Satil card
እሯጭን የሚመለከተው ባየኖር አይሮጥም ነበር
12/08/2026
ሶስት ወጣቶች… ሶስት ህልሞች… ሶስት ቤተሰቦች የተሰበሩበት አሳዛኝ ክስተት
ከቤታቸው የወጡት እነዚህ ሶስት ወጣቶች እንደ ሌሎች ወጣቶች ህይወታቸውን ለመገንባት፣ ቤተሰባቸውን ለመርዳትና የተሻለ ነገን ለማየት ህልም ነበራቸው። ዛሬ ግን እነዚያ ህልሞች በጥ ይት ተቀጩ።
በማህበራዊ ገጾች እየተሰራጨ ባለው መረጃ መሰረት፣ ሶስቱ ወጣቶች በህዝብ አውቶብስ ሲጓዙ ከመኪናው አስወርደው “ፋኖ ናችሁ” በሚል ጥርጣሬ ተገ ድለዋል።
ነገር ግን ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው ነገር ፤ የሰው ልጅ ህይወት እንዴት ይህን ያህል ቀላል ሊሆን ቻለ?
እነዚህን ልጆች ለዘጠኝ ወር በማህፀናቸው የተሸከሙ እናቶች ነበሯቸው።
በድካም፣ በላብና በብዙ መስዋዕትነት ያሳደጓቸው አባቶች ነበሯቸው።
እህትና ወንድሞች፣ ጓደኞችና የሚወዷቸው ሰዎች ነበሯቸው።
ዛሬ ግን እነዚህ ቤተሰቦች ልጆቻቸውን ከፎቶ ብቻ እንዲያዩ ተደርገዋል። 💔
አንዲት እናት የልጇን የመጨረሻ ፎቶ ስትመለከት ምን ይሰማታል?
አንድ አባት በዓመታት የድካም ላቡን አፍስሶ ያሳደገውን ልጁን እንዲህ ሆኖ ሲመለከት ምን ይሰማዋል?
የልጃቸውን ድምፅ እንደገና መስማት ለማይችሉ ወላጆች የሚሰማቸውን ሀዘን የሚገልጽ ቃል ከየት ይገኛል? 😭
ሰው በማንነቱ፣ በጥርጣሬ ወይም በፖለቲካዊ ክስ ምክንያት ያለፍርድ ሊገደል አይገባም። የተጠረጠረ ሰው ካለ ህግ አለ፤ ምርመራ አለ፤ ፍርድ ቤት አለ።
ጥያቄያችን ፦ ህግ የት ነው? ፍትህስ የት ነው?
የሰው ህይወት ከማንኛውም ፖለቲካዊ አቋም በላይ ነው።
ግድያ ይቁም። ንፁሃን ከጥርጣሬ ይጠበቁ። ተጠያቂዎችም በህግ ፊት ይቅረቡ።
ለሶስቱ ወጣቶች ነፍስ እረፍትን፤
ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን፤
ለኢትዮጵያ ደግሞ ሰላምና ፍትህን እንመኝ። 🕯️🇪🇹
የእናት እንባ የሚያበቃበት፣ የአባት ልብ የሚረጋበት ቀን ይምጣ።
Via ዳኒ ታምራት
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
ደንገል በር
Bahir Dar