Yemane Gebremedhin - MD
health is the deed
17/10/2025
https://www.facebook.com/share/p/19vRkfxLMa/
Unusual presentation of complicated relapsing fever with spontaneous hemoperitoneum mimicking surgical acute abdomen: a case report - International Journal of Emergency Medicine Louse-borne relapsing fever (LBRF) is a prevalent disease in Ethiopia, affecting malnourished and impoverished populations. Historically fatal, mortality has decreased to less than 5% with antibiotics. Symptoms include high fever, rigors, myalgia, hepatosplenomegaly, jaundice, and petechial rash. Di...
13/05/2025
የአእምሮ ህመም ህክምና ምንነትና መለያ ባህሪያት
#ክፍል አንድ
የአእምሮ ጤንነት የሰው ልጅ ትርጉም ያለው ሕይወት እና ጤናማ ግንኙነቶች እንዲኖሩት የሚያስችሉት መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ይስማሙበታል፡፡ የአእምሮ ህመም አንድ ፍቺ እንደሌለው፤ የሚደረስበት አንድ ግብ ያለው ሳይሆን እንደሂደት ሊቆጠር እንደሚችልም ይጠቀሳል፡፡
በዛሬው ዓምድ ባነሳነው የአእምሮ ህመምና ህክምና ርእስ ዙሪያ፤ ስለአእምሮ ህክምና ምንነት፣ ህመሙን እንዴት መለየት እንደሚቻል እና ተያያዥ ጉዳዩችን እንዳስሳለን፡፡
በዚህ ጉዳይ መረጃውን በማጋራት የተባበሩን በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የአዕምሮ ትምህርት ከፍል ሐላፊ ዶ/ር ባርኮት ሚልኪያስ ናቸው፡፡
የአዕምሮ ህክምና ትምህርት ክፍል አመሰራረት
የአዕምሮ ህክምና በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ50ዎቹ መጨረሻ (እአአ 1966) በውስጥ ደዌ ህክምና ትምህርት ክፍል ሥር እንደአንድ አነስተኛ ዘርፍ ሆኖ ነበር የተመሰረተው፡፡ የመሰረቱትም ከደች የመጡ ፕሮፌሰር ሮበርት ጊል የተባሉ የአእምሮ ሃኪም ናቸው፡፡
ከውስጥ ደዌ ህክምና ክፍል ወጥቶ ራሱን ችሎ የአዕምሮ ህክምና ክፍል የሆነው እአአ በ1973 ነው፡፡ እንደክፍል ሆኖ አገልግሎት ቢሰጥም፤ በስሩ የትምህርት መርሃ ግብሮች በተለይም የአእምሮ ህክምና ስፔሻላይዜሽን አልነበሩትም፡፡ በአእምሮ ህክምና ትምህርት ስፔሻላይዝድ ያደረጉ ባለሙያዎች ትምህርት መውሰድ ከጀመሩ ደግሞ 21 ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡
ትምህርት ክፍሉ አገልግሎት የሚሰጥበት የራሱ ቦታ አልነበረውም፡፡ ነገር ግን በአዲስ አበባ ካሉ የተለያዩ ሆስፒታሎች ጋር የአእምሮ ህክምና አገልግሎትን ማስጀመርና አገልግሎቱን እንዲጠናከር ማድረግ ችሏል፡፡ በጳውሎስ ሆስፒታል እና በየካቲት 12 ሆስፒታል አገልግሎቱን በማስጀመርም ሰርቷል፡፡
እስካሁን ድረስ የቀጠለው ደግሞ በዘውዲቱ ሆስፒታል እየተሰጠ ያለውን አገልግሎት መጥቀስ ይቻላል፡፡ እንዲሁም አማኑኤል፣ የካ ኮተቤም የአእምሮ ህክምና አገልግሎትን ሰጥቷል፡፡ የትምህርት ክፍሉ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዜሽን ሆስፒታል ውስጥም የአእምሮ ህክምና አገልግሎት ይሰጣል፡፡
የትምህርት ክፍል እንደመሆኑ በክፍሉ መማር ማስተማር ይከናወናል፣ ሳይንሳዊ ጥናቶች ይሰራሉ፣ የሕክምና አገልግሎትም አለው፣ ማህበረሰብ አገልግሎትም አንድ አካል ሆኖ ይተገበራል፡፡
እንደሆስፒታል ሲታይ የመጀመሪያ እና ለረጅም ጊዜም አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው አሁንም ስፔሻላይዝድ የሆነ የአእምሮ ህክምና አገልግሎት የሚሰጥ አማኑኤል ሆስፒታል ብቻ ነው፡፡
ሆኖም የጥቁር አንበሳ ስፔሻይዝድ ሆስፒታል ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አማኑኤል ሆስፒታል ላይ ከምስረታው ጀምሮ ያለውን ህክምና በማጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡
የአእምሮ ህክምና ምንድን ነው ?
የአእምሮ ህክምና በጣም ሰፊ ነገር ነው፡፡ ሰዎች በእለት ተእለት እንቅስቃሴያቸው ላይ ጤናማ ሆነው ለመኖር ከሚያሥፈልጋቸው አንዱ ነገር ውስጥ ጤነኛ አእምሮ እንደመሆኑ ትኩረቱም እዚሁ ላይ ነው፡፡ ይህ ማለት የሰዎችን አመለካከት፣ ስሜታቸውን፣ ባህሪያቸውን ወይም ድርጊታቸውን በአጠቃላይ ጤናማ በሆነ መንገድ ህይወታቸውን መምራት እንዲችሉ ማብቃት ወይም ማገዝ ነው፡፡
የአእምሮ ጤና ሲባል የሚደረስበት አንድ ግብ ሳይሆን እንደሂደት ልንቆጥረው የምንችለው ነው፡፡ በመኪና ምሳሌ አድርገን ብንመለከት የሚደረስበት ቦታ ሳይሆን መኪናው የሚሽከረከርበት መንገድ አድርገን ልንመለከተው እንችላለን፡፡
አንድን ሰው በአእምሮ ጤነኛ ለማድረግ ሳይሆን ህይወቱን በተስተካከለ ሁኔታ እንዲመራ ለማድረግ ነው፡፡ ለምሳሌ የአለም ጤና ድርጅት የአእምሮ ጤናን ፍቺ፤ አካላዊ ጤና፣ የአእምሮ ጤና፣ ማህበረሰባዊ ጤና እና መንፈሳዊ ጤንነትም አለ ሲል ያስቀምጧል፡፡
ስለዚህ አእምሮ የሚባለው ክፍል ሰው ሕይወትን ሲመራ ስሜቱን፣ ድርጊቱን፣ ግንዛቤውን፣ ማመዛዘን መቻሉን ሁሉ በተገቢው ሁኔታ እየመራ ትርጉም ያለው ሕይወት እና ከሌሎች ሰዎች ጋር ጤናማና መስተጋብር ኖሮት እንዲኖር የማድረግ ሂደት ነው፡፡ እርሱ ላይ የሚደረግ የትኛውም አይነት እገዛ እና ድጋፍ የአእምሮ ጤና ህክምና እንለዋለን፡፡
ህክምናው አሁን ማህበረሰቡ ውስጥ እንደሚታሰበው አይነት የአማኑኤል ተብላ የምትታሰበውን መድሃኒት መስጠት አይደለም፡፡ ግለሰቡን/ቧን ከመረዳት ጀምሮ ያለውም ህክምና ነው፡፡ ግለሰቧን/ቡን ማነጋገርም ሆነ መድሃኒት ማዘዝም ህክምና ነው፡፡
የንግግር ሕክምና አንዱ ሲሆን ከዛም አልፎ በአካባቢው ካሉ ሰዎች ጋር የተሻለ እገዛ እንዲያገኝ ማመቻቸት በራሱ እንደአእምሮ ጤና ህክምና እገዛ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ እነዚህን ሁሉ ባካተተ መልኩ የሚደረጉ እገዛዎች በሙሉ የአእምሮ ጤና ህክምና እንላቸዋለን፡፡
ዘርፉ በራሱ አወዛጋቢ ነገር አለው፡፡ ለምሳሌ የልብ ህክምና ሲባል አልፎ አልፎ የሚመጣ ነው ወይም ከመንፈሳዊ ነገር ጋር ይገናኛል ሲባል አይሰማም፡፡ የአእምሮ ህክምና ሳይንሱ በአለም አቀፍ ደረጃ በፍጥነት እያደገ መምጣቱ በራሱ ሙያውን ልዩ ያደርገዋል፡፡
በተለይ የአእምሮ ህመም ተፈጥሯዊ ወይም አካላዊ ምክንያቶች ለአእምሮ ህመም የሚያጋልጡ አንጎል ውስጥ ግኝቶች አሉ፡፡ ህክምናውም ይበልጥ መድሃኒቶች ወይንም ደግሞ ከኤሌክትሪክ ንዝረት ጋር የተገናኙ ህክምናዎች የዘረመል ጥናቶቹን ጨምሮ የዘረመል ህክምና ለማድረግ ጉዳት የነበረበትን በማከም ረገድ ሳይንሱ በጣም አድጓል፡፡
ከቀደመው በበለጠ ተፈጥሯዊ የሆነ ፍች ያለው ማስረጃዎች ተገኝተዋል፡፡ ሳይንሱ ይበልጥ በምርመራ እና በጥናት ትኩረት እያገኘ በፍጥነት እያደገ ነው፡፡
አወዛጋቢ ነው የሚባለው ደግሞ አንጎል ውስጥ ያሉ ነገሮች ናቸው፡፡ የማናየው፣ የማንዳስሰው፣ በላቦራቶሪ ምርመራ የማናረጋግጠው ነው፡፡ ሁሉም ህብረተሰብ ስለአእምሮ ህመም የራሱ አመለካከት አለው፡፡
ስለሌላ ህመም ሳይንስ ከሚለው ውጭ ሌላ ሰው ብዙ ሊል አይችልም፡፡ ስለአእምሮ ህመም ግን ሁሉም ሰው የራሱ ለየት ያለ አመለካከት አለው፡፡ ዘርፉ ለተለያየ ህዝባዊና ግላዊ አመለካከቶች ወይም አስተያየቶች ክፍት ነው፡፡
ፍልስፍና፣ ስነአእምሮ፣ መንፈሳዊ ትምህርት፣ የማህበረሰብ ጥናት፣ ሜዲሲንም ሆነ እያንዳንዱ ክፍል ውስጥ ብንመለከት ሁሉም የተለያየ አስተያየት ሊኖረው ይችላል፡፡
ዋናውና አስፈላጊ የሆነው ደግሞ የአእምሮ ህመም በባህል ጉዳይ በጣም ስሜታዊ የሆነ ጉዳይ መሆኑ ነው፡፡ አሜሪካ ወይም ወደምዕራባውያን ጋር የአእምሮ ህመም የሚታይበት መንገድ እና ኢትዮጵያ ውስጥ የሚታይበት መንገድ ይለያያል፡፡
ምእራባውያን ጋር የአእምሮ ህመም የሚገለጥባቸው እና ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገለጥባቸው ምልክቶቹ ይለያያል፡፡ ከባህልና ከእምነት ጋር በጣም የተሳሰረ፣ የተቆራኘ እና ባህሉ ራሱ የሚገለጥበትን መንገድ ስለሚወስን ጥንቃቄ ይፈልጋል፡፡ የማይታይ ባለመሆኑ ተግዳሮትም አለው፡፡ ባህሉም በጣም ይለያል ለግላዊ አስተያየትም የተጋለጠ ነው፡፡
የአእምሮ ህመም ሙያው አሁንም የሚያወዛግቡ፣ ብዙ ክርክር ያላቸው፣ ሳይንስ ግን ከቀደመው ጊዜ የበለጠ ትክክለኛ ህመም መሆኑን እያረጋገጠ መጥቷል፡፡
በዚህ ዘርፍ ያለው የተዛባ አመለካከት በሌሎቹ ላይ በዚህ መልኩ አይስተናገድም፡፡ በመሆኑም እንደባለሙያም፣ እንደአገልግሎቱ ተጠቃሚ ወይም እንደታማሚ በብዙ ጥያቄዎችና ማስረዳት የተሞላ ነው፡፡
የአእምሮ ሃኪሞች የሚጠየቁትን ያህል ወይም እንዳለው የተዛባ አመለካከት የልብ ወይም የቀዶ ጥገና ሃኪሞች ላይ አይስተናገድም፡፡ ስለዚህ እንደባለሙያም እንደዘርፍም፣ እንደአገልግሎቱ ተጠቃሚም ወይም እንደታማሚ በብዙ ጥያቄዎች፣ ማስረዳትና ማስተማር በየቀኑ የሚታለፍበት ዘርፍ ነው፡፡ ሰፊ በመሆኑም ማንም አንድ ፍቺ ሊያስቀምጥ አይችልም፡፡
የአእምሮ ህመምን እንዴት መለየት ይቻላል ?
የአእምሮ ጤንነት የሰው ልጅ ትርጉም ያለው ሕይወት እንዲኖር እና ጤናማ ግንኙነቶች እንዲኖሩት የሚያስችሉት እንዲሁም በዚህ ሂደት ውስጥ መሄድ መቻሉ ነው፡፡ በዚህ ሂደት የተለያዩ እክሎች ሊገጥሙ ይችላሉ፡፡ አንዳንዶቹ አነስተኛ ሲሆኑ ሰው በራሱ ሊያልፈው ይችላል፡፡
የተለያየ መንገድ ተጠቅሞ ለምሳሌ ከሰው ጋር በመነጋገር፣ በራሱ ጊዜ ወስዶ በማመዛዘን፣ ወይም ሃይማኖታዊና እምነታዊ ዘዴዎችን ፈልጎ አልፎ አልፎ ከአእምሮ ጋር የሚፈጠሩ ተግዳሮቶችን ይሻገራል፡፡
ህመም ነው? ወይስ ህመም አይደለም? የሚለውን የሚለይበት መንገድ አለ፡፡ ሰው በጣም የተለመደው ህመም ላይ ሲመጣ ቸገረኝ ብሎ ከሚመጣበት ጭንቀትን እንደምሳሌ ማንሳት ይቻላል፡፡ ብዙ ሰው ጭንቀት የሚለውን ቃል ይጠቀመዋል፡፡ ማንም ፈተና ሲኖረው ልፈተን ስል ጨነቀኝ ይላል፡፡
በጣም ከባድ፣ የተቸገረበት ሥራን፣ ትዳርን ሁሉ መረበሸ የደረሰ የጭንቀት ህመም ያለበት ሰው ‹‹ጭንቀት›› የሚለውን ቃል ይጠቀማል፡፡ ነገር ግን ጭንቀት ብቻ ስለሆነ በሽታ ነው ወይም ህመም ነው ማለት አይደለም፡፡
ስለዚህ ጭንቀቱ ህመም ደረጃ ደረሰ የምንለውና የአእምሮ ህመም ብለን የምንገልጸው ስሜቶቹ ወይም ድርጊቶቹ ከተለመደው በጣም ወጣ ያሉ ሲሆኑ ነው፡፡
ወጣ የሚሉት ለምሳሌ በየቀኑ ምን ያህል አዘውትረው ይመጣሉ፣ ምን ያህል በሰውዬው/ በሴትየዋ ቁጥጥር ውስጥ ናቸው፣ ምን ያህል አልፎ/ፋ መቆጣጠር ከሚችለው/ ከምትችለው በላይ ተጽእኖ እየፈጠሩበት/ሩባት ነው ? የሚለውን በመመልከት ነው ይህ ነገር የአእምሮ ህመም ነው ወይም አይደለም የምንለው፡፡
አንድ የሚወደውን ያጣ ሰው በጣም ተረብሾ ሊቆይ ይችላል፡፡ ከተወሰነ መጠን በላይ ሲሆንና ጫናው በጣም ለየት ያለ ሲሆን፤ ይሄ ነገር የአእምሮ ህመም ሊሆን ይችላል ብለን እንገምታለን፡፡ የምናያቸውን ነገሮች በባለሙያ አጢነን ከዛ በኃላ የአእምሮ ህመም መሆንና አለመሆኑን መለየት የምንችለው፡፡
በዚህ መንገድ ካየነው ሁሉም ከአእምሮ ጋር የተያያዘ ተግዳሮት/ ችግር ህክምና አያስፈልገውም፡፡ ህመም ነው ከተባለ ግን ሁሉም መታከም ይችላል፡፡ ስም የተሰጠው ህመም ከሆነ ባለሙያ አይቶ ያረጋገጠው ከሆነ መታከም ይችላል፡፡
ሊድን ይችላል ? ወይስ አይችልም ? የሚለውን ማየት የምንችለው አብዛኛው የአእምሮ ህመም (ክኖኒክ) የሚባል ነው፡፡ ማለትም አንዴ ሲከሰት ታካሚው ጋር ለረጅም ጊዜ ሊቆይ የሚችል ነው፡፡
በተለይ ካልታከመ ለረጅም ጊዜ ሊቆይ የሚችል ነው፡፡ የአእምሮ ህመም ይጠፉና የማገርሸት ባህሪ ሊኖራቸው ስለሚችል አብዛኛውን ጊዜ ስናክማቸው ስኳር፣ ደም ግፊት ወይም አስም አይነት ለረጅም ጊዜ እየታከሙ ወይም እገዛ እያገኘ መቆየት ያለበት አይነት ህመም ነው፡፡
ከታከመ ግን ለውጥ ማምጣት የሚችል፣ የህመሙ ስሜቶችም አንዳንዴ ሙሉ በሙሉ በሚባል ሁኔታ ሊቀረፉ የሚችሉ ናቸው፡፡ በተለይ አብዛኛው ከባድ ያልሆነ የአእምሮ ህመም ስሜቶቹን መቅረፍ እና ስሜቶቹን ማቅለል ይቻላል፡፡
አንዳንድ ህመሞች በተለይ በጊዜ ወደህክምና ያልመጡ ህመሞች ሲሆኑ በህክምናም ሙሉ ለሙሉ ለውጥ ለማምጣት ሊከብድ ይችላል፡፡ ነገር ግን በህክምና ከመጀመሪያውም ለውጥ በማምጣት የተሻለ ደረጃ ላይ እንዲደርስ ማድረግ ይቻላል፡፡
በቀጣይ ክፍል የአእምሮ ህመም ምልክቶች፣ የአእምሮ ህመም ደረጃዎቹ፣ የተዛቡ አመለካከቶች፣ የአእምሮ ህመም አጋላጭ ምክንያቶች እና ህክምና አሰጣጡን ጨምሮ ያሉ አጠቃላይ ጉዳዩችን አካትተን እናቀርባለን፡፡
13/05/2025
የጨጓራ በሽታና የአመጋገብ ሥርዓት
የጨጓራ በሽታ ማለት በተለያዩ ምክንያቶች አሲድ ከተፈለገው በላይ በማመንጨት በጨጓራ የላይኛው ንጣፍ ላይ የሚከሰት ቁስለት ወይም ቁስለት መሰል ነገሮች የሚያመጡት ስሜት መሆኑን የሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ።
በዛሬው ዓምዳችን ስለጨጓራ በሽታ ምንነት፣ መንስኤና መፍትሄው እንዲሁም በበዓል ሰሞን ሕብረተሰቡ ሊከተላቸው ስለሚገቡ የአመጋገብ ስርዓትን እንዳስሳለን። ሙያዊ ማብራሪያውን መረጃውን የሰጡን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሕክምና ኮሌጅ የውስጥ ደዌ ሕክምና ትምህርት ክፍል መምህርና የጨጓራ፤ የአንጀትና የጉበት በሽታ ሰብ ስፔሻሊስት ዶ/ር መንግሥቱ እርቄ ናቸው።
የጨጓራ በሽታ ምንነት
የጨጓራ ሕመም ከአሲድ መመንጨት ጋር በተገናኘ የሚከሰትና ከምግብ ሥርዓት ጋር ግንኙነት ያለው ነው። በተለምዶ ሕመሙ ከመጀመሪያው የምግብ መውረጃ ቱቦ ጀምሮ ሙሉ የጨጓራ መውረጃ ቱቦዎችን በማጠቃለል የጨጓራ በሽታ ተብሎ በአንድ ላይ ይጠራል። ነገር ግን ራሳቸውን የቻሉ የተለያዩ በሽታዎች ናቸው።
የጨጓራ በሽታ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ አሲድ ከአቅም በላይ ሲመነጭ፣ አልሰር ሲፈጠር ወይም ሌላ ምክንያት ኖሮ ለዚህ ተጋላጭ የሚያደርጉ ምክንያቶች ሲኖሩ አንድ ሰው ስሜት ይኖረዋል። ይህ ስሜትም በተለያየ መንገድ ሊገለጽ ይችላል። ጤናማ ወይም የተለመደ አይነት አገላለጽ አንደኛው ነው።
ከጨጓራ ጋር ተያያዥነት ያላቸው የሰውነት ክፍሎች የሚያሳዩአቸው ምልክቶች በአሲድ መብዛት ወይም ደግሞ ቁስለት በመፈጠሩ ምክንያት የሚታዩ ምልክቶችም አሉ። ማቃር፣ ማቃጠል፣ ምግብ አለመፈጨት፣ አንዳንዴ ማስታወክ፣ የአይነምድር መጥቆር ወይም ሬንጅ መምሰል ነገሮች ይከሰታሉ። ይህ ክስተት ከጨጓራ፣ ከምግብ መውረጃ ቧንቧ እና በአንጀት የመጀመሪያ ክፍል ከአሲድ ጋር በተገናኘ የተፈጠረ ነው።
የጨጓራ ሕመም የሚባሉት ከላይ የተዘረዘሩት ናቸው። ነገር ግን የበሽታው መገለጫ አንድ አይነት ቢሆንም፤ ችግሩን የሚያመጡት መሰረታዊ ምክንያቶች ከሰው ሰው ይለያያል። ለምሳሌ አንድ ሰው የጨጓራ ባክቴሪያ ኖሮት በዛ ምክንያት የሚመነጨው የባክቴሪያ አሲድ ስለሚጨምር አልሰር (ቁስለት) ሊፈጥር ይችላል። ሲጋራ የሚያጨሱ፣ ምግብ በሥነ-ስርዓት የማይመገቡ፣ የሥራ ጫና ወይም ጭንቀት ያለባቸው ከሲጋራ ማጨሱ ጋር ተዳምሮ አሲድ ያመነጭና አልሰር ሊፈጥርባቸው ይችላል። ይህ ራሱን የቻለ ምክንያት ሊሆን ይችላል።
አንዳንድ ሰው ደግሞ በሕመም ምክንያት ከሶስት እና ከአራት በላይ መድሃኒቶችን (የስኳር፣ የግፊት፣ የኮሌስትሮል፣ የአስም እና የተለያዩ መድሃኒቶችን) እንዲወስድ ሊገደድ ይችላል።እነዚህ መድሃኒቶች በራሳቸው የጨጓራ በሽታ ያመጣሉ። ይህ ማለት የጨጓራውን አካል በቀጥተኛ ሁኔታ ስለሚፈጩ ቁስል ያመጣሉ። ቁስሉ ደግሞ በአሲድ ይባባሳል። እነዚህና መሰል ተጋላጭ ሊያደርጉ የሚችሉ ምክንያቶቹ ብዙ ናቸው።
በአጠቃላይ የጨጓራ በሽታ ማለት በተለያዩ ምክንያቶች አሲድ ከተፈለገው በላይ በማመንጨት በጨጓራ የላይኛው ንጣፍ ላይ የሚከሰት ቁስለት ወይም ቁስለት መሰል ነገሮች የሚያመጡት ስሜት ነው።
የጨጓራ ሕመም እና ሕክምና
የጨጓራ ሕመም ብዙ አይነት እንደመሆኑ ሕክምናውም ይለያያል። ለምሳሌ በምግብ መውረጃ ቧንቧ ላይ አሲድ በብዛት ወደ ጉሮሮ መውጣት ሕመም በመድሃኒት ወይም ምግብ በማስተካከል ይታከማል። ስሜቱም ጥሩ ወደሚባል ደረጃ ይመለሳል። ሆኖም ግን ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ተመልሶ የመምጣት እድል ሊኖረው ይችላል።
ዋና ጨጓራ በሚባለው ቦታ ውስጥ የሚፈጠሩ አልሰሮች ለምሳሌ ሲጋራ የሚያጨስ ሰው ሲጋራ ማጨሱን ካቆመ፣ ባክቴሪያ ከሆነ ደግሞ ባክቴሪያው ከታከመ በተጨማሪም የአሲድ መድሃኒት ከወሰደ እና የሚሰጣቸውን ምክር የሚያሟሉ ታካሚዎች ከሆኑ አልሰሩ በሂደት ይድናል። ስሜቱም ሙሉ ለሙሉ ይጠፋል።
ነገር ግን አንዳንዴ ጨጓራ ውስጥ ያለ ቁስል ሁሉ የጨጓራ አሲድ መድሃኒት ብቻ ላያድነው ይችላል። መልኩን ወደእጢ ወይም ወደካንሰር የቀየረ ሊሆን ይችላል። እንደዚህ በሚሆንበት ጊዜ ታካሚዎቹ ክብደት ይቀንሳሉ፣ ደም ማነስ ይይዛቸዋል፣ አይናቸው ቢጫ ይሆናል፣ ሰገራቸው ይጠቁራል፤ እነዚህና መሰል ነገሮች ይታያሉ። በጨጓራ መድሃኒት የማይመለስ ሕመም ይኖራቸዋል።
በዚህ ጊዜ በኢንዶስኮፒ ምርመራ ናሙና ተወስዶ ናሙናው የቁስልነት ወይም የካንሰርነት ባሕሪ እንዳለው ከተረጋገጠ በኋላ የቁስል ከሆነ ይድናል። ካንሰር ከሆነ ደግሞ ደረጃውን ወደ መወሰን ይኬዳል፤ ደረጃው በቀዶ ጥገና የሚሰራ ሆኖ ከተገኘ እዛ ቦታ በቀዶ ጥገና ይሰራል። ተዛማጅ የሆኑ የጨረር ሕክምና ወይም ኬሞ ቴራፒ ሕክምና የሚያስፈልገው ከሆነ ሊሰጥ ይችላል። ሁለተኛው ነገር ወጣ ያለ እና ያልተለመደው የጨጓራ ችግር ነው ማለት ነው።
አብዛኞቹ የጨጓራ በሽታዎች በሥርዓት ከታከሙ ይድናሉ። የተወሰኑት ደግሞ መልካቸውን ከቀየሩ መዳን በማይችሉበት ደረጃ ላይ ሊሆን ይችላል።
የጨጓራ ሕመምና የሕብረተሰቡ ግንዛቤ
ማሕበረሰቡ ስለጨጓራ በሽታ ግንዛቤዎች አሉት። ነገር ግን ትልቁ ችግር የሚሆነው እና ብዙ ሰው ሲቸገር የሚስተዋለው ታክሞ የሚድን እና ታክሞ የማይድንን የጨጓራ በሽታን መለየት ላይ ነው። በጊዜው እና በአግባቡ ቢታከም የሚድነውን በሽታ ከፍ ወዳለ ደረጃ መቀየሩን አለማወቅ እና ምርመራዎችን የመፍራት ስጋት አለ። አንድ ሕመምተኛ ታክሞ መዳን በሚችልበት ሂደት ባለመታከሙ በሽታው ወደ ከፍተኛ ደረጃ ሊሸጋገር ይችላል። ብዙ ጊዜ ያለው ችግር ሰዎች ግንዛቤ ቢኖራቸውም ወደ ሕክም ተቋም አይሄዱም።
አንዳንዶች ወደ መድሃኒት መደብር ሄደው በራሳቸው መድሃኒት ይጠቀማሉ። መድሃኒት በሚውጡበት ጊዜ ጊዜያዊ መፍትሄ ሲያገኙ ሃኪም ማየት የነበረበት አንዳንድ መሰረታዊ የበሽታው መገለጫዎች ታክሞ የሚድነውን ከማይድነው ጋር የሚለይበትን ጊዜ ያሳልፋል። ታካሚው ያንን ጊዜ በከንቱ በማባከኑ በኋላ ላይ በሽታው መልኩን ቀይሮ የመምጣት ሁኔታ ያጋጥማል። ይህ ብዙ ጊዜ በሕክምና ተቋማት የሚያጋጥም ነው።
ስለሕመሙ በሕብረተሰቡ ዘንድ ሙሉ ለሙሉ ግንዛቤ አለ ማለት ባያስደፍርም ብዙ ሰው የጨጓራ በሽታን በስሜት ያውቀዋል። ሆኖም ግን ትልቁ ችግር የሚሆነው የጨጓራ በሽታ ሁሉ ሁሌም ስሜት ላይኖረው ይችላል። አንድ ሰው ውስጥ ትልቅ ቁስል ኖሮት ካንሰር ደረጃ ደርሶም ክብደት ብቻ ሊቀንስ ይችላል። ማቃር ሳይኖረው፣ ማቃጠል ሳይሰማ፣ አለመፈጨት ሳያጋጥም በኋላ፤ ክብደትህ አነሰ፣ ደም ማነስ አለብህ ተመርመር ተብሎ ወደ ሕክምና ሲመጣ ጨጓራው ላይ አልሰሩ ወደ ካንሰር ተቀይሮ ሊሆን ይችላል።
ከግንዛቤ ጋር በተያያዘ ሌላው ጉዳይ የአመጋገብ ስርዓትን ይመለከታል። በኢትዮጵያ የአመጋገብ ስርዓት እንጀራ ነገርና መሰሎች፣ ፓስታ ማካሮኒ የሚዘወተሩ ናቸው። አሁን አሁን ጥራጥሬ የመመገብ ልምድ ቀንሷል። በዚህ ላይ ደግሞ ከአቅም በላይ የበሰሉ ተዘጋጅተው የሚሸጡ ምግቦችንም መመገብ ተለምዷል።
ምግብ የሚዘጋጀው በመቀቀል፣ በማብሰል እና በመጋገር ነው። በጤና ለአመጋገብ ጥሩ ነው የሚባለው በመጀመሪያ የተቀቀለ፣ በመቀጠል ደግሞ የተጋገረው፣ በመጨረሻ ረድፍ የሚቀመጠው ደግሞ የተቁላላው ወይም የበሰለ ምግብ ነው።
የበሰለ ምግብ ለጤና ጥሩ አይደለም። ብዙ ጊዜ የምንጠቀማቸው ምግቦች ቁርስ፣ ምሳ እና እራት ላይ ዘይት የተደረገበት ከአንድ ሰዓት በላይ (ከሚገባው በላይ) በስሎ የምግብነት ንጥረ ነገሩን ያጣ ነው። የተወሰኑ ንጥረ ነገሮች በእሳት ተቃጥለው፣ ዘይቱ መልካቸውን ቀይሮት ነው የምንጠቀመው። አጠቃቀሙም ሁሉም ምግብ ላይ ዘይት ገብቶ ቅባት በዝቶበት በመሆኑ ጨጓራ ለመፍጨት ይቸገራል፤ በዚህ ሰዓትም ስሜት ይኖራል። ከአሲዱ ጋር የጠለሉ ቅባቶችና ኬሚካሎች ስሜት ያመጣሉ።
ግንዛቤን በተመለከተ በከፊል ቢኖርም፤ በከፊል ደግሞ ሰው የሚመጣው ስሜት ሲኖረው ነው። ሲያቃጥላቸው ወይም አላስበላ ሲላቸው ወይም ሥራ ሲከለክላቸው ወደ ሕክምና ይመጣሉ። በዚህ ጊዜ ጤናማ የአመጋገብ ስርአት እንዲከተሉ ይመከራል።
ጤናማ የአመጋገብ ስርዓት
የሚመከሩ ጤናማ የአመጋገብ ስርዓት ከምንላቸው መካከል፤ ሆድ በጣም ሳይሞላ መብላት፣ ብዙ ያልበሰሉ ምግቦች መመገብ፣ ሲጋራ ማጨስ ካለ ማቆም ወይም መቀነስ እና መድሃኒቶችን ያላግባብ አለመውሰድ ይጠቀሳል። አልኮል በብዛት አለመጠጣት፣ በልቶ ወዲያው አለመተኛት፣ የሚስማሙ የምግብ አይነቶች ለይቶ ማወቅ፣ ምግብ በአግባብ መጠን በአግባብ ጊዜ መውሰድም ይመከራል።
ለምሳሌ አንዳንድ ሰዎች የአእምሮም የጉልበት ሥራም እየሰሩ ቁርስ ሳይበሉ ውለው ማታ 12፡00 ሰዓት የሚመገቡ አሉ። ይህ ሊሆን አይችልም። ይህ ሲሆን ጨጓራ ውስጥ ከአቅም በላይ አሲድ ይመነጫል። ከመነጨ ደግሞ ለስሜት፣ ለአልሰር ያጋልጣል። ስለዚህ ሰዎች በተገቢው ሰዓትና በተገቢው መጠን ምግባቸውን ተረጋግተው አኝከው፣ አላምጠው አዋህደው መዋጥ ይጠበቅባቸዋል። ይህ ለጨጓራ ጥሩ ስሜት ይፈጥራል።
የጨጓራ በሽታ ሊያመጡ የሚችሉ ተጋላጭ የሚያደርጉ እና የመከላከያ ነገሮች አሉ። ለምሳሌ ተጋላጭ ከሚያደርጉ ነገሮች መካከል መጨናነቅ፣ ከአቅም በላይ ሥራን ለመወጣት መሞከር፣ ሲጋራ ማጨስ፣ አልኮል በብዛት መጠቀም፣ ከአቅም በላይ መወፈር፣ ተደጋጋሚ ተገቢ ያልሆኑ መድሃኒቶች መውሰድ፣ ምግብ በሰዓት አለመብላት ለጨጓራ ጫና ይፈጥራል።
እነዚህ ሁሉ አሲድ በማብዛት የመከላከያ ስልቶቹን በማጥቃት የጨጓራውን ንጣፍ ለአሲድ ተጋላጭ ያደርጉታል። መከላከያ ስልቶቹ በተፈጥሮ የጨጓራ የላይኛው ንጣፍ ሙከስ የሚባል ንፍጥ የሚመስል ነገር አለው። ከቁስለት አሲዱን ይከላከላል።
ጨጓራ ላይ የተፈጠረ ቁስለት በኢንዶስከኮፒ ክትትል ይፈልጋል። የአንጀት የመጀመሪያ ክፍል ላይ የተፈጠረ ቁስለት ቶሎ ይድናል። ጨጓራ ላይ የተፈጠረ ቁስለት ግን ቶሎ ላይድን ስለሚችል ተገቢ ለሆነ ጊዜ መድሃኒት ወስደው ትልቅ ቁስለቶች ከሆኑ ከሶስት እስከ ስድስት ወራት ባሉ ጊዜያቶች በኢንዶስኮፒ ታይቶ የመዳናቸውን አቅጣጫ አይቶ ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
የበዓል ሰሞን አመጋገብ ሥርዓት
የተለያዩ የማሕበረሰብ ክፍሎች የተለያየ ሃይማኖት ይከተላሉ፣ የተለያየ አጽዋማት አላቸው። እንደየእምነቱ ለምሳሌ በኦርቶዶክስ እምነት ከጾም በኋላ ከጾም ምግብ ወይም ቅባት ነክና ስጋ ነክ ካልሆኑ ምግቦች ወደ ቅባት እና ስጋ ነክ ወደ ሆኑ ምግቦች ይሻገራሉ። በሙስሊም ቢጾሙም ቅባት ነክ ምግብ ነገር ማታ ላይ ስለሚፈቀድ ያን ያህል አንጀታቸውን አይከብዳቸውም። ለረጅም ጊዜ ቅባት የረሳ፣ በመጠኑ መብላት የለመደ አንጀት ወይም ጨጓራ በአንዴ ከፍተኛ አመጋገብ እና ካሎሪ ሲወስድ ይጨናነቃል።
ብዙ ጊዜ ቅባት የሚያበዙ ሰዎች የሃሞት ጠጠር ይኖርባቸዋል። የሃሞት ጠጠር የሚባለው ጠጠር ሳይሆን የረጋ ቅቤ እንደማለት ነው። የሃሞት ጠጠር የሚኖረው ሰው እንደጨጓራ ሕመም ስሜት ይኖረዋል። በላይኛው የሆድ ክፍል ውስጥ ማቃጠል፣ አለመፈጨት፣ መቁረጥ፣ የሆድ መነፋት፣ ማስታወክ እና የመሳሰሉ ነገሮች ያጋጥማሉ።
እነዚህ ነገሮች ለጨጓራ ስሜት እንደሰጠ ሁሉ ለሃሞት ከረጢት ላለ ጠጠር ስሜት ይሆናል። በመሆኑም በበዓል ጊዜ ማሕበረሰቡ የሚጠቀማቸው ከአቅም በላይ ቅባትና ዘይት ተኮር ናቸው። ዶሮ ወጥን በአብነት ብንመለከት ለመብሰል ቢያንስ እስከ ሶስት ሰዓት እሳት ላይ ይቆያል። እንደዚህ አይነት ምግቦች አንጀት አይቋቋማቸውም፤ ይከብዳሉ።
በመሆኑም መጠን ቢቀንስ ጥሩ ነው። አንድ ሰው ከአንድ ዶሮ ወጥ እስከ ዘጠኝ ጊዜ የሚጎርስ ቢሆን አምስት ጊዜ ብቻ ቢጎርስ ይመከራል። በጎን ደግሞ እንደቆስጣ፣ ሰላጣ፣ የተቀቀለ ድንች፣ ያሉ አትክልቶችን ተልባ መቀላቀልና ተመጣጣኝ የሆኑ ምግቦችን መጠቀም መልካም ነው።
ሁሉንም ምግቦች በጣም አጣፍጦ፣ ቆልቶ አለመመገብ ይመከራል። ቀቅለን ብንመገብ የተሻለ ነው። በዓመት በዓል ሰሞን ስጋ እስኪያልቅ ባንጠቀም ጥሩ ነው። ስጋ አብዝቶ መጠቀም አንጀትን ለከፍተኛ (የቅባት) የፕሮቲን መጠን ያጋልጣል።
ይህ ደግሞ የሰውነት ቅርጽና የክብደት መጠንን በአጭር ጊዜ ውስጥ ያዛባል። የስኳር መጠን እና ክብደት እስከ ስድስት ኪሎ ይጨምራል። ክብደት መጨመር በራሱ ለጤና ትልቅ ችግር አለው። ለመቀነስ ብዙ ጊዜ ይወስዳል። በዓመት በዓል ጊዜ አልኮልና ጣፋጮች ይወሰዳሉ። እነዚህን ከአቅም በላይ ከመጠቀም መቆጠብና በሂደት ሰውነትን አስለምዶ ቀስ በቀስ መጥኖ መጠቀም አግባብ ነው።
የአመጋገብ ስርዓት ከመጥገብ አንጻር መቃኘት የለበትም። ሰዎች በጣም እስኪጠግቡ መመገብ የለባቸውም። የሚያስፈልገውን መጠነኛ አመጋገብ መጠቀም ጥሩ ነው። ስንመገብ መጠንን መቀነስም አስፈላጊ ነው።
ምግብን ከአቅም በላይ አለማብሰል፣ ሌሎች ተለዋጭ ምግቦች አትክልትና አትክልት መሰል ነገሮችን ከስጋ ጋር በተመጣጠነ መልኩ በማዕዳችን ማቅረብ፣ ከምግብ በኋላ ተገቢ የሆነ እንቅስቃሴ ማድረግ (ወጣ ብሎ መመለስ)፣ ራትን መዝለል ለሰውነት ረፍት ይሰጣል እንዲሁም አልኮል በብዛት አለመጠቀም ተገቢ ነው የዶ/ር መንግሥቱ እርቄ መልእክት ነው።
12/05/2025
Resuscitative Endovascular Balloon Occlusion of the Aorta in surgical and trauma patients: a systematic review, meta- analysis and practice management guideline from the Eastern Association for the Surgery of Trauma
https://tsaco.bmj.com/content/tsaco/10/1/e001730.full.pdf
14/03/2025
https://doi.org/10.1177/26339447251323439
Pattern and Predictors of Positive Head Computed Tomography Scan in Mild Traumatic Brain Injury at Addis Ababa Burn Emergency and Trauma Hospital - Hilina Taye Sh*ta, Yemane Gebremedhin Tesfay, Tesfaye Getachew Shawel, Dirijit Mamo Alemu, Ayalew... Background Mild traumatic brain injury (mTBI) is one of the most common causes of emergency department presentation. However, using a head computed tomography (...
06/01/2025
https://www.facebook.com/share/p/15VHu75nnK/
በመሬት መንቀጥቀጥ (earth quake) ጊዜ መደረግ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች፦
በአዋሽ ፈንታሌ እና አጎራባች አከባቢዎች ለወራት የቆየ እና የመንቀጥቀጥ ምጣኔው (richter scale) እየጨመረ ያለ የመሬት መንቀጥቀጥ (earth quake) እየተከሰተ መሆኑ ይታወቃል። ንዝረቱም አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች እና አከባቢዎች እየተሰማ ይገኛል።
🎯የመሬት መንቀጥቀጥ ጥንቃቄዎች፦
1. በመሬት መንቀጥቀጥ ጊዜ ሊደረጉ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች፦
🛐በህንፃዎች ውስጥ እያለን በሚያጋጥምበት ጊዜ በመጀመርያ እራስን ማረጋጋት እና ባለንበት መቀመጥ ያስፈልጋል።
🛐ከጠረጴዛ፥ ዴስክ፥ ወይም አግዳሚ ወንበር ስር መደበቅ።
🔕ጭንቅላት ጉልበት ስር በማሳረፍ ጎንበስ ማለት እና አይናችንን በመጨፈን ጆሯችንን መድፈን።
⛩የምንደበቅበት ጠረጴዛ ከሌለ የህንፃ የውስጠኛው ግድግዳ ከውጫዊው ግድግዳ የመደርመስ አደጋው የቀነሰ ስለሆነ ከውስጠኛው ግድግዳ ስር መቀመጥ።
🏢በቀላሉ ሊደረመሱ እና ሊወድቁ ከሚችሉ ከደረጃ፥ ከመደርደርያ፥ ከመስኮት እና ከመሳሰሉ አካባቢዎች አስር ጫማ (10 feet) መራቅ።
🚷ሊፍት እና ደረጃን ተጠቅሞ ለመሸሽ እና ከህንፃ ለመውጣት አለመሞከር። የመሬት መንቀጥቀጡ እስኪቆም (usually seconds) ድረስ አለመሮጥ፥ አለመንቀሳቀስ እና ከመንቀጥቀጥ በኃላ ለሚፈጠር ንዝረት (after shock) መዘጋጀት።
🔥በመሬት መንቀጥቀጥ ጊዜ የሚፈጠር የእሳት አደጋ የተለመደ ስለ ሆነ ብሎም የመሬት መንቀጥቀጥ የእሳት አደጋ ማስጠንቀቅያ ደወል እና አሳንሰር እንዳይሰራ ስለሚያደርግ እሳት አደጋ መከሰቱን በንቃት ማስተዋል እና ለመሸሽ ደረጃን መጠቀም ያስፈልጋል።
🔕በመሬት መንቀጥቀጥ ጊዜ ውጭ ከሆንን ባዶ ቦታ ላይ በመቀመጥ ከዛፍ፥ ህንፃ፥ የኤሌክትሪክ ፖል እና በመውደቅ እና በመፈናጠር አደጋ ሊያደርሱ ከሚችሉ ነገሮች መራቅ።
🚗መኪና ውስጥ ከሆንን ውስጥ መቆየት እና ለመውጣት አለመሞከር።
2. ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ።
ለምሳሌ፦ ቤት ውስጥ ሊወድቁ የሚችሉ እንደ ጠረጴዛ፥ መጽሐፍት መደርደርያ፥ ጠረጴዛ እና የተሰቀሉ እቃዎች በአስተማማኝ ሁኔታ ጠብቀው መቀመጣቸውን ማረጋገጥ።
🏢ከተቻለ ህንፃዎች እና መኖርያ ቤቶች ለመሬት መንቀጥቀጥ መቋቋማቸውን ማረጋገጥ።
🧰የድንገተኛ አደጋዎች የሚያገለግሉ የህክምና ቁሶች (first aid kits), disaster kits, and earth quake specific kits ለምሳሌ፦ የእጅ መብራት፤ ጠንካራ ጫማ (ከስከስ) እና የአደጋ ኮፍያ (helmet) መያዝ ያስፈልጋል።
🚷አደጋ አድራሽ ከሆኑ ህንፃዎች፥ ተራራ እና ድንጋያማ ቦታዎች፥ ትላልቅ ዛፎች፥ የኤሌክትሪክ ፖሎች እና የመንገድ ዳር መብራቶች መራቅ እና ባዶ ሜዳ ቦታ ላይ መቆየት።
Stay still, stay safe!❤
Source:
Earthquake Precautions
https://www.mcasiwakuni.marines.mil/Emergency-Preparedness/Earthquake-Precautions/
ዶ/ር የማነ ገብረመድህን: የድንገተኛ እና ጽኑ ህሙማን ህክምና ስፔሻሊስት ሐኪም
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Gulelle
Addis Ababa
12/05/2025