Abu amiralmuminin
Support macro business
ሱሉ አለን ነብይ 🍂 ﷺ 🍂
አሏሁመ ሰሊ ወሰሊም ዐላ ሰይዲና ወሐቢቢና ወሸፊዒና ሙሐመድ ወዓላ ዓሊሂ ወሰሕቢሂ አጀመዒን ።
06/09/2026
በዛሬው ዕለት በቤተል ሙጀመዑ ተቅዋ መስጂድ የቁርዓን ሂፍዝ ተማሪዎች በደማቅ ሁኔታ ተመርቀዋል። ለተመራቂዎችና ለተመራቂ ቤተሰቦች እንኳን ደስ ያላችሁ እያልኩ፤ ተመራቂ ተማሪዎች የተሸከማችሁትን አማና ትልቅነት ተረድታችሁ ጉዟችሁ የአስተውሎት እንዲሆን አደራ ለማለት እወዳለሁ።
06/09/2026
አፋልጉኝ
ስም- ዩኑስ ይማም ሙሀመድ
ቀደም ብሎ ይኖር ነበረው በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 ደሳለኝ ሰፈር ነበር።
በቅርቡ ለህክምና ወደ አዲስ አበባ መቶ ሽገር ሲቲ ልዩ ስሙ አንፎ ድልድይ አካባቢ ይገኝ የነበረ ሲሆን ሀምሌ 13 2018 ለህክምና በወጣበት አልተመለሰም።
በዕለቱ ለብሶ የነበር ጥቁር ጃኬትና ሰማያዊ ጅንስ ሱሪ ነዉ።
ወንድማችንን ያያችሁ ወይንም ያለበትን የምታውቁ ከታች በተቀመጡት ስልክ ቁጥሮች እንድታሳዉቁን በትህትና እንጠይቃለን፦ፈላጊ ቤተሰቦቹ
📲+251967143116
📲+251932913683
05/09/2026
በዳውሮ ዞን በጣለው ከባድ ዝናብ ህይወት ነጠቀ
05/09/2026
እቺ እናት ስሟ ዛቡ ሀሰን ወሎ ነች አዲስ አበባ ኮተቤ አከባቢ ቤት ጠፍቶባት ውጭ ስታድር አይተው ወደ ቤት ወስደዋታል 4ቀን ነው ከልጇ ቤት ነው ከግቢ ወጥታ ቤቱ ጠፍቷል።
ቤተሰቧ በዚህ ደውላቹ ውሰዷት 0910323467
ኢና ሊላሂ ወዒና ኢለይሂ ራጂዑን
የወንድሜ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ወላጅ እናት ወደ አኼራ ሄደዋል::
የእናታችን ስርዓተ ቀብርም ነገ ቅዳሜ ከዝሁር ሰላት ቡኃላ ሰናተል ጀናዛ ተሰግዶባቸው በኮልፌ የሙስሊሞች መካነ መቃብር የሚፈፀም ይሆናል
አላህ ይዘንላቸው፣ ማረፊያቸውንም በጀነተል ፊርዶስ ያድርግላቸው
ለኡስታዝ አህመዲን ጀበል እና ለመላው ቤተሰቦቹ አላህ ሰብሩን ይወፍቃቸው
04/09/2026
ይህ የተወዳጁ ሸይኽ ኢብራሂም ሲራጅ (ረሒመሁላህ) ይፋዊ የፌስቡክ ገጽ ነው።
አንጋፋው አፍሪካ ቲቪ የሸይኹን የዳዕዋና የትምህርት ሥራዎች በስፋት ተደራሽ ለማድረግ በስማቸው የሞባይል መተግበሪያ (App) ማስመረቁ ይታወሳል።
አሁን ደግሞ የሸይኹ ትምህርቶች ይበልጥ ለሕዝበ ሙስሊሙ እንዲደርሱ በማሰብ እነዚህን ይፋዊ የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮች አዘጋጅቶ ወደ እናንተ አድርሷል።
https://www.facebook.com/share/1DVcveQkSC/?mibextid=wwXIfr
ገጹን ይከተሉ፤ ለሌሎችም በማጋራት የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ!
Category
Telephone
Website
Address
Butajira
WORABE