Abem Primary Hospital
we care for your better health.
ቀላል ነው ብለው አንዳይዘናጉ!
ጀምረናል!
12/05/2026
የታካሚዎችን ጤንነት ለመጠበቅ ሌት ተቀን ለምትለፉ፣ የርህራሄና የጥንካሬ ተምሳሌት ለሆናችሁ ነርሶቻችን በሙሉ፤ መልካም የነርሶች ቀን እንዲሆንላችሁ እንመኛለን! 💙🩺
አቤም የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
ለጤናዎ ቅድሚያ እንሰጣለን!"
ሁልግዜም ለጤናዎ ቅድሚያ እንሰጣለን!
01/05/2026
የተወደዳችሁና የተከበራችሁ የአቤም የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሰራተኞች፣
እንኳን ለዓለም የሰራተኞች ቀን በሰላም አደረሳችሁ!
የሰው ልጅ ጤናን ለመጠበቅና ህይወትን ለማትረፍ ቀንና ሌሊት በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት ለምታደርጉት የማያቋርጥ ጥረት የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
ለሙያቸው የደከሙና የለፉ ባለሙያዎችን የምናከብርበት ይህ ልዩ ቀን ለሁላችንም የደስታ ቀን ይሁንልን።
25/04/2026
🌍 ዓለም አቀፍ የወባ ቀን | ሚያዝያ 17 🦟
ወባ ገዳይ ቢሆንም፣ በጋራ ጥረት ልናሸንፈው የምንችለው በሽታ ነው! ዛሬ ይህንን ቀን ስናስብ፣ እራሳችንን እና ማህበረሰባችንን ለመጠበቅ ቃል በመግባት ይሁን። 🤝
📉 ወባ በቁጥሮች፡ ያውቁ ኖሯል? 📊
🛑 249 ሚሊዮን — በየዓመቱ በዓለማችን በወባ በሽታ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር።
💔 600,000+ — በየዓመቱ በበሽታው ምክንያት ሕይወታቸውን የሚያጡ ወገኖቻችን።
🌍 95% — በዓለም ላይ ካለው የወባ ስርጭት እና ሞት ውስጥ የአፍሪካ ድርሻ።
👼 80% — በበሽታው ከሚሞቱት ውስጥ አብዛኞቹ ከ5 ዓመት በታች ያሉ ህጻናት ናቸው።
🛡️ መከላከያ መንገዶች፡ ምን እናድርግ? 💡
1️⃣ በአጎበር ስር መተኛት 🛌፦ ሁልጊዜ ማታ ማታ በኬሚካል የተነከረ አጎበርን በአግባቡ በመጠቀም ትንኞችን ይከላከሉ። 2️⃣ አካባቢን ማጽዳት 🧹፦ በቤትዎ ዙሪያ የሚገኙ የውሃ ማጠራቀሚያዎችን፣ ኩሬዎችን እና ቁጥቋጦዎችን በማስወገድ የትንኝ መራቢያ ቦታዎችን ያጥፉ። 3️⃣ አፋጣኝ ምርመራ 🏥፦ የትኩሳት፣ የብርድ ብርድ ማለት ወይም የራስ ምታት ምልክቶች ሲታዩ ሳይዘገዩ ወደ ህክምና ተቋም ይሂዱ።
📢 የእርስዎ ድርሻ ምንድነው? መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ Share በማድረግ ህይወትን ይታደጉ! 🔄
ሁልግዜም ለጤናዎ ቅድሚያ እንሰጣለን!
አቤም የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
🇪🇹✨
በስፔሻሊስት ሀኪሞች የታገዘ የቀዶ ህክምና አገልግሎት- ከአቤም ሆስፒታል!
እንኳን አደረሳችሁ!... መልካም በዓል!
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
ሀዋሳ ሰፈረ ሰላም ትሩፋት መብራቱ ጋር እንገኛለን ። Hawassa
Awassa
84