረሰበት የቴክኖሎጂ አቅም እንዲገነባም በልዩ ትኩረት እየተሰራ ሲሆን በአጭር ጊዜ ውስጥም የተወዳዳሪነት ደረጃውን ማሳደግ ተችሏል።

መከላከያ እንደ ተቋም ሀገርን ከማናቸውም አይነት ጥቃቶች መከላከል የሚያስችል አቅም ለመገንባት ከሚያደረገው ርብርብ ባሻገር ለሀገራችን ፈጣን ዕድገትም በተለያየ መልኩ አሻራውን እያሳረፈ ይገኛል።

ተቋሙ ትጥቁንም ስንቁንም በራሱ ለመቻል እያደረገ የሚገኘው ብርቱ ጥረት ተስፋ ሰጪ ነው፡፡ በቴክኖሎጅውም በግብርናውም ፈጠራና ፍጥነት በታከለበት አግባብ የድርሻውን እየተወጣ የሚገኘው መከላከያ ህዝባችን ላይ የሚደቀኑ ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ ችግሮችን ሁሉ ፊት ለፊት በመጋፈጥ አለኝታነቱን አስመስክሯል ፤ ህዝባችንም አስተማማኝ ደጀንነቱን እያረጋገጠለት ይገኛል።

በማንም ሳትደፈር የተነኮሷትን ሁሉ አዋርዳ በመመለስ ሉዓላዊነቷን አስጠብቃ የዘለቀችውን ኢትዮጵያን ለክፉ የማያስቧት የተፈራች ሀገር ለማድረግ መከላከያ ሰራዊታችን በአደረጃጀትም ፣ በሰው ኃይልም አስተማማኝ ቁመና ላይ ይገኛል።

ተተኳሽ መሳሪያዎችን በራሱ አቅም ለማሟላት የጀመረው እንቅስቃሴ ደግሞ ለሌሎች ሀገራትም በመትረፍ የውጭ ምንዛሬ ማስገኘት መጀመሩን ክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ ከሁለት ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ የተገነባውን የሆሚቾ ጥይት ፋብሪካ ሲመርቁ መግለፃቸው ይታወሳል።

ለሲቪልና ወታደራዊ አገልግሎት የሚውሉ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን የሚያመርተው እና ሰሞኑን በክቡር ጠ /ሚ ዶ /ር ዐብይ አህመድ የተመረቀው የስካይ ዊን ኤሮኖቲክስ ኢንዱስትሪም የሰራዊታችንን የመከላከል አቅም በማሳደግ ለሀገራችን ብቻ ሳይሆን ለቀጠናው ሁሉን አቀፍ ሰላም አለኝታነቱን የሚያረጋግጥ ነው፡፡

ሁለንተናዊ ብልፅግናችንን እውን በማድረግ ታፍራና ተከብራ የምትኖር ሉዓላዊት ሀገር በመገንባት የመደመር ትውልድ ታሪካዊ አሻራችንን በወርቃማ ቀለም እንፅፋለን።

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address


Addis Ababa
Addis Ababa