Samvision eye Clinic

Samvision eye Clinic

Share

Eye clinic

09/08/2018

ግላኮማ( Glaucoma)
በቃለአብ ገነነ (opto.)

ግላኮማ በዋነኝነት የዓይን ዉስጥ ግፊት ከተገቢዉ በላ ይጨምሮ የእይታ ማሰተላለፊያ ነርቭ ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ በጊዜ ሂደት መመለስ የማይችል የእይታ አድማስ መቀነስና ሙሉ ለሙሉ የዓይን ብርሀንንየ ሚያሳጣ ህመም ነዉ፡፡ በቀላሉ ግላኮማን በሁለት ከፍለን ማየት እንችላለን ይህም ክፍት ማእዘን ግላኮማ (open angle glaucoma) እና ዝግ ማእዘን ግላኮማ (closed angle glaucoma)
1. ለክፍት ማእዘን ግላኮማ(open-angle glaucoma) አጋላጭ ሁኔታዎች ዉስጥ ዋናዋናዎቹ፡-
* እድሜ (ከ50 አመት በላይ)
* በዘር በመተላለፍ
* ማዮፒያ (short-sightedness)
* ሌሎች የሰዉነት ህመሞች ለምሳሌ እንደ ደም ግፊት፣የስካር ህመምና የልብችግር የመሳሰሉት
* ረጅም ጊዜ ኮርቲኮሰቴሮይድ መድሃኒቶችን መጠቀም
* ሲጋራማ ጨስና ከመጠን ያለፈ አልኮል መጠጣት

2. ለዝግ አንግል ግላኮማ(closed-angle glaucoma)ከሚያጋልጡ ነገሮች ዋናዋናዎቹ፡-
* እድሜ
* በተፈጥሮ ትንሽ መጠን ያለዉ የዓይን ኳስ
* ጻታ ( በሴቶች ላይ የበለጠ ይታያል)
* ዓይን ላይ የደረሰ ምት ወይ ምአደጋ
* በዓይን ዉስጥ ያሉ ክፍሎች በተለያየ ምክንያት መቆጣት
* ህክምና ሳይደረግለት የቀረ የዓይን ሞራ

በሳም ቪዥን የዓይን ክሊኒክ ንኪኪ በሌለዉ ሁኔታ የዓይን ግፊትን በመለካትና የእይታ አድማስን (visual filed) በመለካት ግላኮማን የከፋ ጉዳት ሳያደርስ ለማወቅ የሚያስችል ዘመናዊ የዓይን ህክምና መሳሪያዉችን በመጠቀም እንደአስፈላጊነቱ የህክምና አማራጮች ያቀርባለ፡፡
እነኝህም፡-
=>የመድሐኒት ህክምና ከቅርብ ክትትል ጋር
=>የጨረር ህክምና
=>የቀዶ ህክምና

ለበለጠ መረጃ በ0944751322/0941545454 ደዉለዉ ማማከር ይችላሉ፡፡
ሳም ቪዥን ልዩ የዐይን ክሊኒክ

05/08/2018
20/06/2018

Only on our retail shops!

10/05/2018

ከአይን ጤና ጋር በተያያዘ ጥያቄ ወይም ማማከር ይፈልገሉ? በፅሁፍ መልእክት (inbox) የድርጉልን ወይም በስልክ ቁጥር 0944751322/ 0941545454 ደውለው ማማከር ይችላሉ፡፡
በአካል መምጣት ለምትፈልጉ አድራሻችን ፦
ሳር ቤት ብስራተ ገብርኤል
ሆም ዴፖ ፊትለፊት
ሳን ህንፃ 3ተኛ ፎቅ
ሳም ቪዥን ልዩ የዓይን ክሊኒክ!!

05/05/2018

May is Healthy Vision Month. To enhance vision worldwide, the WCO hopes that you will support optometry’s expansion of scope, support legislation promoting eye health and schedule your eye examination with your optometrist.

Parasitic Worms Found in a Woman's Eye—First Case of Its Kind 28/02/2018

Parasitic Worms Found in a Woman's Eye—First Case of Its Kind An Oregon woman’s infection marks the first time on record that an eye worm species normally found in cattle has been seen in humans.

24/02/2018

SAM VISION EYE CLINIC!

21/02/2018

የዓይን መነፅር እይታችንን እነዴት ያስተካክላል?
በመነፅር መስተካከል የሚችል የእይታ ችግር የምንላቸዉ በርቀት የማየት ችግር (Myopia) እንዲሁም በቅርበት የማየት ችግር (hypermetropia) ናቸዉ፡፡
በርቀት የማየት ችግር (Myopia):- የሚፈጠረዉ ምስል ብርሀን መቀበያ (retina) ጋረ ሳይደርስ በሚፈጠርበት ጊዜ ነዉ፡፡ ይህም ችግር ከዓይን በሌን (cornea) እስከ ብርሀን መቀበያ (retina) ያለዉ የዉስጥ ርዝመት ትልቅ ሲሆን ወይም የብሌን (cornea) ብርሀን ጨረርን የመስበር አቅሙ ከፍተኛ ሲሆን የሚፈጠር ነዉ፡፡ ይህን የእይታ ችግር በስርጉድ ሌንስ (concave lens) መስተካከል ይቻላል፡፡ ስርጉድ ሌንስ የብርሀን ጨረር በዉስጡ ሲያልፍ ይበትናል ይህም የዓይናችን ሌንስና ብሌን ምስሉን ብርን መቀበያ ላይ እንዲፈጥሩ ይረዳቸዋል፡፡
በቅርበት የማየት ችግር(hypermetropia) :-ችግሩ የሚፈጠረዉ ምስል ከብርሀን መቀበያን (retina) አልፎ ሲፈጠር ነዉ፡፡ ይህም የበሌን ብርሀንን የመስበር አቅም ከዓይናችን የውሰጥ ርዝመት ጋር ሳይመጣጠን ሲቀር ወይም የዓይናችን የዉስጥ ርዝመት አነስተኛ ሲሆን ይፈጠራል፡፡ በእድሜ ከ 40 ዓመት በላይ ሲሆን ሌንሳችን ቅርፅ የመቀየር ችሎታዉን እያጣ ይመጣል ይህም ምስል በትክክል ብርሀን መቀበያ ላይ እንዳይፈጠር ያደርጋል፡፡ ይህ ችግር ፕረስባዩፒያ (presbyopia) ይባላል፡፡ እብጥ ሌንስ (convex lens) ይህንን ችግር ለማስተካከል እንጠቀምበታለን፡፡ ብርሀን በእብጥ ሌንስ (convex lens) ዉስጥ ሲያልፍ ይሰበሰባል ይህም ሌንስንና ብሌንን በማገዝ ምስል ብርሀን መቀበያ ላይ እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡
ለበለጠ መረጃ ሳም ቪዝን ልዩ የዓይን ክሊኒክ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 0944751322/0941545454 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

Amsler Grid | Prevent Blindness 15/02/2018

ከእድሜ ጋር ተያይዞ የሚመጣውን የብርሃን መቀበያ (retina) ማርጀት ይህን በማውረድ እራስዎትን ይመርምሩ!
ለበለጠ መረጃ 0941545454/094751322 ደዉለው ማማከር ይችላሉ!
ሳምቪዥን ልዬ የዓይን ክሊኒክ!!

Amsler Grid | Prevent Blindness Amsler Grid Printable Amsler Grid Page , Amsler Grid Instructions Click here, to download and print our Amsler Grid and instruction card, featuring Betty

15/02/2018

After successful surgery @ samvision eye clinic.

Photos 26/01/2018

Red-green color blindness is the most common type of color vision loss. Eye care professionals use the Ishihara Color Test to check for red-green color blindness — and it looks a little something like this.

Learn more about color blindness: https://nei.nih.gov/health/color_blindness/facts_about

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address


Addis Ababa