Adem siraj

Adem siraj

Share

Man United 🍏

Photos from Adem siraj's post 03/05/2026

ድል ለሀያሉ እና ለታላቁ
Man United

Photos from Adem siraj's post 20/03/2026

እንኳን ለ1447ኛው ኢድ አል ፈጥር በሰላም አደረሳችሁ።
በዓሉ የሰላም የፍቅርና የመተሳሰብ ፣እንድሁም ከአመት አመት የምናከብርና የምንሰባሰብ አላህ ያድርገን አሚንንንን 🙏🙏🙏🙏
ኢድ ሙባረክ

11/09/2025

😍 OFFICAL

2018 ለ365 ቀናት በኢትዮጵያ ካላንድር ላይ የሚያቆየውን የ 1 ዓመት ኮንትራት አሁን ላይ በይፋ ተቀብሏልልልልልልል 🔥🇪🇹

🔺🔹🔹 2️⃣0️⃣1️⃣8️⃣ 🔺🔹🔹

Here We Go

20/08/2025

# ሶስት (3) ነገሮች በህይወትህ ላይ ትልቅ ትምህርት ይሰጡሃል
1.ባዶ የሆነ ኪስ
2 .የተራበ ሆድ
3 .የተሰበረ ልብ

18/08/2024

Pedophilic Disorder(ከህፃናት ጋር በወሲብ የመሳብ ትልቅ የአዕምሮ በሽታ)
ይህ pedophilic disorder የተባለው ትልቅ የአዕምሮ እክል እጅግ ከባድ በሽታ ነው ሰዎች በዚህ በሽታ በሚጠቁ ጊዜ ከ13 እናከዚያ በታች እድሜ ባላቸው ህፅናት ላይ የወሲብ ፍላጎት እንዲኖራቸው ያደርጋል ፤እነዚህ ሰዎች ሴቶችን ብቻ ሳይሆን ወንዶችም ላይ ይህን የመፈፀም ፍላግት ያድርባቸዋል ይህነገር ከባድ የአዕምሮ በሽታ ነው።
ምንምኳ በጥናት መረጋገጥ ባይችልም ሰዎች በልጅነታቸው ይደርስባቸው የነበረ የፆታ ጥቃት ካለ በዚያ እያደገ ሄዶ ትልቅ ሰው በሚሆኑ ወቅት በዚህ የአዕምሮ እክል የመጠቃት ሰፊ እድል እንዳላቸው ይታመናል።

። ይህ በሽታ ይድናል?
በጭራሽ የሚድን በሽታ እንዳልሆነ ሳይንስ ያስረዳናል ከ2001 እስከ 2003 ድረስ ህፃናት ለይ ፆታዊ ጥቃት ባደረሱ 1100 ሰዎች ላይ በተደረገ ጥናት 63% ሰዎች ደግመው ህፃናትን የማጥቃት ፍላጎት ያላቸው ናቸው።
።።። ባለሙያወች ያ ሰው ወደ ጥቃት መልሶ እንዳይገባ ሊረዱት ቢችሉም እንድድን ግን ሊያደርጉት በጭራሽ አይችሉም ብሎ ሳይንሱ በግልፅ አስቀምጧል።
።
ታራሚ ቤቶች?

በህግ ሰዎች አጠራር ታራሚ ቤት በተለምዶ እስር ቤት አንድ ሰው የሚገባው ካጠፋው ጥፋት ያገግማል ይታረማል የሚል እምነት ስላለ ነው ነገርግን በዚህ በሽታ የተጠቁ ሰዎች የማገገም ወይም የመዳን ምንም እድል እንደሌላቸው ግልፅ ነው።

እንደሳዉዲ ባሉ ሀገራትም ይህ ስለሚታወቅ ነው የመድፈር ወንጀል የሚፈፅሙ ሰዎች የሞት ፍርድ እንድፈረድባቸው የሚያደርገው ስለዚህ እነዚህ ሰዎች በበሽታ ስቃይ ውስጥ ሆነው እነዚህን ጥቃቶች ይፈፅማሉ የመዳን አማራጭም የሌላቸው በመሆኑ ከሌላ ጥፋት ለማዳን እስከ ወዳኛው ከዚች ምድር መሸኘት ብቸኛው አማራጭ ይሆናል።

። ፍትህ ለሄቨን 😭😭😭

Photos from Hakim's post 20/06/2024
28/04/2024

በቫያግራ ምክኒያት በሺህ የሚቆጠሩ ወንዶች ሞተዋል!!!!
=============================
ለስንፈተ ወሲብ የሚወሰደው በተለምዶ ቫያግራ የሚባለው መድሀኒት ምክኒያት በአለማችን በሺህ የሚቆጠሩ ወንዶች ሞተዋል። ሆኖም የመድሀኒት ሸያጩ በሀገራችን ተጧጡፏል። "ያሉበት ድረስ እናመጣለን።" የሚሉ ማስታወቂያዎች በማህበራዊ ሚዲያ መመልከት አዲስ ነገር አይደለም።

ቫያግራ (Sildenafil citrate) ሲጀመር የልብ መድሀኒት ነበር። የልብ ህመም ያለባቸው ሰዎች ደግሞ ለስንፈተ ወሲብ የመጋለጥ እድላቸው ከፍ ይላል። ሲልዴናፊል ብልት እንዲቆም የሚያደርገው የደም ዝውውርን በመለወጥ ወደ ብልት ብዙ ደም እንዲገባ የገባው ደግሞ እንዳይወጣ በማድረግ ነው። ይህ ለውጥ ደግሞ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ላይም ተፅእኖ ያመጣል።

ቫያግራ የሚጠቀሙ ሰዎች ራስ ምታት፣ የጨጓራ ህመም፣ የጀርባ ህመም ሊያጋጥማቸው ይችላል። ከሁሉም የሚያስፈራው ግን ድንገት የደም ግፊት ዝቅ ብሎ የልብ ምት መቋረጥ ነው። በአለማችን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በዚህ ምክኒያት ህይወታቸውን አጥተዋል።

ከወሲብ ጋር የተያያዙ ችግሮች ሲኖሩ በዘፈቀደ ቫያግራ ከመግዛት በተገቢው ሁኔታ ተመርምሮ ትክክለኛውን ህክምና ማድረግ የተሻለ ነው። ማስታወስ የሚያስፈልገው ወሳኙ ጉዳይ አብዛኞቹ ከወሲብ ጋር የተያያዙ ችግሮች ስነ ልቦናዊ መንስኤ እንዳላቸው ማወቅ ነው።

በዩቲዩብ የአእምሮ ጤና መረጃ ለማግኘት https://www.youtube.com/
ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Semera
Addis Ababa