Dr. Mekdes Daba
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Dr. Mekdes Daba, Health/Beauty, Finfine, Addis Ababa.
የጤና ሚኒስቴር ለፌደራል ተጠሪ ተቋማትና ለክልል ጤና ቢሮዎች የተሸከርካሪና ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች ድጋፍ አደረገ
_____________
ከጤና ኬላ ጀምሮ እስከ ከፍተኛ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ ድረስ ያለውን የጤና አገልግሎት ለማሳለጥና አገልግሎቶቹን ለማቀላጠፍ ይረዳ ዘንድ የተሸከርካሪና የላፕቶፕ ኮምፒውተሮች ድጋፍ ለክልል ጤና ቢሮዎች፣ ለፌደራል ሆስፒታሊችና ተጠሪ ተቋማት ተደረገ፡፡
በድጋፍ ርክክቡ ወቅት ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ እንዳሉት በጤናው ዘርፍ የተያዘውንና በትኩረት እየተሰራበት የሚገኘውን የመካከለኛ ዘመን ኢንቨስትመንት ዕቅድን ከግብ ለማድረስ የክልል ጤና ቢሮዎች፣ የፌደራል ተጠሪ ተቋማት እና ሆስፒታሎች ያላቸው ድርሻ ጉልህ ነው ያሉ ሲሆን በተለይ የማህበረሰቡን የጤና ፍላጎት ለማርካትና ጥራት እና ፍትኃዊነት ያለው የጤና አገልግሎት ለመስጠት የሚደረጉ ድጋፎች የሚኖራቸው ሚና ቀላል የሚባል አይደለም ብለዋል፡፡
በርክክቡ ወቅትም በዓለም ባንክ ድጋፍ አንድ መቶ ስልሳ (160) የሚሆኑ ተሸከርካሪዎችን መገዛታቸውንና በአሁኑ ወቅት የደረሱትን ስልሳ (60) ተሸከርካሪዎች በተለያዩ ምክንያቶች ጉዳት ለደረሰባቸው ክልሎች ቅድሚያ በመስጠት እንዲሁም የፌዴሬሽን ምክር ቤት ቀመር መሰረት በማድረግ አበርክተናል ያሉት ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ የክልል ጤና ቢሮዎች እና የፌደራል ተጠሪ ተቋማት የተደረገላቸውን ድጋፍ ለጤና ስራ ብቻ እንዲያውሉት አደራ ብለዋል፡፡
የጤናውን ዘርፍ ከማዘመን ጋር ተያይዞ በዓለም ባንክ ድጋፍ ሰማንያ (80) የዲጂታል ጤና ባለሙያዎችን በመቅጠርና በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል በመሰማራት በርካታ ስራዎች እየተሰራ ነው ያሉት በጤና ሚኒስቴር የፋይናንስ ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ሰለሞን እጅጉ ሲሆኑ ከዚህ ጋር ተያይዞ ከሁለት መቶ ሃምሳ አምስት (255) በላይ የላፕቶፕ ኮምፒውተሮች መገዛታቸው እና የርክክቡ አንድ አካል እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ አቶ ሰለሞን አክለው እንደገለጹት የሚደረጉ ማናቸውም ድጋፎች በምንም መልኩ ከጤና ስራ ውጪ መዋል የሌለባቸው መሆኑን ገልጸው ይህ ሳይሆን ቢቀር ለወደፊቱ ሊያስከትል የሚችለው ተጽዕኖ ከፍተኛ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
የክልል ላብራቶሪዎችን የስራ ጫና ከመቀነስና የተገልጋይን እርካታን ከመጨመር ረገድ ትልቅ አበርክቶ የሚኖራቸውን ከአራት መቶ ሃምሳ (450) በላይ የሚሆኑ ላፕቶፕ ኮምፒውተሮችን እና ስምንት (8) የላብራቶሪ ናሙና ማድረስና የምርመራ ውጤት መመለስ የሚያስችሉ ተሸከርካሪዎችን በግሎባል ፈንድ በመግዛት ያስረከቡት የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ ሲሆኑ በተለይ እንደዚህ አይነት ድጋፎች በላብራቶሪ ናሙና ምልልስ ወቅት የሚያጋጥመውን ተግዳሮት በእጅጉ ይቀንሳል ብለዋል፡፡
በተጨማሪም የኢትዮጵያ ምግብ መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አንድ መቶ ሰማንያ አምስት (185) የላፕቶፕ ኮምፒውተሮችን ለተቆጣጣሪ አካላት ድጋፍ ያበረከተ ሲሆን የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ም/ል ዋና ዳይሬክተር አቶ ስዩም ወልዴ በበኩላቸው ድጋፉ በቁጥጥር ስራው ላይ የሚኖረው እገዛ እና የቁጥጥርና ክትትል ስራዎችን ከማዘመን ረገድ የሚኖረው አበርክቶ ከፍተኛ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Finfine
Addis Ababa