ETHIO kenubish
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ETHIO kenubish, Health/Beauty, Addis Ababa.
25/04/2025
25/04/2025
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!
ውድ የክርስትና እምነት ተከታዮች ከሁሉ አስቀድሜ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነትና የጤና እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።
በዓሉን በማከበርበት ወቅት ልክ እንደሁል ጊዜው የሌለውን በማስታወስ የመረዳዳት፣ የመተባበርና የመደጋገፍ እሴቶቻችን ተግባራዊ በማድረግ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን ማዕድ በማጋራትና በመርዳት ወንድማማችነታችንን እና እህትማማችነታችንን በተግባር ማረጋገጥ ይኖርብናል፡፡
ውድ የእምነቱ ተከታዮች በዓሉን ስናከብር ፍቅርን ፣ መተሳሰብን፣ አንድነትን፣ ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን ባጠናከረ መልኩ እዲሆን ጥሪዬን እያቀረብኩ በዓሉ የሰላምና የፍቅር እንዲሆን ከልብ እመኛለሁ።
በድጋሚ እንኳን አደረሳቹህ !!
አቶ ሙሉጌታ ጉሉማ
የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ብልጽግና ፖርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ
25/04/2025
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ!!
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለከተማ ወረዳ 10 ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደስታው ካሳው ለስቅለትና ለትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፦
በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደስታው ካሳው ለ2017 ለስቅለትና ለትንሳኤ (ፋሲካ) በዓል የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላለፉ።
ሀላፍው አክለውም፦ለወረዳችን፣ ለሀገራችን እንዲሁም በመላው ዓለም ለምትገኙ የክርስቲና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለስቅለትና ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!
የኢየሱስ ክርስቶስ ስቃይና ሞት እንዳለ ሆኖ ምህረት፣የዘላለም ሕይወት ፣የመንፈስ ጥንካሬና ጽናት የተገኘው በትንሳኤው መሆኑ ለክርስትና እምነት ተከታዮች በዓሉን ልዩ ያደርገዋል።
በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ከሚከበሩ አበይት በዓላት መካከል በድምቀት የሚከበርና ትልቅ ትኩረት የሚሰጠው የፋሲካ በዓል የሰላም የፍቅር የደስታ እንዲሆን መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ።
በዓሉ ሲከበር የሀገራችን እንዲሁም የወረዳዋ መገለጫ የሆኑትን የመረዳዳትና የመተሳሰብ መልካም እሴቶችን አጠናክሮ በማስቀጠል መሆን አለበት።
በዝቅተኛ የኑሮ ሁኔታ ላይ የሚገኙ እህት ወንድሞች አቅመ ደካሞች በዓሉን በደስታና በምስጋና ማሳለፍ እንዲችሉ ካለን በማካፈል በጋራ ማክበር እንደሚገባ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ ።
በቀጣይ ሰላምን በማስቀጠል በሁሉም መስክ ልማትን በማፋጠን ለወጣቶችና ሴቶች የስራ ዕድል ፈጠራን በማስፋት የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በሚሰራው ስራ ድጋፍና ተሳትፎው እንዲጠናከር እጠይቃለሁ።
በድጋሚ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለስቅለትና ለፋሲካ በዓል በሰለም አደረሳችሁ በዓሉ የሰላም የደስታ የፍቅርና የመተሳሰብ በዓል ይሆን ዘንድ መልካም ምኞቴ ነው።
መልካም በዓል ይሁንላችሁ !!
አቶ ደስታው ካሳው
ሚያዚያ 12/2017ዓ.ም
25/04/2025
25/04/2025
የወረዳው አስተባባሪ ኮሚቴ መልዕክት
እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አስተባባሪ ኮሚቴ ትንሳኤ በክርስትና አምነት ተከታዬች ዘንድ የሚከበር ክርስቶስ ለሰው ልጆች ያለውን ጥልቅ ፍቅር የገለጠበት ከሞት ወደ ህይወት ሊያሸጋግረው በመከራ መስቀል ተሰቅሎ ሞትን ድል ነስቶ የተነሳበት ለፍቅር የተከፈለ ዋጋ የታየበት ድንቅና ታላቅ በዓል ነው።
የትንሣኤ በዓል የሰላም፣የቅር፣ የመቻቻል፣ የመደጋገፍ፣የመተባበር፣ የመተሳሰብና የወንድማማችነት እና እህትማማችነት እንድሁም የህብረብሔራዊ አንድነትና አንዳችን ለአንዳችን የምንሆንበት በዓል እንድሆን ልባዊ ምኞታችን እንገልፃለን።
በድጋሚ መልካም የፋሲካ በዓል!!
የኮልፌ ቀራንዮ ወረዳ 10አስተባባሪ ኮሚቴ
25/04/2025
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa