Tena Woyesa Worana
Interested poletics
21/08/2026
ርዕስ የጸሎት ታላቅ ኃይልና ጥቅም
ናሐሰ 15ን በፀሎት እንጨርስ {ከለሊቱ 9 ሠዓት}
አዱሱን ዓመት በድል እንቀበል! (ተነስተን እንፀልይ)
አጋንንትና የጨለማ ኃይላት የሚሸበሩበት ሰዓት
ሌሊት የጨለማው ሥልጣን የሚሠራበት ጊዜ እንደመሆኑ መጠን፣ ክርስቲያን ወዳጆች በሌሊቱ 9 ሰዓት ተነስተን በጸሎት እንትጋ የጠላት የዲያብሎስ ውጊያና ወጥመድ ይሰበራል፤ መንፈሳዊ ድልም ይገኛል።
በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ብንሆን ሳናቋጥ እንጸልይ።
በክርስቶስ ኢየሱስ የተወደዳችሁ ቅዱሳን፡ ጸሎት ማለት ለቤተክርስቲያን የመንፈሳዊ ሕይወት የሳንባ ያህል አስፈላጊ የሆነ፡ ከሰማያዊው አባታችን ከእግዚአብሔር ጋር የምናደርገው ሕያው ግንኙነ ነው።
እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚነጋገረው በቃሉ (በመጽሐፍ ቅዱስ) ሲሆን፡ እኛ ደግሞ ከእርሱ ጋር የምንነጋገረው በጸሎት ነው።
1. የሚፀልይ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር የጠበቀ ቅርበትና ህብረት ይፈጥራል
ጸሎት በሃይማኖታዊ ሥርዓት ብቻ የሚፈጸም ግዴታ ሳይሆን ከፈጣሪያችን ጋር ፍቅርን የምንለዋወጥበት መንገድ ነው። “ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል” (ያዕቆብ 4:8) እንደሚል፡ በጸሎት ወደ እርሱ ስንቀርብ የእግዚአብሔርን ልብ እናውቃለን፤ ድምፁንም ለመስማት እንበቃለን።
2. የልብ ሰላምና ዕረፍትን ያጎናጽፋል
በዚህ ዓለም ውስጥ ጭንቀት፡ ፍርሃትና ውጥረት ቢበዛም፡ ጸሎት ግን መለኮታዊ ሰላምን ያመጣል። ሐዋርያው ጳውሎስ “በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር ልመናችሁን በእግዚአብሔር ፊት አስታውቁ እንጂ በአንድ ነገር እንኳ አትጨነቁ፤ አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል” (ፊልጵስዩስ 4:6-7) ይለናል። ሸክማችንን በጸሎት ወደ እርሱ ስንጥል፡ እርሱ አእምሮን የሚያልፍ ሰላም በልባችን ይሞላል።
3. ፀሎት በፈተናና በዲያብሎስ ውጊያ
የማሸነፊያ ኃይል ነው
የመንፈስ ቅዱስ ኃይልና ጥንካሬ የሚገኘው በጸሎት ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን “ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ” (ማቴዎስ 26:41) ብሏቸዋል።
የጠላትን የዲያብሎስን ውጊያና ወጥመድ ሰብረን ማለፍ የምንችለው በጸሎት ትጋት ብቻ ነው።
4. የእግዚአብሔርን መልስና ታላቅ ነገር ያመጣል
ጸሎት በምድር ላይ ሆኖ የሰማዩን በረከትና ተአምራት የሚከፍት ቁልፍ ነው። ነቢዩ ኤርሚያስ “ወደ እኔ ጩህ፥ እኔም እመልስልሃለሁ፤ አንተም የማታውቀውን ታላቅናኃይለኛ ነገር አሳይሃለሁ” (ኤርሚያስ 33:3) ይላል። የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይልን ታደርጋለች (ያዕቆብ 5:16)።
ማጠቃለያ
ወንድሞቼና እህቶቼ! ጸሎት የእግዚአብሔርን እጅ የሚያንቀሳቅስ፡ የሰውን ሕይወት የሚያድስና ሰማያዊ ኃይልን የሚያ ታጠቅ ታላቅ መሣሪያችን ነው። ስለዚህ በሕይወታችን በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ብንሆን ሳናቋርጥ እንጸልይ።
Ermias Petros
No Maganu���
Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Abiyot Mena, Maciisho Boona
16/06/2026
"የያዕቆብ ሌሊት ያድርግላችሁ!"
ስንል ምን ማለታችን ነው?
///////////////////////////
✍ ብዙ ጊዜ ሰዎች በተለይ እኛ ክርስቲያኖች
ማታ ልንተኛ ስንል ወይም በሰላም እደሩ ከተባባበልን በኋላ "የያእቆብ ሌሊት ይሁንላችሁ" ወይም "የያእቆብ ሌሊት ያድርግላችሁ" እንባባላለን ።ይህ አባባል ከየት መጣ?
በልምድ ወይስ በመጽሐፍ ቅዱስ ይታወቃል?
✍
ቃሉ ሙሉ ለሙሉ መጽሐፍ ቅዱስን መሰረት ያደረገ ነው ።ሁላችንም እንደምናውቀው ቤተክርስቲያን የሁሉም ነገር መሰረቷ መጽሐፍ ቅዱስ ነው ።በዚህም መሰረት የአባታችን የአብረሐም የልጅ ልጅ ፤የአባታችን የይስሐቅ ልጅ የሆነው አባታችን ያዕቆብ በቤተክርስቲያን ሰፊ ምስጢር ያዘሉና ሰፊ ትምህርት የያዙ ሁለት ታሪኮች አሉት ።እኔ ግን አሁን ላነሳሁት ርዕስ የሚሆነውን ብቻ መርጬ አስቀምጣለሁ ።
✍
ሁለቱ የያዕቆብ ያማሩ ሌሊቶች
***********************
#1አንደኛውን የያዕቆብ ሌሊት የምናገኘው በኦሪት ዘፍጥ 28:1-22 ላይ ነው።
ታሪኩን በአጭሩ ለመግለጽም ኤሳው ለያዕቆብ ብኩርናውን ከሸጠ በኋላ ይስሐቅ አባታቸው ያዕቆብን ባረከው ።በዚህ ምክንያት ኤሳው በዚህ በጣም ተቆጣ እናቱና አባቱ የወንድሙ ቁጣ እስኪበርድ ድረስ ያዕቆብን ከካራን ወደ ቤርሳቤህ ወደ አጎቱ ቤት ሰደዱት።
#ያዕቆብ በመንገድ ላይ ምን አጋጠመው ?
ያንን ቆንጆ የተቀደሰ ሌሊትን አገኘ።
=>1ኛው የያዕቆብ ሌሊት
(ዘፍጥ 28:1-22)
*ወደ አንድ ስፍራም ደረሰ፥ ፀሐይም ጠልቃ ነበርና ከዚያ አደረ፤ በዚያም ስፍራ ድንጋይ አነሣ፥ ከራሱም በታች ተንተርሶ በዚያ ስፍራ ተኛ።
*ሕልምም አለመ፤ እነሆም መሰላል በምድር ላይ ተተክሎ፥ ራሱም ወደ ሰማይ ደርሶ፥ እነሆም የእግዚአብሔር መላእክት ይወጡበት ይወርዱበት ነበር።
* እነሆም፥ እግዚአብሔር በላይ ቆሞበት ነበር፥ እንዲህም አለ። የአባትህ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ይህችን አንተ የተኛህባትን ምድር ለአንተም ለዘርህም እሰጣለሁ፤
* ዘርህም እንደ ምድር አሸዋ ይሆናል፤ እስከ ምዕራብና እስከ ምሥራቅ እስከ ሰሜንና እስከ ደቡብ ትስፋፋለህ፤ የምድርም አሕዛብ ሁሉ በአንተ በዘርህም ይባረካሉ።
*እነሆም እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፥ በምትሄድባትም መንገድ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፥ ወደዚችም ምድር እመልስሃለሁ፤ የነገርሁህን ሁሉ እስካደርግልህ ድረስ አልተውህምና።
* ያዕቆብም ከእንቅልፉ ተነሥቶ። በእውነት እግዚአብሔር በዚህ ስፍራ ነው፤ እኔ አላወቅሁም ነበር አለ።
*ፈራ፥ እንዲህም አለ። ይህ ስፍራ እንዴት ያስፈራ፤ ይህ ስፍራ የእግዚአብሔር ቤት ነው እንጂ ሌላ አይደለም፤ ይህም የሰማይ ደጅ ነው።
*ያዕቆብም ማልዶ ተነሣ፥ ተንተርሶት የነበረውንም ድንጋይ ወስዶ ሐውልት አድርጎ አቆመው፥ በላዩም ዘይትን አፈሰሰበት።
*ያዕቆብም ያንን ስፍራ ቤቴል ብሎ ጠራው፤ አስቀድሞ ግን የዚያች ከተማ ስም ሎዛ ነበረ።
* ያዕቆብም እንዲህ ብሎ ስእለት ተሳለ። እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ቢሆን፥ በምሄድባትም በዚች መንገድ ቢጠብቀኝ፥ የምበላውንም እንጀራ የምለብሰውንም ልብስ ቢሰጠኝ፥
*ወደ አባቴ ቤትም በጤና ብመለስ፥ እግዚአብሔር አምላኬ ይሆንልኛል፤
✍
#2ኛው የያዕቆብ ያማረ ሌሊት የምናገኘው
ላይ ነው ።
ታሪኩ በአጭሩ ያዕቆብ በአጎቱ ቤት ራሔልን በሚስትነት ለማግኘት 14 አመት አገልግሏል ።
በመጨረሻ ግን ያዕቆብ ወደሀገሩ ተመለሰ ።
✍
#ያዕቆብ በመንገድ ላይ ምን አጋጠመው?
2ኛውን ያማረ የያዕቆብ ሌሊትን አገኘ
(ኦ ዘፍጥ 32:1-32)
*ያዕቆብም መንገዱን ሄደ፥ የእግዚአብሔር መላእክትም ተገናኙት።
*ያዕቆብም ባያቸ
��
22/05/2026
አሜን ብርታተ ኢየሱስ ❤🙏
01/05/2026
ብዙ ባልቀርበውም ግን አቃዋለሁ🤔
የተማረውን የሚያስተምር ፣
የሰበከውን የምኖር ትልቅ የእግዚአብሔር ባረያ Yosef Wariko ❤
ስለክርስቶስ ትምህርት በተጠንቀቅ የቆሜ፣ የሆዱን ከርስ ለመሙላት የማይጨነቅ፥
እንዲሁም ያልሆነውን እንደሆነው አድርገው ለማሳየት ብዙ የማይለፋ የዘመናችን ብርቅዬ የሀዋሳና ዙሪያዋ ከቃል ሕይወት ቤተክርስቲያን አብራክ የተገኘ ታላቅ የወንጌል መምህር ።
እንደዚህ ዓይነት ወርቃማ አገልጋዮችን ደግፉአቸው ።
የአቋም ሰው እወዲሃለው ❤
ጌታ እስከጨረሻው በፊቱ በብርቱ ክንዱ ደግፎ ፊፃሜህን ያሳምርልህ ።
እውነተኛ የምስራቹ አገልጋይ ...
#ተባረክ
👉ለእናንተ ያልሆነ በልክ ያልተሰፋ ነገር ባይመጣ እግዚአብሔርን ለምን አትበሉት።
መሳቅ ግዴታ አይደለም አለማልቀስም ተስፋ ነዉ
እግዚአብሔር እዉነተኛ ረዳት ነዉ።
በሁኔታዎች አይለካም በነገሮችም አይቀየርም
ጎዶሎን መሙላት ያዉቅበታል
ሽንቁርን መድፈን ያውቅበታል
እግዚአብሔርን ሚስጥረኛቹ አድርጉት
ደሞም ዝም ብላቹ አመስግኑት።
እንኳን ለብርሃነ ስቅለቱ በሰላም አደረሳችሁ።
❤🙏
Ayirro Maganu��
Contact the business
Telephone
Website
Address
Awassa
@06.COM
Alerts
Be the first to know and let us send you an email when Tena Woyesa Worana posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.