Zemen bank

Zemen bank

Share

bank of zemen

10/08/2025
Photos from Zemen bank's post 08/05/2024

የንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆኑ

| በቅርቡ ዋና ሥራ አስፈጻሚውን ያሰናበተው ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩትን እመቤት መለሰ ዘለቀ (ዶ/ር)ን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አድርጎ ሰየመ፡፡

ከንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመላክተው እመቤት (ዶ/ር) የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው እንዲያገለግሉ ለብሔራዊ ባንክ የቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶ ሹመቱ ፀድቆላቸዋል፡፡

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በሥራ አስፈጻሚነት የሚመራ የባንክ ባለሙያ ሲያፈላልግ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን፣ ካወዳደራቸው ሦስት የባንክ ባለሙያዎች መካከል እመቤት (ዶ/ር)ን ሊመርጥ ችሏል፡፡

አዲሷ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እመቤት (ዶ/ር) በባንክ ኢንዱስትሪ ውሰጥ ከ22 ዓመታት በላይ ልምድ ያላቸው ሲሆን የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው እስከ ተሰየሙበት ድረስ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እስትራቴጂክ ፕላኒንግ እና ትራንስፎርሜሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ሲያገለግሉ እንደ ነበር ታውቋል፡፡

#ሪፖርተር

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Address


Ethiopia
Addis Ababa
ZEM