Sidama Public Health Institute Communication Affairs

Sidama Public Health Institute Communication Affairs

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Sidama Public Health Institute Communication Affairs, Health/Beauty, Awassa.

Photos from Ethiopian Public Health Institute's post 27/08/2026
Photos from Ministry of Health,Ethiopia's post 25/08/2026
25/08/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1501ኛዉ የመዉሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ:: በዓሉ የሰላም የጤናና የደስታ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።

የሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ነሀሴ 19/2018 ዓ/ም
ሀዋሳ

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
👇👇👇👇 ይመልከቱ

ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794
Web site: sphi.gov.et/emergency

Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=100083576610173

Telegram: https://t.me/c/1865772308/1

Email:- [email protected]

Photos from የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ's post 12/08/2026
Photos from Sidama Public Health Institute Communication Affairs's post 07/08/2026

የዓለም አቀፉ ጌትስ ፋውንዴሽን ልዑካን በሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ጤና አደጋ ቅኝትና ምላሽ ሥራዎች ያለበትን ደረጃ ጎበኙ።

የሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ሀምሌ 30፣ 2018 ዓ.ም.

ከዓለም አቀፉ ጌትስ ፋውንዴሽን የተውጣጡ ከፍተኛ ልዑካን በሲዳማ ክልል እየተተገበረ ያለውን የድንገተኛ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ (Public Health Emergency Management-PHEM) ሥርዓት በመጎብኘት የተመዘገቡ ስኬቶችን አድንቀዋል።

ልዑካኑን የሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ በቢሯቸው ተቀብለው ስለ ክልሉ የህብረተሰብ ጤና አደጋ ቅኝትና ምላሽ ሥርዓት፣ የተገኙ ውጤቶችና የወደፊት እቅዶች ዙሪያ ሰፊ ውይይት አድርገዋል።

በጉብኝታቸው ወቅት ልዑካኑ የበሽታዎች ቅኝት ሥርዓት፣ የሪፖርት ፍሰት፣ የመረጃ ጥራት ማረጋገጥ፣ የመረጃ ዲጂታላይዜሽን፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) አጠቃቀም እና በመረጃ ላይ ተመስርቶ የሚሰጥ የውሳኔ አሰጣጥ ሥርዓትን በዝርዝር ተመልክተዋል።

በተጨማሪም በመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ አሃዶችና በክልሉ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሚሰጡ የPHEM አገልግሎቶችን በጥልቀት ገምግመዋል።

ልዑካኑ በጉብኝቱ የተመለከቱት የሥራ አፈጻጸም እጅግ አስደናቂ መሆኑን ገልጸው፣ በክልሉ ለሚከሰቱ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች የሚሰጠው ፈጣንና ተገቢ ምላሽ ከሀገራዊና ከዓለም አቀፍ መመዘኛዎች ጋር የተጣጣመ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ይህም የክልሉ የጤና ሥርዓት አቅም እያደገ መሆኑን የሚያሳይ አበረታችና ተስፋ ሰጪ ውጤት መሆኑን ገልጸዋል።

በተለይም የPHEM መረጃዎችን በDHIS2 ሥርዓት በወቅቱ የማስገባት አፈጻጸም ከ95 በመቶ በላይ የሪፖርት ሙሉነትና ወቅታዊነት ማስመዝገቡ፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተቀመጠው 80 በመቶ ዒላማ በእጅጉ የላቀ ውጤት መሆኑን በማድነቅ ክልሉ በዚህ ዘርፍ ለሌሎች ተሞክሮ የሚሆን አፈጻጸም ማሳየቱን ገልጸዋል።

ጉብኝቱ በሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ጤና አደጋ ቅኝትና ምላሽ ሥርዓት የተመዘገቡ ውጤቶችን በሀገር ብሎም በዓለም አቀፍ አጋሮች ዘንድ ለማስተዋወቅና የቀጣይ ትብብርን ለማጠናከር ጠቃሚ አጋጣሚ መሆኑ ተጠቁሟል።

በጉብኝቱ ማጠቃለያ ልዑካኑ የሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ላቦራቶሪን በመጎብኘት በክልሉ እየተሰጡ ያሉ የላቦራቶሪ አገልግሎቶችን፣ የምርመራ አቅምንና የጥራት ማረጋገጫ ሥርዓቶችን የተመለከቱ ስሆን በቀጣይነት አብሮ እንደሚሰሩ ቃል በመግባት ጉብኝታቸውን አጠናቀዋል።

የሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ሀምሌ 30/2018 ዓ/ም
ሀዋሳ

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
👇👇👇👇 ይመልከቱ

ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794
Web site: sphi.gov.et/emergency

Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=100083576610173

Telegram: https://t.me/c/1865772308/1

Email:- [email protected]

Photos from Sidama Public Health Institute Communication Affairs's post 03/08/2026

Today, the Sidama Public Health Institute (SPHI) hosted a research workshop focused on strengthening evidence-based health interventions across the region. In his opening remarks, SPHI Director General Dr. Damene Debalke emphasized that scientific research and data-driven evidence are vital for driving progress and improving healthcare performance.

The session featured presentations on completed research alongside upcoming initiatives. Senior researcher Dr. Amelo Bolka presented study findings on the readiness of health professionals for digital health implementation in public hospitals. Following this, senior researcher and statistician Dr. Dereje shared a comprehensive multi-year analysis of reportable disease profiles from 2013 to 2024, examining regional trends, spatial distributions, and case fatality rates.
Expanding on future health priorities, Mr. Aschalew Arega outlined a 2026 research proposal investigating primary healthcare facility readiness for routine immunization delivery beyond basic vaccine supply. The workshop concluded with an interactive discussion moderated by SPHI Vice Director General Mr. Ougamo Hanaga, where presenters addressed audience feedback and key questions.

በዛሬው ዕለት የሲዳማ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት (SPHI) በክልሉ ቅድሚያ የሚሰጣቸው የጤና ችግሮች ላይ ያተኮረ የጥናትና ምርምር ወርክሾፕ አካሂዷል። የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዳመነ ደባልቄ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት፣ በክልሉ የጤና አገልግሎትን ለማሻሻል ጠንካራ ሳይንሳዊ ምርምርና አስተማማኝ መረጃዎች ወሳኝ ናቸው። የሲዳማ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከተሰጡት ተልዕኮዎች አንዱ በጥናትና ምርምር የጤና ችግሮችን በመለየት ለፖሊሲ የሚሆን መረጃን ማቅረብ ስለሆነ በሚቀጥሉት ጊዜያትም ጥናትና ምርምርን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

በወርክሾፑ ላይ በተጠናቀቁ ጥናቶች የቀረቡ ሲሆን አንድ አዲስ የጥናት ፕሮፖዛል ቀርቧል፡፡ የኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር አመሎ ቦልካ የህዝብ ሆስፒታሎች ላይ የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች የዲጂታል ጤና ቴክኖሎጂዎችን ለመጠቀም ያላቸውን ዝግጁነት የሚያሳይ የጥናት ግኝት አቅርበዋል።

በመቀጠልም፣ ከፍተኛ ተመራማሪና ስታትስቲሻን ዶክተር ደረጀ ከ2013 እስከ 2024 (እ.ኤ.አ) በክልሉ የታዩ ዋና ዋና በሽታዎችን፣ የሥርጭት ሁኔታ እና፣ መልክአ-ምድራዊ ስርጭታቸውን እና የሞት ምጣኔያቸውን የሚያሳይ የጥናት ውጤት አቅርበዋል።

በቀጣይነት ሊሰራ የታቀደ ጥናትን ያቀረቡት ደግሞ ፣ አቶ አስቻለው አረጋ የጤና ተቋማት መደበኛ የክትባት አገልግሎት ለመስጠት ያላቸውን ዝግጁነት የሚመለከት የጥናት ፕሮፖዛል አቅርበዋል። ወርክሾፑ በኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር በአቶ ኡጋሞ ሃናጋ መሪነት በተካሄደ የውይይት መድረክ የተጠናቀቀ ሲሆን፣ ፕሬዘንተሽን ያቀረቡት ተመራማሪዎች ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽ ሰጥተዋል።

የሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ሀምሌ 27/2018 ዓ/ም
ሀዋሳ

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
👇👇👇👇 ይመልከቱ

ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794
Web site: sphi.gov.et/emergency

Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=100083576610173

Telegram: https://t.me/c/1865772308/1

Email:- [email protected]

Photos from Sidama Public Health Institute Communication Affairs's post 02/08/2026

የሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለ31ኛ ዙር በድግሪና በዲፕሎማ ፕሮግራም ያሰለጠናቸውን 830 ተማሪዎች አስመረቀ

የሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለ31ኛ ዙር በተለያዩ የጤና ሙያዎች በድግሪና በዲፕሎማ ያሰለጠናቸውን 830 ተማሪዎች በዛሬው ቀን አስመርቋል።

በምረቃ መርሀ ግብሩ ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው ተማሪዎችን ያስመረቁት የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ ባስተላለፉት መልዕክት አንጋፋው የሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዘንድሮ ለ31ኛ ዙር ተማሪዎቹን ሲያስመርቅ ከእውቀት ከልምዳቸው ሳይሰስቱ ይህን ሁሉ ባለሙያ ላፈሩ መምህራን፣ ከሌላቸው ላይ ቆርሰው ላስተማሩ ወላጆች ፣እንዲሁም ለኮሌጁ ማህበረሰብ በሙሉ እንኳን ለዚህች ልዩ ቀን አበቃችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

በሲዳማ ክልል ሞዴል የጤና ስርዓት ለመገንባት በሚደረገው ጉዞ የዕለቱ ተመራቂዎች ጉልህ ሚና ማበርከት እንደሚጠበቅባቸው ያሳሰቡት ሀላፊዋ፣ ለማህበረሰባቸሁ ጤና ዘብ በመቆም፣ ህዝባቸሁን በመልካም ስነምግባር፣ በርህራሄና በቅንነት በማገልገል ሙያዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ የአደራ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ወ/ሮ ትሁን ፈለቀ በበኩላቸው ከብዙ ውጣ ውረድ እና ልፋት በኋላ የድካማቸውን ፍሬ ለማየት ለተገኙ ተመራቂዎችና ወላጆቻቸው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በ1972 ዓ.ም በጤና ረዳትነት ተማሪዎችን በማስተማር የጀመረው ይህ ኮሌጅ በአሁኑ ሰዓት በ6 የድግሪና በ7 የዲፕሎማ ፕሮግራም ተማሪዎችን ተቀብሎ በማሰልጠን በስነምግባር የታነፁ ብቁና ርህራሄን የተላበሱ ባለሙያዎችን በጥራት በማሰልጠን የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እየተወጣ የሚገኝ ተቋም መሆኑንም ወ/ሮ ትሁን ገልፀዋል።

ከጊዜ ወደ ጊዜ የኮሌጁን የመማር ማስተማር ሂደት ለማሻሻልና ፅዱና ምቹ አካባቢን ለመፍጠር በተሰራው ስራ ተማሪዎች እየተዝናኑ የሚያጠኑበት ስፍራ በማመቻቸት፣ የኮሌጁን አገልግሎት በቴክኖሎጂ በማዘመን እና በተለያዩ የሪፎርም ስራዎችና የማህበረሰብ አገልግሎት የተጀመረው ሥራ ውጤት እያመጣ መሆኑን ወ/ሮ ትሁን ተናግረዋል።

ዲኗ አክለውም የጤና ሙያ በገንዘብ የማይተመንና ድንበር የሌለው በመሆኑ የዕለቱ ተመራቂዎች በተመደቡበት የሙያ መስክ በትጋትና በአገልጋይነት መንፈስ ሊሰሩ እንደሚገባም አሳስበዋል።

የሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ሀምሌ 26/2018 ዓ/ም
ሀዋሳ

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
👇👇👇👇 ይመልከቱ

ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794
Web site: sphi.gov.et/emergency

Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=100083576610173

Telegram: https://t.me/c/1865772308/1

Email:- [email protected]

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Awassa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Address


Awassa