Hussein Hassen
Official
11/08/2023
21/11/2022
የአይምሮ ሰላም
ሁሉንም ለማስደሰት እንደሚጥር ሰው ከንቱ የለም! ሁሉም ሰው በተመሳሳይ ነገር አይደሰትም እኮ፤ በተለያየ ነገር ለሚደሰቱ ሰዎች ስንል ደግሞ እኛ እንደ ወረቀት መተታጠፍ የለብንም።
ህሊናችን የሚነግረንን አይምሮአችን የሚያዘንን ልባችንን በደስታ የሚቀበለውን ብቻ መርጦ ማድረግ፤ ያኔ ሰዎች ቢደሰቱም ባይደሰቱም ህሊናችን ግን ምን ነካህ እያለ አያስጨንቀንም። ወዳጄ ለህሊናህ ስትታመን ሁሌም ውስጥህ ሰላም አለ!
14/11/2022
የመፍትሄ ሰው ሁን !
ማደግ ከፈለግህ የመፍትሄ ሰው ሁን "መፍትሄ ወዳለበት ገንዘብ ይፈሳል " ስለዚህ ምንም የምሰራው አጣው ካልክ ውጣ እና ዞር ዞር ብለህ አካባቢህን ቃኝ ምን ምን የጎደለ ነገር አለው? ሰዎች ምን አስፈልጎቸዎል? በዚህ ምድር ላይ ያለ ስራ ሁሉ የተፈጠረው መፍትሄ ለመስጠት ነው ህክምናው፣ ትምህርቱ ፣ ምግብ ቤቱ ፣ ልብስ ሰፊው ፣ ሊስትሮው ሁሉም የሰዎችን ችግር በመቅረፋቸው ሰው ወደ እነርሱ እየሄደ ገንዘቡን ያፈሳል ! እድለኛነታችን የእኛ ሀገር ብዙ መፍትሄ የሚፈልጉ ጥያቄዎች መኖራቸው ነው ስለዚህ የመፍትሄ ሰው እንሁን! ያኔ ከእኛም ተርፈን ለብዙው እንሆናለን!
30/10/2022
እንደ አሸናፊ አስብ!
ሰው ምንድነው ቢሉ ደጋግሞ ያሰበውን ነው ይባላል፤ ስለዚህ ለማን ብለህ ነው አብዝተህ የጎደለህን ከሰው ያሳነሰህን የምታስበው?!
በቃ ተዓምር መስራት እንደምትችል ባንተ ምክንያት መጀመሪያ የራስህ ከዛ የቤተሰቦችህ ህይወት እንደሚቀየር አስብ እሱን እውነት ለማድረግ የምትችለው ጥግ ድረስ ጣር የቀረውን ለፈጣሪ ተወው!
09/10/2022
ሁሉም ለበጎ ነው!
ፈጣሪ በነገሮች በሁኔታዎች ነው የሚናገርህ፤ በጆሮህ መጥቶ እንዲህ አድርግ አይልህም፤ በህይወት እየሆነ ያለው ነገር በሙሉ ለምክንያት ነው።
ንቁ ሆነህ በህይወትህ የሚሆነውን ሁሉ ማስተዋል አለብህ! ደግሞ አትርሳ ተማሪ ካለ አስተማሪ የትም ቦታ አለ።
12/09/2022
ያንተ አመት ነው!
ዛፍ ለመትከል ወሳኙ ጊዜ ከ 20 ዓመት በፊት ነበር፤ ከዛ ቀጥሎ ግን ወሳኙ ጊዜ አሁን ነው! በምንፈልገው ጉዳይ ራሳችንን ለመለወጥ ጊዜው አልረፈደም፤ መወሰን ከዛ ወደ ተግባር መግባት ብቻ ነው ከኛ የሚጠበቀው። ቆራጥ ሆነን መለወጥ ለምንፈልግ ሁሉ ቀላል የሆኑ መንገዶችን እናወራለን::
ለመጀመር ጠንካራ መሆን አይጠበቅብህም ፣
ጠንካራ ለመሆን ግን መጀመር አለብህ‼️
22/04/2022
ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ!
በተስፋ ስሜት ዱዓ አድርጉ!
ዱዓ ሩቁን ያቀርባል!… ከባዱን ያቀላል! ደጃፋችን የደረሰን ክፉ ነገር ይመክታል!
ዱዓ ላለንበት መከራም ሆነ ወደ ፊት ለምንሰጋው ችግር ሁሉ ይጠቅማል!
ዱዓ መድኅን ነው! ዱዓ ጋሻ ነው! "ዱዓ የሙእሚን መሣሪያ ነው!"
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Alaba K'ulito