Mesfin bekele

Mesfin bekele

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Mesfin bekele, Health/Beauty, Addis Ababa.

Photos from Lideta Woreda 3 Communication Office's post 22/05/2026
20/05/2026

የሰዎችን ደስታና የከተማዋን እድገት መሸከም ያቃተው አፍራሽ ኃይል ይውደም

በአንድ በኩል ለሺዎች የሥራ ዕድል የሚፈጥር የኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገነባ፣ ለሕፃናትና ለደካሞች የምገባ ፕሮግራም የሚዘረጋ እና ዛሬ በጥቅሉ ገብስ ተራ ተብሎ በሚጠራ አከባቢ ደግሞ ከ370 በላይ አባወራዎችንና እማወራዎችን የቤት ባለቤት አድርጎ የእንባ አባሽ የሆነ የከተማ አስተዳደር አለ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ይሄ ሁሉ መልካም ስራ ሲሰራ እንቅልፍ የሚያጣ፣ የሰዎችን ደስታና የከተማዋን እድገት መሸከም ያቃተው አፍራሽ ኃይል አለ።

ዛሬ የተረጨው የኮዬ ፈጬ እና የአራብሳ ሳይት የሱቆች የውሸት ወሬ፣ ከተማዋ እያስመዘገበችው ያለውን ተከታታይ የልማት ድሎች ለመሸፈንና የህዝብን ልብ በጥርጣሬ ለመሙላት የተወረወረ የክፋት አረር ነው። አስተዳደሩ የዜጎችን መሰረታዊ ጥያቄዎች በተግባር ሲመልስ፣ እነሱ ግን በወሬና በሃሰት ክስ ህዝብን ለማደናገር ይሮጣሉ።

ይህ የፈጠራ ዘገባ ተቃዋሚዎች ለአገርና ለሕዝብ የሚጠቅም ምንም ዓይነት አማራጭ ሃሳብ እንደሌላቸውና ስራቸው በሙሉ መልካም ስራዎችን ማጠልሸት ብቻ መሆኑን ያረጋገጠ ነው። የ370 ዜጎች የቤት ቁልፍ የመረከብ ደስታና የ20 ሺህ ወጣቶች የሥራ ዕድል ተስፋ በወሬ አይሸፈንም፤ የከተማው አስተዳደርም በእንደዚህ ዓይነት የፌስቡክ አሉባልታዎች ሳይገታ የጀመረውን የልማትና የፍትሃዊነት ጉዞ አጠናክሮ ይቀጥላል።

የከተማዋ ነዋሪዎችም የነዚህን አካላት አፍራሽ ዓላማ በመገንዘብ፣ ከወሬ ይልቅ ለመሬት ላይ እውነታዎችና ለከተማዋ ብልጽግና ትኩረት ሊሰጡ ይገባል።

Photos from Lideta sub-city communication office's post 08/05/2026
Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address


Addis Ababa