Ethio-prosperity
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethio-prosperity, Health/Beauty, Addis Ababa.
06/05/2024
"እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ"!!!!!!
አቶ ዘይኑ ኸሊል
የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ዋና ስራ አስፈፃሚ
#የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አስተዳደር ለመላው ክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ይላል !!
የወረዳው አስተዳደር የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሠላም አደረሳችሁ በማለት በዓሉን ስናከብር የሌላቸውን በመርዳት ፣ የወደቁትን በማንሣት እርስ በእርስ በመረዳዳት ማክበር እንዳለበት መልእክት አስተላልፈው። በመጨረሻም በ ሰላም፤በፍቅር፤በአንድነት ሆነን በያለንበት በደስታ እናሳልፍ ሲሉም በአጠቃላይ ለእምነቱ ተከታዮች ሁሉ መልካምን ተመኝተዋል።
በአጠቃላይ ለወረዳው ነዋሪ፤ለአመራሮች፤ሴክተር ሰራተኞችና ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ በድጋሚ መልካም የትንሳኤ በዓል ይሁንላችሁ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ሚያዚያ 26/2016 ዓ.ም
12/03/2024
የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አስተዳደር ለመላው የኦርቶዶክስና የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለአብይና ለረመዳን ፆም በሰላም አደረሳችሁ።
መጋቢት 01/16 ዓ.ም
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዘይኑ ኻሊል ይህ ታላቅና የተባረከ ወር በልዩ ሁኔታ ከፈጣሪያችን ጋር የምንገናኝበት እና በዱአ እና በፀሎት ለሀገርና ለህዝባችን ሰላም፣ እድገት፣ መረጋጋትና የተሻለ ነገር የምንመኝበት ወቅት ነው ብለዋል።
ፆም የመልካምነት ፣ የንስሃ ፣ የይቅርታ ፣ የተቸገሩትን የመርዳት እና የሌሎች ብዙ ፀጋዎች ወር ነው ያሉት ኃላፊው በዚህ የፆም ወቅት የተቸገሩ ወገኖችን ማስታወስና ከጎናቸው መቆምን መዘንጋት እንደማይገባም አመላክተዋል።
ህዝበ ሙስሊሙና ክርስቲያኑ ይህን የተከበረ እና የተባረከ ወር በፆም እና በዱአ ሲያሳልፍ በድርቅ የተጎዱ ወገኖችን በማስታወስ መደገፍና በዱእና በፀሎት ማሰብ አለበት ነው ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
አቶ ዘይኑ ኻሊል
የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አስተዳደር
ዋና ስራ አስፈፃሚ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa