Beza Lealem
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Beza Lealem, Health/Beauty, Addis Ababa.
13/12/2025
25/11/2025
21/07/2025
“በላቀ ትጋት ቀጣይነት ያለው ስኬት ለማስመዝገብ እንሠራለን!”
የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የነዋሪውን ኅብረተሰብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እና የተጀመረው የብልጽግና ጉዞ በስኬት ከዳር እንዲደርስ ባለፉት ዓመታት ዘርፈ ብዙ ተግባራትን በማከናወን እና ዙሪያ መለስ ርብርብ በማድረግ አንጸባራቂ ስኬቶችን አስመዝግቧል፡፡ በሁሉም መስኮች ሕዝብንና አጋር አካላትን በማስተባበር የተከናወኑ ሥራዎች ተጨባጭና የሚቆጠሩ ድሎችን ያስገኙ ከመሆኑ ባሻገር በመተባበር መሥራት ምንጊዜም አሸናፊ እንደሚያደርግ ያረጋገጡ የክፍለ ከተማችን አሻራዎች ናቸው፡፡
በ2015 እና 2016 በጀት ዓመታት የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በአጠቃላይ አፈጻጸም በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙት አሥራ አንድ ክፍለ ከተሞች የቀዳሚነት ደረጃን ያገኘ ሲሆን፣ በ2017 በጀት ዓመትም ይህንን ስኬታማ ጉዞ አጠናክሮ በማስቀጠል በበጀት ዓመቱ አጠቃላይ የተግባራት አፈጻጸም በከተማ አስተዳደሩ በተካሄደው ምዘና 95.8 ከመቶ አጠቃላይ ከፍተኛ ውጤት በማግኘትና አንደኛ በመውጣት ለሦስተኛ ተከታታይ ዓመት የዘመናዊ መኪና ተሸላሚ ለመሆን በቅቷል፡፡ ይህ ተከታታይ ድል በመላው የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች እንድሁም የመንግስት ሰራተኞች፣ በባለድርሻ አካላት እና በመላው የክፍለ ከተማችን ነዋሪዎች የጋራ ርብርብ የተገኘ ስኬትና ውጤታችን ነው፡፡ ያገኘነውን ተጨማሪ ድል እያጣጣምን፣ በአሸናፊነታችን ሳንዘናጋ ለላቀ ድልና ስኬት በጀመርነው የትጋትና የስኬት መንገድ እጅ ለእጅ ተያይዘን መጓዛችንን እንቀጥላለን፡፡
የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት
ሐምሌ 14/2017
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa