Yeab sera medium clinic and diagnostic Laboratory
it is a basic medical laboratory center found in Hawassa city alamura near kerod caffe it is a pri
03/12/2025
« ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ »
አንድ ገዳማዊ አባት የዚህን ትውልድ አካሄድ ታዝበው እንዲህ አሉ . . .
" . . በአፍላ ትጀምራላችሁ በወረት ትተውታላችሁ፤ ያወቃችሁትን ረስታችሁ ያላወቃችሁትን ለማወቅ ትጥራላችሁ፤ የያዛችሁትን ትረግጣላችሁ፣ የረገጣችሁትን ትይዛላችሁ፤ ምኞታችሁ ብዙ ነው፣ አምሮታችሁ ልክ የለውም። ያማራችሁን ስታገኙ ወዲያው ይሰለቻችኋል፣ ተው የተባላችሁትን ትሽራላችሁ፣ የተከለከላችሁትን ትደፍራላችሁ የተፈቀደላችሁን ችላ ትላላችሁ።
ቤተ መቅደስ እንዳትገቡ ብትከለከሉ ወደ ፊት ቤተ መቅደሱን በመስታውት ሠርታችሁ መቅደስ ባትገቡም እንኳን ሁሉን ከውጭ ሆናችሁ ማየት ትፈልጋላችሁ። ሁሉን ማወቅ ትፈልጋላችሁ በአንዱም ግን አትጠቀሙበትም። ሁሉ አላችሁ ግን ባዷችሁን ናችሁ። ሃይማኖት እንጂ እምነት የላችሁም"።
በስሜት እየናጡ ቀጠሉ . . .
"ተምራችሁ እውቀት ስታገኙ ሠርታችሁ ሀብት ስታፈሩ ከላይ የሆናችሁበትን ሀገር ለቃችሁ ሰፋ ወዳለው እንሂድ ብላችሁ እንደገና ከታች ትጀምራላችሁ፣ ትቀጥላላችሁ በመጨረሻ ከጀመራችሁበት ትገኛላችሁ። ቸኩላችሁ ትወስናላችሁ ወዲያው ትጸጸታላችሁ። በጽኑ ታማችኋል"።
"ከታሪክ ፍቅርንና ልማትን ሳይሆን ጥላቻንና ጥፋትን ለይታችሁ ትቆፍራላችሁ። ከዚያም ቀጥላችሁ የከበረ ማዕድን እንዳወጣችሁ ሁሉ በኩራት ደረታችሁን ነፍታችሁ ሳትመርጡ ሁሉን በአደባባይ ትዘሩታላችሁ የአሸናፊነትንና የተሸናፊነትን ሃውልት በአንድ ላይ ታቆማላችሁ። ለግልፅነትና ለነፃነት እያላችሁ በምታደርጉት ሽኩቻ እርቃን ወደመሆን ወረዳችሁ።
በዚህ አለም ጥድፊያ ታማችኋል ሀገራችሁን ትንቃላችሁ፣ ጥላችሁ ለመሄድ ትፈልጋላችሁ ከሄዳችሁ በኋላ ደግሞ አፍታ ሳትቆዩ ሀገሬ ናፈቀኝ ትላላችሁ በቁማችሁ የናቃችሁትን አፈር በሞታችሁ ልትለብሱት ትመኛላችሁ። ለሀገሬ አፈር አብቃኝ ብላችሁ በድናችሁን ልካችሁ የወገኖቻችሁን ልብ ትሰብራላችሁ።
በዚህ የተነሳ ምሥጢር ለመካፈል ቅርስ ለመረከብ የሚያስችል ስብእና አልገነባችሁም። እኛ ገዳማውያን የመገናኛውን ድልድይ ስላልሠራንና ከእናንተ ስለራቅን ሳይሆን ስለማታዩት ወይም ማየት ስለማትፈልጉት አለበለዚያም እንደ ልቦለድ ገፀ ባህርይ የራሳችሁን ያሸበረቀ አስረካቢ ፈጥራችሁ እውኑን ሳይሆን ምናባችሁን መረከብ ፈለጋችሁ። እኛ ደግሞ እናንተ ታዩን ዘንድ አላሸበረቅንም ማሸብረቅም አንፈልግም በዚህ ምክንያት ለእናንተ ምሥጢር ለመንገር ቅርስ ለማውረስ ከባድ ሆኗል።
እኛ አባቶቻችንን እናምናለን፤ በእነርሱም ደስ ይለናል የነገሩንን ተቀብለን ቃል ኪዳናቸውን ጠብቀን እንኖራለን።
"ጽላተ ሙሴ አክሱም ጽዮን እንዳላች ሲነግሩን መጋረጃ ገልጠን ሳጥን ከፍተን እንይ አላልንም።
"ጌታ የተሰቀለበት የግማደ መስቀሉ ክፋይ ግሸን ማርያም አለ ሲሉን ቆፍረን አውጥተን እንይ አላልንም።
"ቅዱሱ ጽዋ መንዝ ውስጥ አለ ሲሉንም ዋሻ እናስስ አላልንም።
አባቶቻችንን አምነን ሀገራችን የበረከት ምድር መሆኗን ተረድተን የጌታችንን የፀጋ ስጦታ ተቀብለን በእምነት እንኖራለን። ምንም የለንም፤ ሁሉ ግን የኛ ነው። ድሆች ብንባልም ባለጸጎችም ነን። የተራቆትን ብንመስልም የጸጋ ልብስ አለን። ሐዘንተኞች ብንመስልም ደስተኞች ነን። ስለ ሀገራችን መባረክ፣ ቅድስት ሀገር መሆን፣ ቅዱስ ቅርስ በእጃችን እንዳለ ዓለም እንዲያረጋግጥልን አንፈለግም"።
አባ በአጭሩ የሚመለሱ አይመስሉም እንደ ጥሩ ተኳሽ ኢላማቸውን እያጠበቡ ይህን ትውልድ ይቀጠቅጡት ይዘዋል።
》 #ከእመጓ መጽሀፍ የተወሰደ።
ሺኖዳ መጻሕፍት አቅራቢ//𝐒𝐡i𝐧𝐨𝐝𝐚 𝐁𝐨𝐨𝐤𝐬 𝐃𝐞𝐥𝐢𝐯𝐞𝐫𝐲
📍መንፈሳዊና አለማዊ መጻህፍት፣
📍የትምህርት መርጃ መጻህፍት፣
📍የልብወለድና የታሪክ መጻህፍት፣
📍የግጥምና የወግ መጻህፍት፣
📍የፖለቲካና ኢኮኖሚ እሳቤ መጻህፍት፣
📍የፍልስፍና እና የስነልቦና መጻህፍት ሁሉንም እኛጋ ያገኛሉ።
ሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ማንኛውንም መጽሐፎችን ይዘዙን። ያለ ተጨማሪ ክፍያ እንልክለዎታለን✈️ ባሉበት እናደርስልዎታለን።🚴♂
መጽሐፍቶችን ለማዘዝ👇
💬https://t.me/Shinodabooks
ከዚህ በታች ሁሉም ማህበራዊ ሚዲያዎቻችንን ሊንክ አስቀምጠናል። በቅንነት ተወዳጁን!
!
➡️Tiktok➦ tiktok.com/
➡️Telegram➦ https://t.me/shinodabooksdelivery
➡️YouTube➦https://www.youtube.com/
➡️Facebook➦ https://www.facebook.com/share/1DFjW4kq84/
03/12/2025
03/12/2025
03/12/2025
👑ታቦተ ጽዮን እና ታሪካዊ አመጣጥዋ👑
ከሲና ተራራ እስከ ኢትዮጵያ ታሪካዊ ዳራ እንመልከት
በትእግሥት አንብበው ለሌላውም ያድርሱ
መግቢያ
ታቦተ ጽዮንን ማዕከል ላደረገው ትምህርትዎ የሚሆን
"ውድ አባቶቻችንና እናቶቻችን ወንድሞችና እህቶች ልጆችን ጨምሮ ይህንን ጽሁፍ የምታነቡ ሁላችሁም እንኳን ለእመቤታችን የህዳር ጽዮን በዓል አደረሳችሁ ፣
ዛሬ ሁላችንንም የሚያስተሳስረን፣ የሀገራችንን ዕድል የወሰነ እና የሕይወታችንን ትርጉም የሚገልጽ ታላቅ ምሥጢር እንመልከት
በሺህ ዓመታት ታሪክ ውስጥ፣ ከግብፅ በረሃ እስከ ዮርዳኖስ ወንዝ፣ ከኢያሪኮ ግንብ ግርጌ እስከ ንጉሥ ሰሎሞን ቤተ መቅደስ ድረስ፣ ከዚያም በተአምርና በክብር ተጉዛ እስከ ኢትዮጵያ ምድር ድረስ የደረሰችውን የቃል ኪዳኑን ታቦት ክብር ልብ ብለን እንመልከት!
ታቦተ ጽዮን የድንጋይ ሳጥን ብቻ አይደለችም። እርሷ የእግዚአብሔር ማደሪያ፣ የቃሉ ምስክር እና የኃጢአት ሥርየት ማዕከል ናት። በታሪኩ ውስጥ፣ የገፏትን ሁሉ የገዛች፣ ንጉሥ የናቅችውን ሜልኮልን መካን ያደረገች፣ ጠላት የሰገደላት እና ውኃ የከፈለች አምላካዊ ኃይል የተገለጠባት በእግዚአብሔር ጣት ቃሉ የተጻፈባት የአማናዊቷ ታቦት የእመቤታችን ምሳሌ የሆነችውን ታቦት ታሪካዊ አመጣጥ እንመለከታለን ።
ታዲያ የዛሬው ዘመን ምዕመናን፣ ካህናት፣ ወላጆች እና ወጣቶች፣ የዚህ ታላቅ ቃል ኪዳን ጠባቂዎች እንደመሆናችን መጠን፣ ከታቦቱ ታሪክ በየድርሻችን ምን እንማራለን? ቅድስናን ለመጠበቅ፣ ኃላፊነትን ለመወጣት እና በእምነት ለመኖር ከቀደሙት አባቶቻችንስ ምን እንቀዳለን?
እስኪ አብረን ወደዚህ ታሪካዊና መንፈሳዊ ጉዞ እንግባ!..."
📜 የታቦተ ጽዮን አመጣጥና ታሪክ (የብሉይ ኪዳን ክፍል)
📜1ኛ የእግዚአብሔር ታቦት ከእግዚአብሔር ለሰው የተሰጠበት ምክንያትን በአጭሩ እንመልከት
የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት የተሰጠባቸው ዋና ዋና ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው።
አንደኛ የእግዚአብሔር መገኘት ምልክትና ማደሪያ
(ዘጸአት 25÷22) ነው
ታቦቱ በምድራዊው መቅደስ (ማደሪያው ድንኳን) ውስጥ የእግዚአብሔር ምልአት መገኘት መገለጫ ነበር። እግዚአብሔር ከሁለቱ ኪሩቤል መካከል ሆኖ ሕዝቡን እንደሚናገርና መመሪያ እንደሚሰጥ ቃል ገብቷል። ታቦቱ ከሕዝቡ ጋር አብሮ ሲጓዝ፣ የእግዚአብሔር ጥበቃ ከእነርሱ ጋር መሆኑን ያመለክታል።
"በዚያም ከአንተ ጋር እገናኛለሁ፥ በሥርየቱም መክደኛ ላይ ባሉት በሁለቱ ኪሩቤል መካከልም ከእስራኤል ልጆች ጋር የምነጋገርበትን ነገር ሁሉ እናገርሃለሁ።" (ዘጸአት 25÷22)
ሁለተኛ የቃል ኪዳኑ ምስክር (ዘጸአት 25÷16)
ታቦቱ የእግዚአብሔርን ሕግጋትና ትእዛዛት የተቀረጹበትን የድንጋይ ጽላቶች (የምስክሩ ጽላት) ለመያዝ ተሠራ። ይህ የሚያመለክተው እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ያደረገው የጽሑፍ ውል ማኅተም ነው።
"እኔም የምሰጥህን ምስክር በታቦቱ ውስጥ ታኖራለህ።" (ዘጸአት 25÷16)
ሦስተኛ የኃጢአት ሥርየት ማዕከል
(ዘሌዋውያን 16÷2. ||. 14÷16)
ታቦቱ የኃጢአት መሥዋዕት የሚቀርብበትን የሥርየት መክደኛ ይዞ ነበር። ሊቀ ካህኑ በዓመት አንድ ጊዜ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ገብቶ ለሕዝቡ ኃጢአት በሥርየት መክደኛው ላይ ደም ይረጭ ነበር። ይህም የእግዚአብሔርን ምሕረትና ይቅርታ መገኛ ያደርገዋል።
"እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ አትሙትም ዘንድ ወደ መቅደሱ ውስጥ ከመጋረጃው ወደ ፊት በሥርየት መክደኛው ወደ ፊት በሥርየት መክደኛው ላይ ባሉት ኪሩቤል አጠገብ እገለጣለሁና ወደ መቅደሱ በማንኛውም ጊዜ አይግባ።" (ዘሌዋውያን 16÷2)
አራተኛ ሕግን ለመጠበቅና ለማስታወስ (ዘዳግም 31÷26)
ታቦቱ የእግዚአብሔርን ሕግ የሚያስቀምጥ በመሆኑ ሕዝቡ ሕጉን እንዳይረሳና በሥርዓት እንዲመራ ያደርጋል። በታቦቱ ላይ ያለው ኪሩብ ደግሞ የሕጉን ቅድስናና ታቦቱን ያለ አግባብ እንዳይቀርቡ የሚጠብቅ ነበር።
"ይህ የሕግ መጽሐፍ ከእግዚአብሔር አምላካችሁ ቃል ኪዳን ታቦት አጠገብ ይሁን፤ በዚያም በላያችሁ ምስክር ይሆን ዘንድ ይኑር።" (ዘዳግም 31÷26)
📜2ኛ. የመጀመርያው እግዚአብሔር የሠራው ታቦትና የተቀረጸበት ሕግ
በመጀመሪያ እግዚአብሔር ያዘጋጀው የመጀመሪያው ታቦት ሳይሆን የመጀመሪያዎቹ የሕግ ጽላቶች ናቸው። ታቦቱን (ማኅደሩን) የሠሩት እስራኤላውያን በሙሴ ትእዛዝ ነው።
የመጀመሪያዎቹ ጽላቶች አዘጋጅ
እግዚአብሔር ራሱ ነው
ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኘት ወደ ሲና ተራራ በወጣ ጊዜ፣ እግዚአብሔር አሠርቱን ትእዛዛት በራሱ ጣት ሁለት በድንጋይ ጽላቶች ላይ ጻፈ።
"ሙሴም ወደ ተራራው በወጣ ጊዜ፦ ከድንጋይ ሁለት ጽላቶችን እንደ ፊተኞች ቀርጸህ ወደ ተራራው ውጣ፤ እኔም በፊት በሰበርሃቸው ጽላቶች ላይ የነበረውን ቃል እጽፋለሁ።" (ዘጸአት 34÷1)
ታቦቱ (ማኅደሩ) አሠራር
ሙሴ በእግዚአብሔር ትዕዛዝ ሕዝቡን አስቀርጾ የሠራው ነው።
"ከግራር እንጨትም ታቦትን ይሥሩ፤ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል፥ ከፍታውም አንድ ክንድ ተኩል ይሁን።" (ዘጸአት 25÷10)
📜3ኛ. ሙሴና ታቦቱን የሰበረበት ምክንያትና ቀር ከመ ቀዳሚ ተብሎ ዳግም ታዞ ሙሴ ቀርጾ አቅርቦ እግዚአብሔር ሕጉን ሙሴ በቀረጸው ላይ መጻፉን
📜ሙሴ ጽላቶቹን የሰበረበት ምክንያት
ሙሴ ከእግዚአብሔር ዘንድ ከሲና ተራራ በወረደ ጊዜ፣ ሕዝቡ አምላክ ያደረገልንን አናውቅም ብለው የአሮንን ፈቃድ በመከተል ወርቃማ ጥጃ ሠርተው ሲያመልኩ አየ። በሕዝቡ ክህደትና ጣዖት አምልኮ እጅግ ተቆጥቶ በእጁ የያዛቸውን የእግዚአብሔር የሕግ ጽላቶች በዓይናቸው ፊት ሰበራቸው።
"ሙሴም ወደ ሰፈሩ በቀረበ ጊዜ ጥጃውንና ዘፈኑን አየ፤ የሙሴም ቍጣ ነደደ፥ ጽላቶቹንም ከእጁ ጥሎ በተራራውም ግርጌ ሰባበራቸው።" (ዘጸአት 32÷19)
"ቀር ከመ ቀዳሚ" ዳግም ታቦት (ጽላት) መሠራቱ
እግዚአብሔር ለሙሴ ተቆጥቶአቸው የነበረውን ሕዝብ ይቅር ብሎ ከፊተኞቹ ጽላቶች ጋር የሚመሳሰል ሌላ ሁለት ጽላቶች እንዲቀርጽ አዘዘው። ሙሴም ጽላቶቹን ከቀረጸ በኋላ ዳግም ወደ ሲና ተራራ ወጣ። እግዚአብሔርም ቃል እንደገባው በሙሴ በተቀረጹት ጽላቶች ላይ አሠርቱን ቃላት ጻፈ።
"እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ ከድንጋይ ሁለት ጽላቶችን እንደ ፊተኞች ቀርጸህ ወደ ተራራው ውጣ፤ እኔም በፊት በሰበርሃቸው ጽላቶች ላይ የነበረውን ቃል እጽፋለሁ።" (ዘጸአት 34÷1, 4, 28)
📜4ኛ. በታቦቶቹ ፊት ሊደረግ ስለሚገባው ጥንቃቄ እግዚአብሔር የሰጠው መመርያ
ታቦቱ እጅግ ቅዱስ የእግዚአብሔር መገኘት ምልክት በመሆኑ በጥንቃቄና በታላቅ ክብር ይያዝ ዘንድ እግዚአብሔር ጥብቅ መመሪያ ሰጥቷል።
📜ሀ) ታቦቱን የሚሸከሙት
መመሪያ
ታቦቱን ሊሸከሙ የሚችሉት ከሌዊ ነገድ የሆኑት ካህናት (የቀዓት ልጆች) ብቻ ናቸው። በብረት ወይም በገመድ መያዝ የለበትም። ታቦቱን የሚሸከሙት ሁልጊዜም በታቦቱ ቀለበት ውስጥ በሚገቡ መሎጊያዎች ነው
(ዘኍልቍ 4÷15, 7÷9)።
📜ለ) በዓይን ማየት ክልከላ
መመሪያ
ታቦቱ ሲነሣና ሲቆም በመጋረጃ መሸፈን አለበት። ታቦቱን ራቁቱን ያየ ሰው በሞት ይቀጣል።
"እነርሱም እንዲሞቱ ቅድስቱን ነገር ባዩ ጊዜ እንዳይሞቱ የሚሸፍኑትን ይሸፍኑ" (ዘኍልቍ 4÷20)
📜ሐ) አለመድፈር
መመሪያ
ታቦቱን ማንም መድፈር ወይም መንካት በፍጹም የተከለከለ ነው። ታቦቱን በድፍረት የነካ ወይም በቸልተኝነት የያዘ ሰው ለሞት ይዳረጋል። ለምሳሌ ታቦቱ ወደ ዳዊት ከተማ ሲመጣ ሊወድቅ ሲል እጁን ዘርግቶ የደገፈው ኦዛ ወዲያውኑ በእግዚአብሔር ተመቶ ሞተ።
"ኦዛም ታቦቱን በግዴለሽነት ስለነካ እግዚአብሔር ተቈጣበት፥ በዚያም በእግዚአብሔር ፊት ሞተ።"
(2 ሳሙኤል 6÷6-7)
📜5ኛ. ታቦታቱ በምድረ በዳ ያደረጉትን ታላቅ ተአምርና ባህረ ዮርዳኖስ መከፈሉ
እስራኤላውያን ከግብፅ ከወጡ በኋላ በምድረ በዳ በሄዱ ጊዜ ታቦቱ መንገዳቸውን ይመራ ነበር (ዘኍልቍ 10÷33)። ታቦቱ ከፊት ሲሄድ የእግዚአብሔር ኃይል በመገለጥ ጠላቶቻቸውን ይበትን ነበር። በከነዓን ምድር ከመግባታቸው በፊት ደግሞ ታላቅ ተአምር ተፈጽሟል።
ባሕረ ዮርዳኖስ መከፈሉ
እስራኤላውያን ኢያሱን ተከትለው ወደ ከነዓን ለመግባት ሲዘጋጁ ዮርዳኖስ ወንዝ በጎርፍ ሞልቶ ነበር። እግዚአብሔርም ካህናት ታቦቱን ተሸክመው የዮርዳኖስን ውኃ እንዲረግጡ አዘዛቸው። የቃል ኪዳኑ ታቦት ተሸካሚዎች እግራቸው ውኃውን እንደነካ፣ ውኃው ከላይ በኩል ቆሞ እንደ ክምር ተጠራቀመ፣ ከታች በኩል ያለውም ወደ ጨው ባሕር ወርዶ ደረቀ። በዚህም የእግዚአብሔር ሕዝብ በደረቅ መሬት ተሻገሩ።
"የቃል ኪዳኑም ታቦት ተሸካሚዎች የዮርዳኖስን ዳርቻ በደረሱ ጊዜ፥ ታቦቱንም የተሸከሙት ካህናት እግሮች በውኃው ዳር ተነከሩ፥... ዮርዳኖስም ከመዓልት ጀምሮ ይፈስ ነበርና፥ ከላይ የሚወርደውም ውኃ ቆመ፥ እጅግም ርቆ በአዳም አጠገብ ከተማ እስከምትሆን እስከ ጻርታን ድረስ እንደ ክምር ሆነ፤ ወደ ምድረ በዳ ባሕር ወደ ጨው ባሕር የሚወርደውም ውኃ ፈጽሞ ተቋረጠ፤ ሕዝቡም በኢያሪኮ አንጻር ተሻገሩ።" (ኢያሱ 3÷15-17)
📜6ኛ. ታቦቱን ይዘው ሲዞሩ የከነዓን ግንብ መፍረሱና የተደረገላቸው ድንቅ ሥራ
የኢያሪኮ ግንብ መፍረስ
እስራኤላውያን ወደ ከነዓን ከገቡ በኋላ የኢያሪኮ ከተማ ግንብ በሩ ተዘግቶ ነበር። እግዚአብሔርም ለኢያሱ ባዘዘው መሠረት፣ ሠራዊቱ ለስድስት ቀናት በቀን አንድ ጊዜ የቃል ኪዳኑን ታቦት ከፊት አስቀድመው ከተማዋን በዝምታ ዞሩ። በሰባተኛው ቀን ግን ከተማዋን ሰባት ጊዜ ዞረው ካህናቱ መለከት ሲነፉ፣ ሕዝቡም በታላቅ ድምፅ ጮኸ። በጩኸታቸውም የኢያሪኮ ግንብ በመሠረቱ ፈርሶ ወደቀ፣ ከተማይቱም ተያዘች።
"ካህናቱም መለከቱን ሲነፉ ሕዝቡም የነፋውን የመለከት ድምፅ በሰሙ ጊዜ፥ ሕዝቡ ሁሉ በታላቅ ጩኸት ጮኸ፤ ግንቡም ፈረሰ፤ ሕዝቡም ሁሉ እያንዳንዱ በፊቱ ቀጥሎ ወደ ከተማዪቱ ገባ፥ ከተማዪቱንም ያዙ።" (ኢያሱ 6÷20)
ድንቅ ሥራ
ይህ ተአምር የእግዚአብሔር ኃይል በታቦቱ ውስጥ መሆኑን በድጋሚ አስመሰከረ፣ እንዲሁም ለጦርነት ሳይሆን ለእምነትና ለትእዛዙ መታዘዝ ድል እንደሚገኝ አስተማረ።
📜7ኛ. ከኢያሱ እስከ ኤሊ ድረስ በታቦታቱ የተደረጉ ሥርዓተ አምልኮቶችና በታቦቱ የተገኘው ድል
በኢያሱ ዘመን
በከነዓን መሬት ከገቡ በኋላ ታቦቱ በሴሎ (ሺሎ) ከተማ በሚገኘው የማደሪያው ድንኳን ውስጥ ለረጅም ጊዜ ይቀመጥ ነበር። በታቦቱ ፊት የእግዚአብሔርን ሕግ የሚያነቡበት (ኢያሱ 8÷33)፣ ሕዝቡ የሚሰበሰብበት እና የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚጠይቁበት ማዕከል ሆኖ አገልግሏል።
በመሳፍንት ዘመን
ታቦቱ በሴሎ ቆይቷል፤ ሆኖም የእስራኤላውያን የኃጢአት ደረጃ በጨመረ ቁጥር የጠላቶች ጥቃት ይበረታ ነበር። ሕዝቡ በታቦቱ ፊት የኃጢአት ስርየት ሥርዓት ይፈጽሙ ነበር። ታቦቱ ከዘመቻዎች ጋር አብሮ መሄድ የጀመረው በችግር ጊዜ ነበር (መሳፍንት 20÷27-28)።
📜በኤሊ ዘመን መጀመሪያ
ታቦቱ አሁንም በሴሎ ነበር። ኤሊ ሊቀ ካህኑ ሲሆን ልጆቹ ግን ክፉዎች ነበሩና የእግዚአብሔርን መሥዋዕት ይንቁ ነበር። ሥርዓተ አምልኮው ቀጥሏል፣ ነገር ግን በካህናቱ ክህደት የተነሳ የእግዚአብሔር ክብር ከመቅደሱ መውጣት ጀምሮ ነበር (1 ሳሙኤል 2÷12-17)።
📜በታቦቱ የተገኘው ድል
ታቦቱ እንደ ዕቃ ሳይሆን የእግዚአብሔር መገኘት እንደሆነ ሕዝቡ ያምን ነበር። ድል የሚገኘው በእምነትና በታዛዥነት ሲሸከሙት ነው።
📜8ኛ. በኤሊ ዘመን ታቦተ እግዚአብሔር ተማርኮ የሔደበት ሦስት ምክንያቶች እና ተአምር ያደረገባቸው ከተሞች እና የዳጎን መቀጥቀጥ በጊደሮች ተመልሶ ወደ እስራኤል የመጣበት ድንቅ ሥራ
📜የኤሊ ልጆች ክፋት (1 ሳሙኤል 2÷12-17)
የኤሊ ልጆች አፍኒንና ፊንሐስ ክፉዎች ነበሩ፣ የእግዚአብሔርን መሥዋዕት ይንቁና በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ኃጢአት ይሠሩ ነበር። በዚህም የተነሳ የእግዚአብሔር ቅድስና ስለተደፈረ ከሕዝቡ ዘንድ ክብሩን አንስቷል።
📜የሕዝቡ ተስፋ መቁረጥና ስንፍና (1 ሳሙኤል 4÷3): እስራኤላውያን ፍልስጥኤማውያን ባጠቁአቸው ጊዜ በመታዘዝና ንስሓ በመግባት ፈንታ ታቦቱን እንደ ጠንቋይ መሣሪያ አድርገው በግድ ከሲሎ ወደ ጦር ግንባር ወሰዱት። ታቦቱ የእግዚአብሔር ዙፋን እንጂ ለአስማት የሚጠቅም ዕቃ አይደለምና በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስ አላገኙም።
የእግዚአብሔር ዕቅድ (1 ሳሙኤል 4÷11)
እግዚአብሔር በታቦቱ መማረክ በፍልስጥኤማውያን ምድር ታላቅ ተአምር በማድረግ ስሙን ሊያስጠራና የጣዖታትን ከንቱነት ሊገልጥ ፈለገ።
📜ተአምር ያደረገባቸው ከተሞች
አሽዶድ (1 ሳሙኤል 5÷1-5):
ተአምር
ፍልስጥኤማውያን ታቦቱን ይዘው ወደ አሽዶድ ከተማ አምጥተው በዳጎን የተባለው ጣዖታቸው ቤተ መቅደስ ውስጥ ከጣዖቱ አጠገብ አስቀመጡት። በነጋታውም ዳጎን በታቦቱ ፊት በግንባሩ ተደፍቶ ተገኘ። ዳግመኛም አቁመውት በነጋታው ሲመጡ ዳጎን እንደገና ተደፍቶ፣ ራሱና ሁለት እጆቹ ተቆርጠው በመድረኩ ላይ ወድቀው ተገኙ።
📜ጌት እና ኤቅሮን (1 ሳሙኤል 5÷6-12)
ተአምር
ታቦቱ ወደ ተዘዋወረባቸው ከተሞች ሁሉ በሰው ላይ ደዌ (ቡቱት) እና በምድሪቱ የአይጥ መንጋ ጣጣ መጣ። ፍልስጥኤማውያን በእግዚአብሔር እጅ ተመቱና ተፈራሩ።
📜በጊደሮች ተመልሶ የመጣበት ድንቅ ሥራ
ማብራሪያ
ፍልስጥኤማውያን ለሰባት ወራት ከተሰቃዩ በኋላ፣ ታቦቱን ለመመለስ ወሰኑ። ታቦቱንና የአምስት ከተሞቻቸውን ምሳሌ አድርገው አምስት የወርቅ ቡቱቶችና አምስት የወርቅ አይጦች የያዘ ሣጥን በአዲስ ሠረገላ ላይ አስቀመጡ። ሠረገላውንም በጭነት ልምድ የሌላቸውን ሁለት የሚያጠቡ ላሞችን (ጊደሮችን) ጠመዱበት። ጊደሮቹ ወደ ጥጃዎቻቸው መመለስ ያለባቸው ቢሆንም፣ የእግዚአብሔር ኃይል አስገድዶአቸው ወደ እስራኤል (ወደ ቤት-ሼሜሽ ከተማ) ቀጥ ብለው ሄዱ። ይህ ድንቅ ሥራ የእግዚአብሔር እጅ በጉዳዩ ውስጥ መኖሩን አስመስክሯል
(1 ሳሙኤል 6÷7-14)።
ዕጐላት እምዕጐሊሆን ከመ ኪያኪ አፍቀራ የተባለውም ለዚህ ነዎ
📜የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት (ጽዮን) በጣዖት መካከል ቢገባም፣ ጣዖት በአምላክ ፊት መቆም እንደማይችል፣ ጊደሮችም በፈቃዳቸው የእግዚአብሔርን ፈቃድ ተቀብለው ታቦቱን እንደተሸከሙት፣ የእግዚአብሔር ክብር ከአገር ወሰን በላይ ያለ እና የሕጉ ቅድስና የማይንቀሳቀስ መሆኑን ያስተምራል።
📜9ኛ. በሳኦልና በዳዊት ዘመን ለታቦቱ የተሰጠው ክብር በአንጻራዊነት በተለይ ቅዱስ ዳዊት ታቦተ እግዚአብሔር ወደ ከተማው ስትገባ ያደረገው ምስጋናና የሜልኮል መሳለቅና መካን ሆና መቅረቷ
የሳኦል ዘመን
ንጉሥ ሳኦል ለታቦቱ ተገቢውን ክብርና ትኩረት አልሰጠም። ታቦቱ በመጀመሪያው ዘመኑ በቄርያት ይዓሪም በአሚናዳብ ቤት በረሀብ ተረስቶ ለረጅም ጊዜ ቆይቷል። ሳኦል ታቦቱን የመጠየቅ ፍላጎትም ሆነ ቅንዓት አላሳየም
(1 ዜና መዋዕል 13÷3)።
የዳዊት ዘመን - ታላቁ ክብር
ንጉሥ ዳዊት ግን ታቦቱን ወደ ዋና ከተማው ወደ ኢየሩሳሌም በማምጣት ትልቁን ቦታ ለመስጠት እጅግ ቀና። በመጀመሪያው የጉዞ ሙከራ በትክክለኛ መንገድ ባለማምጣቱ (ኦዛ በመሞቱ) ተስፋ ቢቆርጥም፣ ከሶስት ወራት በኋላ ታቦቱን በታላቅ ዝግጅትና በኦሪቱ ሥርዓት መሠረት (በካህናት ተሸክሞ) አመጣ።
📜የዳዊት ምስጋና (2 ሳሙኤል 6÷14)
ታቦቱ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ ቅዱስ ዳዊት ከሰዎች ሁሉ ቀድሞ በታላቅ ደስታና ቅንዓት በእግዚአብሔር ፊት በሙሉ ኃይሉ ዘለለና ። ከቄጠማ የተሠራ ኤፉድ ለብሶ በታላቅ ዝማሬና መለከት ከሕዝቡ ጋር አምላኩን አመሰገነ።
የሜልኮል መሳለቅና መካን መሆን
(2 ሳሙኤል 6÷16, 20-23):
መሳለቅ
የሳኦል ልጅ ሚስቱ ሜልኮል ንጉሡ ዳዊት በእግዚአብሔር ፊት ሲዘል በመስኮት በኩል አየችው። ለንግሥና ክብር እንደማይገባውና ለባሪያዎቹ ሴቶች ገልጦ እንደዋለ በመቁጠር በልቧ ንቃው ከዚህም አልፎ በአፍዋ ተናገረችው።
ቅጣት
ዳዊትም የሰጠውን መልስ እግዚአብሔር በሳኦል ፋንታ መርጦት እርሱን እያገለገለ መሆኑን ገልጾ ተሟገተ። በዚህ የክብር መናቅ የተነሳ ሜልኮል እስከ ሞተችበት ቀን ድረስ ልጅ አልወለደችም (መካን ሆና ቀረች)።
ለእግዚአብሔር ቅንዓትና ፍቅር የሚገለጽበትን መንገድ የሚንቅ ሁሉ ቅጣትን እንደሚያገኝ ያስተምራል።
📜10ኛ. ዳዊት ለእግዚአብሔር ቤት ቀንቶ ቤተመቅደስ ሊሠራ ቢያስብም የተፈቀደው ለሰሎሞን ነው ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን አንጾ በምስጋና ታቦተ ሕጉን ወደ ተሠራ ቤተ መቅደስ አስገባ
📜የዳዊት ቅንዓትና ፈቃድ (2 ሳሙኤል 7÷1-3)
ንጉሥ ዳዊት በዝግባ ቤተ መንግሥት ውስጥ ሲቀመጥ፣ የእግዚአብሔር ታቦት ግን በድንኳን ውስጥ መኖሩ አስጨነቀው። ስለሆነም ለእግዚአብሔር ታላቅ ቤተ መቅደስ ለመሥራት አሰበና ለነቢዩ ናታን ነገረው።
📜ትእዛዙ ለሰሎሞን መሰጠቱ (2 ሳሙኤል 7÷12-13) እግዚአብሔር ግን በናታን አማካኝነት ዳዊት ብዙ ጦርነት የገጠመ በመሆኑ የቤተ መቅደሱን ሥራ ለልጁ ለሰሎሞን እንደሰጠው ነገረው። ሰሎሞን የሰላም ሰው ስለሚሆን እርሱ ቤተ መቅደሱን ይሠራለታል ተብሎ ተነገረ።
📜ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን መሥራቱና ታቦቱን ማስገባት
(1 ነገሥት 8:1-9)
ግንባታ
ሰሎሞን አባቱ ዳዊት ያዘጋጀውን ዕቅድና ንዋየ ቅድሳት ተጠቅሞ ለሰባት ዓመታት ያህል የሚፈጅ ታላቅ ቤተ መቅደስ በኢየሩሳሌም ሠራ።
ታቦቱን ማስገባት
ቤተ መቅደሱ ሲጠናቀቅ ሰሎሞንና የእስራኤል ሽማግሌዎች ሁሉ ታቦቱን ከዳዊት ከተማ (ጽዮን) ወደ ተሠራለት አዲስ ቤተ መቅደስ (ቅድስተ ቅዱሳን) በታላቅ በዓልና ምስጋና አስገቡት። በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር ክብር (ደመና) ቤተ መቅደሱን ሞላው።
"ካህናቱም የቃል ኪዳኑን ታቦት ወደ ስፍራው፥ ወደ ቤተ መቅደሱ ውስጥ ወዳለው ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ፥ ወደ ኪሩቤልም ክንፍ አመጡ።... ታቦቱም ከቅድስተ ቅዱሳኑ ወጣ፥ ደመናም የእግዚአብሔርን ቤት ሞላው።"
(1 ነገሥት 8÷6, 10)
📜 የታቦተ ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት (የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት)
📜11ኛ. የንግሥተ ሳባ ወደ ንጉሥ ሰሎሞን መሔድና ቀዳማዊ ምንሊክን ጸንሳ መምጣቷ
የንግሥተ ሳባ ጉዞ (1 ነገሥት 10÷1-13):
የኢትዮጵያ ንግሥት የነበረችው ማክዳ (ንግሥተ ሳባ) የንጉሥ ሰሎሞንን ጥበብና ክብር ወሬ ሰማች። ወደ ኢየሩሳሌምም ሔዳ አስቸጋሪ በሆኑ ጥያቄዎች ፈተነችው። ሰሎሞንም ለሁሉም ጥያቄዎቿ መልስ በመስጠት በታላቅ ጥበብ አስደነቃት።
ቃል ኪዳንና ምንሊክ
1ኛበኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እምነትና በክብረ ነገሥት መሠረት፣ ንግሥቲቱ ከሰሎሞን ዘንድ ተመልሳ ስትመጣ ቀዳማዊ ምኒልክን ጸንሳ መጥታ በኢትዮጵያ ወለደች።
"የሳባም ንግሥት የሰሎሞንን ዝና በሰማች ጊዜ በእንቆቅልሽ ትፈትነው ዘንድ እጅግም ብዙ ጓዝ፥ ግመሎችም ሽቱና እጅግም ብዙ ወርቅ የከበረም ዕንቍ የጫኑ፥ አስጭና ወደ ኢየሩሳሌም መጣች። ወደ ሰሎሞንም በመጣች ጊዜ በልብዋ ያለውን ሁሉ ተናገረችው።" (1 ነገሥት 10÷1-2)
📜12ኛ. ታቦተ እግዚአብሔር ወደ ኢትዮጵያ የመጣበት እውነተኛ የሆነ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሚታመነው ታሪክና ማሥረጃ
የታሪክ ምንጭ
ታሪኩ በዋነኝነት የሚገኘው በኢትዮጵያ ብሔራዊ እና ሃይማኖታዊ መጽሐፍ በሆነው "ክብረ ነገሥት" ውስጥ ነው።
ታሪኩ
ጉዞ ወደ ኢየሩሳሌም
ቀዳማዊ ምኒልክ ካደገ በኋላ የአባቱን ጥበብ ለማየት ወደ ኢየሩሳሌም ተጓዘ። ሰሎሞንም በክብር ተቀብሎት ለተወሰነ ጊዜ አቆየው።
📜የታቦቱ መምጣት
ምኒልክ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለስ፣ ሰሎሞን በእስራኤል ነገዶች በኵር ልጆች መካከል ታቦቱን ተሸክመው የሚሄዱ ካህናት እንዲያጅቡት አዘዘ።
ሊቀ ካህናቱ አዛርያስ
ከእነዚህም ካህናት መካከል የሊቀ ካህናት ሳዶቅ ልጅ አዛርያስ ይገኝበታል። አዛርያስ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በማስተዋል በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ የቃል ኪዳኑን ታቦት (ታቦተ ጽዮንን) ከመቅደሱ ወስዶ በሌላ ተመሳሳይ ታቦት ለወጠ።
📜አምላካዊ ፈቃድ
ምኒልክና አዛርያስ ታቦቱን ይዘው ከኢየሩሳሌም ሲወጡ ታቦቱ ራሱ በደመናና በምስጋና አጅቦአቸዋል፤ ይህም የእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑን ያመለክታል። ምኒልክ ታቦቱን ይዞ ወደ ኢትዮጵያ በመጣ ጊዜ የብሉይ ኪዳን ሥርዓት በኢትዮጵያ ተመሠረተ።
መረጃ
ክብረ ነገሥት
ታሪኩ በሰፊው የተዘገበበት ዋናው መጽሐፍ ነው።
ቤተ ክርስቲያን እምነት
ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታቦተ ጽዮን በአክሱም ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን ትገኛለች ብለን በፅኑ እናምናለን።
📜13ኛ. ታቦተ እግዚአብሔር ወደ ኢትዮጵያ አኲሱም ከመጣች በኋላ ያጋጠማት ስደት
የመጀመሪያው ማረፊያ
ታቦተ ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ ከገባች በኋላ የኢትዮጵያ የብሉይ ኪዳን ማዕከል ወደሆነችው ወደ አክሱም ተወስዳ ተቀምጣለች።
ዋናው ስደት - በዮ-ዲ-ት ጉ-ዲ-ት ዘመን:
ማብራሪያ
በ9ኛውና በ10ኛው ክፍለ ዘመን አካባቢ የነገሠችው ዮ-ዲ-ት ጉ-ዲ-ት ክርስትናን ለማጥፋት ታላቅ ጥፋት አደረገች። ብዙ አብያተ ክርስቲያናትን አቃጠለች።
ስደቱ
በዚህ ስደት ጊዜ ታቦተ ጽዮን ከተማዋን ለቃ ከነካህናቶቿ ተወስዳ በደቡብ ኢትዮጵያ ባለው ዝዋይ ሐይቅ ደሴቶች ውስጥ ለ40 ዓመታት ያህል ተደብቃና ተጠብቃ ቆይታለች። በኋላም የሰላም ዘመን ሲመጣ ወደ አክሱም ተመልሳ ገብታለች።
📜14ኛ. ታቦተ ጽዮን በአኲሱም ጽዮን እንድትቀመጥ የአምላክ ፈቃድ ስለመሆኑ የሚያሳዩ ሦስት መሠረታዊ ነገሮችን
የትንቢት ፍፃሜ (መዝሙር 68÷31):
ማብራሪያ
"ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች" የሚለው የነቢዩ ዳዊት ትንቢት ፍፃሜ እንደሆነ ይታመናል። ታቦቱ ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱ ኢትዮጵያ የእግዚአብሔርን ኪዳን ለመቀበልና ለመጠበቅ የመመረጧ ምልክት ነው።
ታቦቱ የገለጠው ተአምራዊ ፈቃድ:
ማብራሪያ
ቀዳማዊ ምኒልክና አዛርያስ ታቦቱን ይዘው ከኢየሩሳሌም ሲወጡ በእግዚአብሔር ደመና ተሸፍነው መምጣታቸው፣ እንዲሁም ታቦቱ በተአምር መፍጠኑ የእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑን ያረጋግጣል። የሰው እጅ ጣልቃ ገብነት ሳይሆን መለኮታዊ ምርጫ ነው።
የጥበቃ ታሪክ
ማብራሪያ
ታቦቱ በኢትዮጵያ በቆየበት ዘመን ሁሉ፣ ከታላላቅ ስደቶች (እንደ ዮ. ዲ. ት ጉ. ዲ. ት) ተጠብቆና ሳይጠፋ በአክሱም መኖሩ፣ የእግዚአብሔር ዘለዓለማዊ ፈቃድ በዚያ እንዲያርፍ መሆኑን የሚያሳይ ነው።
📜15ኛ. ከበዓሉ የምንማራቸው ነገሮች ምንድናቸው
ከበዓለ ጽዮን እኛ የምንማራቸው ነገሮች በየድርሻው እንደ ቀደሙት አባቶችና ትውልዶች ድርጊት መሠረት ተዘርዝረዋል።
📜ከእስራኤላውያን የምንማራቸው አምስት ነገሮች
የእግዚአብሔርን ክብር መጠበቅ
ለእግዚአብሔር ታቦት (ዛሬ ለቤተ ክርስቲያን) ክብር ሲሰጡ ድልና በረከት እንደሚያገኙ (ባሕረ ዮርዳኖስ መከፈት፣ ኢያሪኮ መፍረስ)።
ትእዛዝን መታዘዝ
በኢያሪኮ ጦርነት ትዕዛዙን ፈጽመው ድልን እንዳገኙ ሁሉ፣ እኛም የእግዚአብሔርን ሕግጋት በፍጹም መታዘዝ እንጂ በግል ጥበብ መመራት እንደሌለብን።
📜ንዋየ ቅድሳትን አለመድፈር
ታቦቱን እንደ ተራ ዕቃ መውሰድ እንደሌለብን (በኤሊ ዘመን ወደ ጦር ግንባር ወስደው መሸነፋቸው)።
📜ከጣዖት መራቅ
ታቦቱ ዳጎንን እንደሰባበረው ሁሉ፣ በልባችንና በሕይወታችን ውስጥ ያለውን የትኛውንም ጣዖት (ገንዘብ፣ ዝና፣ ስንፍና) የእግዚአብሔር ቃል እንዲሰብር።
📜የኃጢአት ቅጣትና ንስሓ
በኃጢአት ምክንያት ታቦቱ እንደተወሰደው ሁሉ፣ ንስሓ ሳንገባ በኃጢአት ስንኖር ከእግዚአብሔር ጸጋ እንደምንርቅ።
📜ከኤሊ የምንማረው
ትጋትና ኃላፊነት
ኤሊ ቤተ ክርስቲያንን በማገልገል ላይ የተሾመ ቢሆንም፣ ልጆቹን በመገሠጽና በማስተማር ረገድ ኃላፊነቱን ባለመወጣቱ ታላቅ የእግዚአብሔርን ቁጣ እንዳመጣ ሁሉ፣ እኛም በቤተሰብም ሆነ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ውስጥ ያሉትን ኃላፊነቶቻችንን በጽኑ መወጣት አለብን።
"ልጆቹም በራሳቸው ላይ መርገምን እንዳመጡ ያውቅ ነበርና፥ እምቢ አላላቸውም ነበር።" (1 ሳሙኤል 3÷13)
📜ከደቂቀ ኤሊ (ሆፍኒና ፊንሐስ) የምንማረው
ሥልጣንን ያለ አግባብ አለመጠቀም
የካህናት ልጆች ሲሆኑ ሥልጣናቸውን ተጠቅመው መሥዋዕቱንና ሕዝቡን እንደናቁ ሁሉ፣ እኛም አገልግሎታችንን ለግል ጥቅም ወይም ለኃጢአት መሸፈኛ አለመጠቀም እንዳለብን።
📜የቅድስና ዋጋ
ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ቅድስት ስፍራ መሆኗን ማወቅና በቅድስና መኖር እንደሚጠበቅብን።
ከነቢዩ ሳሙኤል የምንማረው
ከሕፃንነት ለእግዚአብሔር መገዛት
ሳሙኤል ከሕፃንነቱ ጀምሮ ለእግዚአብሔር ቃል ጆሮ በመስጠትና በታማኝነት በማገልገል የተመረጠ የእግዚአብሔር አገልጋይ እንደሆነ ሁሉ፣ ወጣቶችም ከልጅነታቸው ጀምሮ ለእግዚአብሔር ቃል ቅድሚያ በመስጠትና በታማኝነት በመገዛት መኖር እንዳለባቸው።
የቃልና የሥራ አንድነት
እውነተኛ መሪነት በሥራ መገለጽ እንዳለበት።
ከቀደሙ አባቶች ታቦትንና ሕግጋተ እግዚአብሔርን ጠብቆ መያዝ
ታቦቱና ሕጉን የጠበቁ አባቶች (እንደ ሙሴ፣ ኢያሱ፣ ዳዊት) ታላቅ በረከትና ክብር እንዳገኙ ሁሉ፣ እኛም የዘመናችንን ክብር ሕጉንና ቤተ ክርስቲያንን መጠበቅ እንዳለብን።
በየድርሻው የሚጠበቅበትኖ ያድርግ
📜 የታቦተ ጽዮን አመጣጥ፣ የብሉይ እና ሐዲስ ኪዳን ትስስር
የታቦተ ጽዮን አመጣጥና ታሪክ (የብሉይ ኪዳን ክፍል)
የእግዚአብሔር ታቦት ከእግዚአብሔር ለሰው የተሰጠበት አራት ምክንያቶች
📜የእግዚአብሔር መገኘት ምልክትና ማደሪያ
እግዚአብሔር ከኪሩቤል መካከል ሆኖ ሕዝቡን ለመናገር የተሰጠ (ዘጸአት 25÷22)።
📜የቃል ኪዳኑ ምስክር
አሠርቱ ትእዛዛት የተቀመጡበትና የእግዚአብሔርና የሕዝቡ የቃል ኪዳን መገለጫ (ዘጸአት 25÷16)።
📜የኃጢአት ሥርየት ማዕከል
የሥርየት መክደኛ በመኖሩ፣ ሊቀ ካህኑ ለሕዝቡ ኃጢአት ደም የሚረጭበት ሥፍራ (ዘሌዋውያን 16÷2)።
📜ሕግን ለመጠበቅና ለማስታወስ
የእግዚአብሔር ሕግ እንዳይረሳ በታቦቱ አጠገብ ይቀመጥ ነበር (ዘዳግም 31÷26)።
📜 የመጀመርያ ጽላት፣ መሰበርና ዳግም መጻፍ፣ ጥንቃቄ
የመጀመሪያዎቹ ጽላቶች አዘጋጅ
እግዚአብሔር ራሱ ሲሆን፣ ሙሴ በሰበራቸው ጊዜ
(ዘጸአት 32÷19)፣ በሙሴ በተቀረጹት ሁለተኛ ጽላቶች ላይ እግዚአብሔር አሠርቱን ቃላት ዳግም ጻፈ
(ዘጸአት 34:1)።
📜ጥንቃቄ
ታቦቱ በዓይን ማየት ክልክል ነበር (ዘኍልቍ 4÷20)። ሊሸከሙት የሚችሉት ካህናት ብቻ ነበሩ። በቸልተኝነት የነካው ኦዛ በእግዚአብሔር ተመቶ ሞተ
(2 ሳሙኤል 6÷6-7)።
. በታቦቱ የተደረጉ ተአምራት
ባሕረ ዮርዳኖስ
ካህናቱ ታቦቱን ይዘው ወንዙን እንደረገጡ ውኃው እንደ ክምር ቆሞ ሕዝቡ በደረቅ ተሻገረ
(ኢያሱ 3÷15-17)።
የኢያሪኮ ግንብ
ታቦቱ በሰባተኛው ቀን ከተማዋን ሰባት ጊዜ ከዞረ በኋላ በሕዝቡ ጩኸትና በመለከት ድምፅ ግንቡ ፈረሰ
(ኢያሱ 6÷20)።
ከኢያሱ እስከ ኤሊና ምርኮ
በሴሎ
ከኢያሱ ጀምሮ ታቦቱ በሴሎ ተቀምጦ የሥርዓተ አምልኮ ማዕከል ነበር።
የታቦቱ ምርኮ ምክንያቶች
የኤሊ ልጆች (አፍኒና ፊንሐስ) ክፋትና ኃጢአት
(1 ሳሙኤል 2÷12-17)።
እስራኤል ታቦቱን እንደ አስማት ዕቃ ወደ ጦር ግንባር ወስደው መታመናቸው (1 ሳሙኤል 4÷3)።
በምርኮ የተደረጉ ተአምራት
በፍልስጥኤማውያን ከተሞች አሽዶድ፣ ጌት እና ኤቅሮን ታላቅ መቅሠፍት (ቡቱት) መጣ። የጣዖታቸውም ዳጎን ራሱና እጆቹ ተቆርጠው በታቦቱ ፊት ተደፉ
(1 ሳሙኤል 5÷4)። ታቦቱም በጊደሮች ተመልሶ ወደ እስራኤል መጣ (1 ሳሙኤል 6÷12)።
ዳዊትና ሰሎሞን
የዳዊት ቅንዓት
ንጉሥ ዳዊት በታላቅ ምስጋና እየዘለለ ታቦቱን ወደ ኢየሩሳሌም አመጣ (2 ሳሙኤል 6÷14)።
የሜልኮል መናቅ
ባለቤቱ ሜልኮል ንጉሡ ሲዘል በመናቋ መካን ሆና ቀረች (2 ሳሙኤል 6÷23)።
ቤተ መቅደስ
ዳዊት ቤተ መቅደስ ሊሠራ ቢፈልግም የተፈቀደው ለልጁ ለሰሎሞን ነበር። ሰሎሞንም ታቦተ ሕጉን ወደ ሠራው ቤተ መቅደስ በክብር አስገባ (1 ነገሥት 8÷6-11)።
የታቦተ ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት
ንግሥተ ሳባና ሰሎሞን
የኢትዮጵያ ንግሥት ማክዳ (ንግሥተ ሳባ) የሰሎሞንን ጥበብ አይታ ቀዳማዊ ምኒልክን ጸንሳ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰች (1 ነገሥት 10÷1-13)።
የታቦቱ መምጣት
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና በክብረ ነገሥት መሠረት፣ ቀዳማዊ ምኒልክ ወደ አባቱ ሄዶ ሲመለስ፣ የሊቀ ካህናቱ ልጅ አዛርያስ ታቦተ ጽዮንን ከሰሎሞን ቤተ መቅደስ በድብቅ በመውሰድ በሌላ ለወጠ። ታቦቱንም በደመናና በምስጋና አጅበው ወደ አክሱም አመጡት። ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነበር።
ስደት
ታቦተ ጽዮን በአክሱም ከተቀመጠች በኋላ በ10ኛው ክፍለ ዘመን በዮ.ዲ.ት ጉ.ዲ-ት ስደት ጊዜ ወደ ዝዋይ ሐይቅ ደሴቶች ተወስዳ ለ40 ዓመታት ተጠብቃለች።
በ16ኛ ክፍለ ዘመን በ-ግ*ራ*ኝ ወረራ ጊዜ በቤተ ክርስቲያን ላይ በነበረው ስደት ታቦተ ጽዮንም በካህናቱ አማካኝነት ወደሌላ ቦታ ተሰዳ ነበረ
የዳዊት ትንቢት ፍፃሜ
"ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች" (መዝሙር 68÷31)።
ታቦቱ ራሱ በደመና ተሸፍኖና በተአምር መፍጠኑ መለኮታዊ ምርጫ መሆኑን ማሳየቱ።
🕊️ የታቦቱ ምሳሌ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ታቦቱ የኢየሱስ ክርስቶስን ቃል ኪዳን እንደያዘ እመቤታችንም ሕያው ቃል የሆነውን ክርስቶስን በማኅፀኗ ስለተሸከመች ታላቅ ምሳሌ ናት።
ማደሪያነት
ታቦቱ የእግዚአብሔር ማደሪያ እንደነበረ ሁሉ፣ እመቤታችንም የልዑል ኃይል በላያዋ መጥቶ ክርስቶስን ስለፀነሰች ከታቦቱ የላቀች ማደሪያ ናት (ሉቃስ 1÷35)።
ምስጋና
ታቦቱ ወደ ዳዊት ከተማ ሲገባ ዳዊት እንደዘለለ፣ እመቤታችን ወደ ዘመዷ ኤልሳቤጥ ስትሄድ ዮሐንስ በማኅፀን ዘሏል (ሉቃስ 1÷41-43)።
ሐዲስ ኪዳን ታቦት ለምን አስፈለገ? (መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት)
የቃል ኪዳን ምስክርነት
ታቦቱ በብሉይ ኪዳንና በሐዲስ ኪዳን መካከል ያለውን መንፈሳዊ ትስስር ያረጋግጣል።
የሥርዓተ አምልኮ ማዕከልነት
በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ታቦቱ በመቅደስ ውስጥ ተቀምጦ የሥርዓተ ቅዳሴ ማዕከላዊ ክፍል ነው።
የሥጋውና የደሙ ማክበርያ ነው ሐዋርያው ዮሐንስ በራእይ የኪዳኑ ታቦት በሰማይ መታየቱን ጽፏል (ራእይ 11÷19)። ይህ የሚያሳየው ታቦቱ በዘለዓለም ቃል ኪዳን ውስጥ የራሱ ቦታ እንዳለው ነው።
📜 ከበዓለ ጽዮን የምንማራቸው ፍሬ ነገሮች
ከታቦተ ጽዮን አመጣጥ፣ ታሪክና ሥርዓተ አምልኮ የምንማራቸው ትምህርቶች እንደየኑሯችንና ኃላፊነታችን የሚከተሉት ናቸው።
📜አባቶች፡- ኃላፊነትና የቤተሰብ መምራት
ትምህርቱ አባትነት (መሪነት) ሥልጣን ብቻ ሳይሆን ከባድ ኃላፊነት ነው። ኤሊ ልጆቹን ባለመገሠጹ የተቀጣውን ታሪክ መማር፣ አባቶች ልጆቻቸውን በሥርዓትና በእግዚአብሔር መንገድ የመምራትና የመገሠጽ ግዴታ እንዳለባቸው ያስረዳል።
"ልጆቹም በራሳቸው ላይ መርገምን እንዳመጡ ያውቅ ነበርና፥ እምቢ አላላቸውም ነበር።" (1 ሳሙኤል 3÷13)
📜 ካህናት፡- የቅድስናና የአገልግሎት ጥንቃቄ
ትምህርቱ
ታቦቱን የመሸከም ኃላፊነት የተሰጣቸው ካህናት በሙሉ ንጽህናና ጥንቃቄ ማገልገል እንዳለባቸው ሁሉ፣ የሐዲስ ኪዳን ካህናትም የቤተ ክርስቲያንን ቅዱስ ምሥጢራት፣ ሥርዓተ አምልኮና ንዋየ ቅድሳትን በታላቅ ቅድስናና ፍርሃት ሊጠብቁ ይገባል። የአገልግሎት ቦታን ለኃጢአት አለመጠቀም።
"እርሱና ልጆቹም ቅድስቲቱን ነገር አይሸፍኑ ዘንድ፥ እንዳይሞቱ የሚሸፍኑትን ይሸፍኑ።" (ዘኍልቍ 4÷20)
📜 ባለትዳሮች፡- የእግዚአብሔርን ክብር መረዳትና ያለመናቅ
ንጉሥ ዳዊት ለእግዚአብሔር ባለው ቅንዓት በዘለለ ጊዜ ሚስቱ ሜልኮል ንቃው መካን ሆነች። ባለትዳሮች የእግዚአብሔርን አገልግሎት እና የአጋርን የእምነት ሕይወት ማክበርን መማር አለባቸው። በጋራ ለእግዚአብሔር ቤት መቅናትና መደጋገፍ አስፈላጊ ነው።
"እግዚአብሔርን እያመለክሁ ከባሮቼ ሴቶች ፊት ከዚህም ይልቅ እዋረዳለሁ፥ በራስህም ዘንድ እንከበራለሁ።"
(2 ሳሙኤል 6÷21-23)
📜ወጣቶች፡- ለእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታማኝ መሆን
ሳሙኤል ከሕፃንነቱ ጀምሮ ለእግዚአብሔር ቃል ጆሮ ሰጥቶ እንዳገለገለ፣ ወጣቶችም ከትንሽነታቸው ጀምሮ ለእግዚአብሔር ቃል ቅድሚያ በመስጠት የሕይወት ጉዟቸውን መጀመር አለባቸው። ታማኝ ለሆኑት ለሙሴና ለኢያሱ ታቦቱ በረከት እንደሆነ ሁሉ፣ ሕጉን መጠበቅ ለበረከት ቁልፍ ነው።
"ይህ የሕግ መጽሐፍ ከእግዚአብሔር አምላካችሁ ቃል ኪዳን ታቦት አጠገብ ይሁን፤ በዚያም በላያችሁ ምስክር ይሆን ዘንድ ይኑር።" (ዘዳግም 31÷26)
📜አጠቃላይ ምዕመናን፡- በእምነትና በታዛዥነት መመራት
ድል የሚገኘው በሰው ኃይልና ጥበብ ሳይሆን በእምነትና በታዛዥነት መሆኑን መማር። ታቦቱ ዮርዳኖስን ከፍሏል፣ ግንብ አፍርሷል። ሆኖም የእስራኤል ሕዝብ ታቦቱን እንደ ጠንቋይ ዕቃ ወደ ጦር ግንባር ሲወስደው ግን ተማርኳል። ይህ የሚያስተምረው ቤተ ክርስቲያንና ንዋየ ቅድሳትን በቅን ልቦናና በትሕትና ማክበር እንጂ በድፍረት መቅረብ እንደሌለብን ነው።
"የቃል ኪዳኑም ታቦት ተሸካሚዎች እግራቸው በውኃው ዳር ተነከሩ፥... ውኃውም ቆመ።" (ኢያሱ 3÷15-16)
የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ከእመቤታችን በረከት ለረድኤት ያሳትፈን
“ለግሪክ ሰዎችና ላልተማሩም፥ ለጥበበኞችና ለማያስተውሉም ዕዳ አለብኝ፤”
— ሮሜ 1፥14
ጸልዩ በእንተ ሰላም
ስለ ሰላም እንጸልይ
ስለ ሀገራችን እንጸልይ
ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንጸልይ
በጭንቅ በመከራ ስላሉት እንጸልይ
በረሀብ በስደት ስላሉት እንጸልይ
በጽኑ ሕመም ተይዘው ስለሚሰቃዩት እንጸልይ
ስለ ሃይማኖት መሪዎች አባቶቻችን እንጸልይ
ስለ ሀገር መሪዎች እንጸልይ
የሰላም የምህረት የቸርነት ባለቤት እግዚአብሔር ሰላሙን ምህረቱን ቸርነቱን አይንሳን
አባ አትናቴዎስ ወልደ ጎርጎርዮስ
ዘዝዋይ ገዳም
✍️ ህዳር 18/3/2018 ✍️
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
/// ደራሽ ያጣች ህይወት 😭😭 ///
ከሽህ ስጋ ዘመድ ለችግር ከማይደርስ፣
አንድ ወዳጅ በቂ ነው ሲርበኝ የሚያጎርስ።
ዘመድማ ሞልቷል ዘሩ መች ቸገረኝ፣
ለችግር ደራሽ ነው አብዝቶ የራበኝ!
ስሞት ከሚንጋጋ ከእልፍ አላፍ ቀባሪ፣
አንድ ወዳጅ ውድ ነው ሲኖሩ አኗኗሪ።
/// ስንታየሁ ሀብታሙ ///
01/11/2025
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Addis Ababa