Selwa tube
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Selwa tube, Health/Beauty, Ethopia, Adis.
የደቡብ ወሎ ዞን ትራንስፖርት ጽ/ቤት በ2016 ዓ ም ይዞት የነበረውን ከክልሉ ዞኖች የአንደኛነት ደረጃ በ2017 ዓ ም አሁንም በመድገም የክልሉ ትራ ንስፖርትና እና ሎጅስቲክስ ባለስልጣን ባዘጋጀው ዓመታዊ የዕቅድ አፈፃፀም ና ግምገማ ፕሮግራም የሠርቲፊኬትና የላብቶፕ ሽልማት ተረክቧል። ለዚህ ውጤት መምጣት አብረውን ለደከሙ የዞኑ አስተባባሪ ጠቅላላ አመራር የመስሪያ ቤታችን የዞንና የወረዳ መዋቅሮቻችን በሙሉ የወረዳ አስተባባሪዎችና ጠቅላላ አመራር አጋር አካላት የህዝብ ክንፎቻችንና መላው ህዝባችን በደቡብ ወሎ ዞን ትራንስፖርት ጽ /ቤት ስም ከፍ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ ። ከዚህም በተጨማሪ በዛሬው እለት ማለትም 04/13/2017 የህዳሴው ግድብ በመመረቅ ደስታችንን በመግለፅ የደቡብ ወሎ ዞን ትራንስፖርት ዘርፉ ከማንም በላይ ተራራ ሸለቆውን ቀን ሌሊት ሳይል ለግድቡ ተግባራት ግንባር ቀደምነትን የሚቀዳጅ በመሆኑ በዘርፉ ሁሉ ለተሳተፉ የትራንስፖርት አባላት በሙሉ ዛሬ ታላቅ የክብረ ወሰን ቀን በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ከታላቅ አክብሮት ጋር እናመሰግናለን
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
19/10/2024
05/10/2024
አድናቆት
✍ስለእራሱ ጥሩ ነገር እየተነገረው ያደገ ልጅ ማድነቅን ይማራል
✍አግባብነት ያለው ማበረታቻ እያገኘ ያደግ ልጅ በእራስ መተማመንን ይማራል
✍መቻቻል በሰፈነበት ሁኔታ ያደገ ልጅ ትዕግስተኝነትን ይማራል
✍ልጅ ከአድሎ ነጻ በሆነ ሁኔታ በአግባቡ ካደገ ፍትህን ይማራል
✍ልጅ ዋስትናና ደህንነት በተሞላበት ኑሮ ካደገ ሰውን ማመንን ይማራል
✍ልጅን በማንነቱ ተቀብለን በማቅረብ ካሳደግነው ምሉዕ ፍቅር ከአለም ይማራል
✍ጥላቻ በተሞላበት አካባቢ ያደገ ልጅ ጠባጫሪነትን ይማራል
✍ልጅ በሃፍረት ካደገ የጥፋተኝነት መንፈስን ይማራል
…. እንዳለው ዶርቲ ሎው
በየትኛውም ስፍራ የሚኖር የሰው ልጅ ህጻንም ይሁን አዋቂ አድናቆትንና ሙገሳን ይወዳል እንዲሁም ይፈልጋል፡፡ መደነቅ በሰዎች ዘንድ ትኩረት ማግኘታቸንን ስለሚያመላክት ተደናቂው ክብርና የመንፈስ ከፍታ ይሰማዋል፡፡ “አንበሳ ፣ ጎበዝ ፣ ጀግና ፣ በጣም ድንቅ ስራ ነው የሰራኸው…..ወዘተ” ሰዎች አድናቆትን ለመግለጽ የሚጠቀሙባቸው ቃላት ናቸው፡፡
አድናቆት ተስፍ ለቆረጡና ምንም ማድረግ አንችልም ብለው ለተቀመጡት እንደ ጉዞ ስንቅ በማገልገል እንደገና ተስፋቸውን አለምልመው ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲደርሱ ይራዳቸዋል ይላሉ ፡፡
ወጣት ልጆችን እንዴት እናድንቃቸው?
ትልቁ ትኩረትና ጥያቄ ልጆችን ማድነቅ ያስፈልጋል የሚለው ሳይሆን እንዴት እናድንቃቸው የሚለው ነው፡፡ ብዙ የምርምር ስራዎች እንደሚያመለክቱት የልጆችን የስራ ሂደት ማድነቅ ልጆች ጠንክረው እንዲሰሩ ፤ እንዲማሩ ፤ እንዲመራመሩና ስለ ችሎታቸው አወንታዊ አመለካከት እንዲኖራቸው ይረዳል፡፡ በተጨማሪም በግልጽነትና በእውነተኝነት ላይ የተመሰረት አድናቆት የልጆችን በእራስ መነሳሳት ያሳድጋል፡፡ ወጣት ልጆችን ለማድነቅና ለማበረታታት ከዚህ የሚከተሉት ነጥቦች ወሳኝነት አላቸው፡-
✍ስለ ልጆችች ስራና ጥረት መግለጽ፡- ፍርደ ገምድልነት የሌለው ውሳኔ በመስጠት የስራዎቻቸውን ጥረት ማድነቅ
✍ለአወንታዊው ስራና ጥረት ትኩረት መስጠት
✍ተግዳሮት ለሌለውና ብዙ ጥረት ለማይጠይቅ ስራ አድናቆትን መቆጠብ
✍አድናቆቱና ስራው ተመጣጣኝ መሆን አለበት
✍አግባብነት ያለውን ድርጊት በመምረጥ አድናቆትን መስጠት
✍በጊዜ ሂደት አድናቆትን መቀነስ ምክንያቱም ልጆች በአድናቆት ላይ ጥገኛ በመሆን ለመደነቅ ብቻ ሲሉ አንድን ነገር እንዲከውኑ ስለሚገድባቸው፡፡
✍አድናቆት ተፈጥራዊ ሂደትን ተከትሎ መቅረብ አለበት ከበጎና ከመልካም ድርጊት በኋላ የሚከተል፡፡
በአጠቃላይ የአድናቆት ዋንኛው ግብ ልጆች በእራሳቸው ተነሳሽነት አንድን ድርጊት እንዲከውኑና ተግዳሮቶችን በመቋቋም ጥገኝነትን አስወግደው ወደ ሚፈልጉት የዕድገት ምዕራፍና ውጤት እንዲሸጋገሩ ማስቻል ነው፡፡
02/10/2024
"ሕግ የማስከበር ሂደቱ የሚቆመው የክልሉ ሰላም ሙሉ በሙሉ ሲረጋገጥ ነው" ኮሎኔል ጌትነት አዳነ
በክልሉ የተፈጠረውን የሰላም እጦት ለማስተካከል ሕግ የማስከበር እርምጃ እየተወሰደ ነው። የሕግ ማስከበር እርምጃውን በሚመለከት የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና የክልሉ መንግሥት በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።
በክልሉ ያለው የጽንፈኛ ቡድን የመከላከያን የቆየ ቁስል እየነካ እና ትዕግስቱን እየተፈታተነ የመጣ እንደ ነበር ይታወቃል ያሉት የሀገር መከላከያ ሠራዊት የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ለሕዝብ ሰላም ሲባል ብዙውን ነገር በዝምታ አልፏል ብለዋል።
ለመከላከያ ሠራዊት የሚሰጠው ዝቅ ያለ ግምት፣ ስም ማጥፋት እና ማጠልሸት ከአማራ ሕዝብ ሥነ ልቦና የመነጨ እንዳልኾነ ሠራዊቱ ያውቃል ያሉት ኮሎኔል ጌትነት ሠራዊቱ ለሕዝብ ሰላም ሲባል ዛሬም ከኢትዮጵያዊነቱ ሳይወርድ ሕግ ያስከብራል ብለዋል።
የኦፕሬሽኑ ዓላማ ሁከትን እና ብጥብጥን አስወግዶ ለክልሉ መንግሥት እና ሕዝብ ሰላምን ማስፈን ነው ያሉት ኮሎኔል ጌትነት አዳነ "ሕግ የማስከበር ሂደቱ የሚቆመው የክልሉ ሰላም ሙሉ በሙሉ ሲረጋገጥ ነው" ብለዋል።
መከላከያ ሠራዊት በጽንፈኛ ቡድኑ ላይ የሚወስደው ኦፕሬሽን የተጠና፣ አውድን የለየ፣ ጀሌን ከመሪ የነጠለ እና የቡድኑን ሴል በሚበጣጥስ መልክ የሚመራ ነው ብለዋል። ከሰሞኑ በከተሞች አካባቢ የተፈጸሙት እርምጃዎች ውጤት ያሳዩ ነበሩ ብለዋል።
መከላከያ የአማራን ሕዝብ ስለሚያከብር የክልሉ መንግሥት የጀመረው የሰላም ጥረት ዳር እንዲደርስ የሚችለውን ሁሉ አድርጓል ያሉት ኮሎኔል ጌትነት ከመንግሥት ጋር በሰላማዊ መንገድ የሚነጋገሩ ካሉ በሮቹ ያልተዘጉ ቢኾኑም መከላከያ ግን ሕግ ማስከበሩን አጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት።
ወታደራዊ ኦፕሬሽኑ በሚገባ የተጠና ነው ያሉት የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊው ንጹሐንን ለመጠበቅ ሲባል በጥንቃቄ ይመራል ብለዋል።
የማኅበራዊ ሚዲያው ጩኽት ግን የሚጠበቅ እንደኾነ ኮሎኔል ጌትነት ጠቁመዋል። በምንም መንገድ ቢኾንም ግን መንገድ ዝጉ እና ተማሪዎች አይማሩም ከሚል ጽንፈኛ ቡድን ጋር ከዚህ ያለፈ ትዕግስት አይኖርም ነው ያሉት።
አሚኮ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Ethopia
Adis
0000