bu'aa AI Aanaa Agarfa

bu'aa AI Aanaa Agarfa

Share

jabbiloota

Photos from Prosperity Party - ብልፅግና's post 27/10/2023
Photos from Shimelis Abdisa's post 27/10/2023
Photos from Oromia Prosperity Party / OPP /'s post 27/10/2023
27/10/2023

የሰላም፤ የአንድነት እና ወንድማማችነት ተምሳሌት ለሆነው ለታላቁ የኢሬቻ በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ!

ሰማይና ምድርን ውብ አድርጎ ለፈጠረው፤ ፍጥረታትን ሁሉ አቻችሎ ለሚያኖረዉ ፣ ከዘመን ዘመን ለሚያሸጋግረው ፈጣሪ ( ዋቃ) ምስጋና የሚቸርበት ታላቁ የኢሬቻ በዓል በሚከበርበት ዋዜማ ላይ እንገኛለን፡፡ ይህ ታላቅ የምስጋና ፤የይቅርታ፤ የወንድማማችነት እሴት የሚንፀባረቅበት፤ አባገዳዎች፤ሃደሲንቄዎች፤ፎሌዎች ፤ልጃገረዶች፤ሌሎችም ወንድምና እህት ህዝቦች እና የውጭ ሀገር ዜጎች ጭምር ህብር በሆነው ባህላዊ አለባበስ ደምቀው የሚታደሙበት በዓል በጉጉት ይጠበቃልና በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ለምትኖሩ ለኦሮሞ ህዝብ እንዲሁም ለመላው ወንድምና እህት ኢትዮጲያዊያን፤ እንኳን ለታላቁ የኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ለማላት እወዳለሁ፡፡

በነጎድጓዳማው የክረምት ወራት፤ሰማይና ምድሩ ጭጋግ ለብሶ አስፈሪ በሆነበት፤ወንዞች ከአፍ እስከ ገደፍ ሞልተው ዘመድን ከዘመድ የለዩበት፤ የተደከመበት አዝመራ አሽቶ ደርሶ ከጎተራው ይግባ ይቅር ከፈጣሪ (ከዋቃ) በስተቀር ማንም እርግጠኛ በማይሆንበት እና ውጣውረድ በበዛበት፤ ተፈጥሯዊ አደጋ የሚያንዣብብበት አስቸጋሪው ጊዜ አልፎ የመኸር ወራት ተስፋን አዝለው፤ በፈገገው ሰማይ፤ በብርሃን ደምቀው ሲከሰቱ መለው የኦሮሞ ህዝብ ሰለ ፈጣሪ (ዋቃ) ምህረትና ቸርነት ምስጋና ያቀርባል፡፡

ታድያ በኢሬቻ ለፈጣሪ (ዋቃ) ምስጋና ለመቸር ወደ ሆራ ወይም መልካ ሲኬድ ቂም ቋጥሮ ኩርፍያን አዝሎ ሳይሆን በፍጹም ሰላማዊና ይቅር ባይነት መንፈስ ነውና የተኮራረፈም ሆነ ቂም የቋጠረ በዓሉን ከመታዳሙ በፊት ያቄመወን ልቡን በእርቅና ይቅርታ አንፅቶ ፍቅርና ወንድማማችነትን አንግሶ ነው በበዓሉ ላይ የሚታደመዉ፡፡ ለዚህም ነው እሬቻ የምስጋና ብቻ ሳይሆን የይቅርታ፤የፍቅር፤የወንድማማችነት እሴት መገለጫ ድንቅ ባህል ሆኖ የሚከበረዉ፡፡

ይቅርታና ምህረት፤ ሰላምና መተሳሰብ ባለበት ሁሉ ህዝባዊ አንድነት፤ አዎንታዊ መስተጋብር የፀና ስለሚሆን ኢሬቻ ለኦሮም ህዝብም ሆነ ለሌሎች ወንድም ህዝቦች የፅኑ አንድነት መሰረት ተምሳሌት ነው፡፡ የኦሮሞ ህዝብ በሃይማኖት ፣ በጎሳ ፣ በቀለም፣ ፣ በእድሜ እና ፆታ ሳይገደብ በወል ማንነት ፀንቶ በየዓመቱ በይቅርታና ምህረት መንፈስ በጋራ ቆሞ በኢሬቻ ፈጣሪን (ዋቃን) ያመሰግናል፡፡ በተለይም ከቅረብ ግዚያት ወዲህ ከኦሮሞ ህዝብ ጋር ከሀገር ውስጥ እና ከሀገር ዉጭ በርካታ ወንድም ህዝቦች በስፋት የሚታደሙበት የወንድማማችንት እሴት ማሳያ ትልቅ አለም አቀፋዊ በዓል እየሆነ ነው፡፡

እኛ ኢትዮጲያዊያን የበርካታ ድንቃድንቅ ተፈጥሮ እና ባህል ባለቤት ነን፡፡ በርካቶች ያልታደሉትን ፀጋ እኛ ተችረናል፡፡ ለአብነት ከእሬቻ ውጭ በየ አመቱ፤ የሲዳማ ህዝብ ዘመን መለወጫ ፊቼ ጭምበላላን፤ የሀድያ ዘመን መለወጫ ያሆዴን፤የጋሞ ህዝብ ዘመን መለወጫ ዮማስቃላን፤ የጌዲኦ ብሔር ዘመን መለወጫ ደራሮን፤ የውላይታ ዘመን መለወጫ ጊፋታ፤ አሸንዳ፤ እና በርካታ ተዘርዝረው ያማያልቁ፤ ያየራሳቸው ቀላማት ያሏቸውን ህዝባዊ በዓላት በጋራ እናከብራለን፡፡

በብዛሃነታችን ውስጥ የሚታዩት ህብር ቀለማት የውበታችን ምንጭ እና የአንድነታችን መሰረቶች ናቸው፡፡ ሁላችንም የየራሳችን ቀለም ይዘን በመከባበር በጋራ ስንኖር የበለጠ እንደምቃለን፡፡ አንዳችን የሌሎቻችንን ማንነት አክብረን በመደመር በጋራ ስንኖር ህበረ-ሀጋራዊ አንድነታችን በጽኑ መሰረት ላይ ይተከላል፡፡ የምንወዳት፤ ትውልድ በቅብብሎሽ መሰዋትነት ከፍሎ ያቆያት ኢትዮጲያችን ብልፅግናዋ ይረጋገጣል፡፡ ይህ እንዲሆን ደግሞ፤ ህብር የሆነውን ተፈጥሯዊ ማንነታችንን እንደመለካም እድል በመጠቀም ሊከፋፍሉን የሚሹ ሀይሎችን በጽናጽ ልንታገላቸው ይገባል፡፡

በመጨረሻም፤ ኢሬቻ ስለ ሰላም ፣ይቅርታ ፣አንድነት፣ ወንድማማችንት ብቻ እየተሰበከ ለፈጣሪ (ዋቃ) ቸርነት ምስጋና የሚዥጎደጎድበት ታላቅ በዓል ነው፡፡ ይህ ሰላማዊ በዓል ሰላማዊነቱ ተረጋግጦ እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር የሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚና ወሳኝ ነው፡፡ በዓሉ በሰላማዊና በይቅር ባይነት መንፈስ ለፈጣሪ (ዋቃ) ምስጋና የሚቸርበት ቢሆንም፤ ህዝባዊ በዓላትን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም እኩይ አላማቸውን ለማሳካት የሚጥሩ አካላትን በአይነቁራኛ መከታተል ያስፈልጋል፡፡

በዓሉ ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ እሴቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር እስከ ዋዜማው ከፍተኛ ጥረት ስታደርጉ ለነበራችሁ ለመላው የፀጥታ አካላት ፣ ለአባ ገዳዎች፤ ለሀደ ሲንቄዎች፤ ለፎሌዎች፤ ለሚዲያ ተቋማት፤ እንዲሁም በየደረጃው ለምትገኙ አመራሮቻችን ምስጋናዬን እያቀረብኩ፤ ታላቁ የኢሬቻ በዓል በፍፁም ሰላማዊ ሂደት ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር በድጋሚ በተለመደው ቁረጠኝነት የድርሻችሁን እንድትወጡ አደራ ማለት እወዳለሁ፡፡

በድጋሚ እንኳን ለኢሬቻ በዓል ዋዜማ አደረሳችሁ፡፡
ፍቃዱ ተሰማ

የብልፅግና ፓርቲ ኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃለፊ

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Agarfa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address


Agarfa