Dire Transport

Dire Transport

Share

ይህ የፌስቡክ ገጽ የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ድሬዳዋ

08/11/2025

Terima kasih kepada pengikut terbaru saya! Senang Anda bergabung! Endalamawe Ayalewe

Photos from Dire Transport's post 12/03/2024

挺熱鬧,有緣再來

please - YouTube 09/06/2023

Please subscribe my chanell

please - YouTube Saya di sini ingin berbagi pengalaman tentang aplikasi yang pernah saya mainkan dan terbukti membayar ya , bukan sekedar info info tetapi saya juga menjalank...

Photos from Dire Transport's post 28/07/2022

በድሬደዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አመራርና አባላት እንደሁም በድሬደዋ አስተዳደር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ ባለስልጣን ሰራተኞች እና በስሩ ሚገኙ ማሀበራት እንደሁም የሌሊት ታክሲ አሽከርካሪዎች በአለም አትሌቲክስ ሻንፒያና ከአለም 2ኛ ከአፍሪካ 1ኛ ደረጃን በመያዝ ላጠናቀቀው የኢትዮጵያ አትሌክስ ቡድን ምስጋና መርሀግብር አካሂደዋል፡፡
ዛሬ ከ ቀኑ9:00 በድሬደዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ፊት ለፊት በሚገኘው መንገድ ላይ ክቡር ኮሚሽነር አለሙ መግራ እንዲሁም የድሬደዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አመራሮችና አባላት እና ከድሬደዋ አስተዳደር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ ባለስልጣን እና በስሩ ከሚገኙ ማህበራት ከሌሊት ታክሲ አሽከርካሪ ማህበራት የተውጣጡ ተሳታፊዎች በስነስረአቱ በመገኘት ለአትሌቲክስ ቡድኑ ያላቸውን ክብር እና ፍቅር አሳይተዋል፡፡
በስነስረአቱ ላይ የድሬደዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር አለሙ መግራ እንደተኛገሩት ሁላችንም ቢሆን የመመሰጋገን ባህላችን ሊጎለብት እንደሚገባ ጠቁመው ከሁሉ በላይ በአለም መድረክ እንድንኮራ ያደረጉንን አትሌቶቻችንን ለማመስገን እወዳለሁ ብለዋል፡፡
እኛም በየተሰማራንበት መስክ መመሰጋገናችን ለስራችን ውጤታማ ያደርገናል በመሆኑም መመሰጋገንን ባህል እናድርግ ብለዋል፡፡
በስነስረአቱ ላይም ድል ለሀገራቸው ማስመዝገብ ለቻሉት ለጀግኖች አትሌቶቻችን ለ2 ደቂቃ በጭብጨባና የተሽከርካሪ ጥሩንባ በማሰማት ክብርን አድናቆትና ፍቅራቸውን በመግለፅ ተሳታፊዎቹ ስነስረአቱን አድምቀውታል፡፡
በዘውገ አውላቸው

Photos from Dire Transport's post 28/07/2022

በአትሌቶቻችን በተገኘው ድል ኮርተናል ለቀጣይ ተግባራችንም ድሉ ስንቅ ሆኖናል!!
ዛሬ የሀገር አሸናፊነት የአብሮ መስራት የህብረት እና አንድነት ውጤታማነትን በአትሌቶቻችን ድል አይተናል፡፡
በአለም መድረክ ከፍ አድርገውናልና እናመሰግናቸዋለን፡፡
እኛም በተለይ አሁን ላይ ፈተና እየሆነብን ያለውን እና በርካቶችን እየነጠቀን ያለውን የትራፊክ አደጋ በቃ ብለን በህብረት እንነሳ በአዲስ አመት በጋራ ሰርተን የወገን በትራፊክ አደጋ መሞት ይብቃ እንበል ምክንያቱም የህብረት የአንድነትን ውጤት ከጀግኖቻችን ተምረናል እና እናመሰግናለን በድላችሁ ኮርተናል ፡፡
ክብርት ወ/ሮ ሰአዳ አዋሌ
የድሬደዋ አስተዳደር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ ባለስልጣን
ስራ አስኪያጅ

Photos from Dire Transport's post 27/07/2022

የሞተር አልባ ትራንስፖርት ስትራቴጂን ተግባራዊ ለማድረግ የሁሉንም ባለድረሻ አካላት የጋራ ስራ የሚጠይቅ እንደሆነ ተጠቆመ፤
****
የሞተር አልባ ትራንስፖርትን በከተሞች ለማስፋፋት የሚያግዝ ስልጠና ከክልልና ከተማ አስተዳደሮች ለተውጣጡ የዘርፉ አካላት ተሰጥቷል፡፡ በስልጠናው ላይ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚንስትር ዴኤታ ክቡር አቶ በረኦ ሀሰን የሞተር አልባ ትራንስፖርት ስትራቴጂን ተግባራዊ ለማድረግ የሁሉንም ባለድረሻ አካላት የጋራ ስራ የሚጠይቅ እንደሆነ ገለፀዋል፡፡
የሞተር አልባ ትራንስፖርት ካለው ሀገራዊ ጠቀሜታ አኳያ በ10 አመት የልማት እቀድ ውስጥ ትልቅ ቦታ ይዞ የሚገኝ እንደሆነ የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ በረኦ በአሁኑ ሠዓት በሀገራችን የተለያዩ ከተሞች እየተስፋፋ መሆኑንና የህብረተሰቡን የትራንስፖርት ፍላጎት ለማሟላት ስትራቴጂውን ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡
የሞተር አልባ ትንስፖርት የበካይ ጋዝ ልቀትን የሚያሥቀር በመሆኑ ከአካባቢ ፖሊሲ ጋር የተጣጣመ ከመሆኑም በተጨማሪ ምቹና ቀላል፣ የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ከፍተኛ ሚና ያለውና ለህብረተቡ በቀላሉ ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል በመሆኑ ተመራጭ እንደሆነ ገልፀው በ2015 በጀት አመት ዘርፉን ለማስፋፋት ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን ብለዋል፡፡
በትላልቅ ከተሞች በቋሚነት የህብረተሰቡን ግንዛቤ የማሳደግ ስራ መስራት እንደሚገባና ስትራቴጂውን ተግባራዊ ለማድረግ የመሰረት ልማት ግንባታ ላይ ትኩረት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ የመሰረተ ልማት ግንባታ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ በመሆኑ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎና የአጋር ተቋማት ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እነዳለበት በመድረኩ ተገልጿል፡፡
በሀገራችን በ10 ዓመቱ መሪ የትራንስፖርት ዕቅድ በ69 ከተሞች እንዲሁም በ2015 በጀት አመት ደግሞ በ21 ከተሞች ላይ የሞተር አልባ ትራንስፖትን ተግባራዊ ለማድረግ ታቅዷል፡፡ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ለተግባራዊነቱ መዋቅራዊ አደረጃጀታቸውን ማስተካከልና የሰው ኃይል ማሟላት ላይ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚኖርባቸው ተነግሯል፡፡
ስልጠናው ለሁለት ቀናት የተዘጋጀ ሲሆን በመስክ ምልከታ የታገዘና ሞዴል የመንገድ ላይ ዲዛይኖች የተብራሩበት፣ብሔራዊ የሞተር አልባ ትራንስፖርት ስትራቴጂ ማስፈፀሚያ እቅድ ላይ ግንዛቤ የተፈጠረበት እንዲሁም ስተራቴጂውን ተግባራዊ ለማድረግ የባለድርሻ አካላት ሚና እና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን ከክልልና ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ፣ ከየከተሞች ትራንስፖርት ቢሮዎችና ከንቲባ ጽ/ቤቶች የተወከሉ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡
ስልጠው የተሻለ ተሞክሮ ካላቸው ከተሞች ልምድ ለመውሰድና ለመማር እድል የሚፈጥር እንደሆነም ተመላክቷል፡፡
የስልጠና መድረኩን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር፣ የዓለም ዓቀፉ የትራንስፖርትና የልማት ፖሊሲ ኢንስቲትት /ITDP/ እና ዩኤን ሀቢታት /NU Habitat/ በትብብር ያዘጋጁት ሲሆን የሞተር አልባ ትራንስፖርትን ለማስፋፋት በሚሰሩ በርካታ ስራዎች ላይ ድጋፍና ትብብር እያደረጉ እንደሆነም ተገልጿል፡፡

26/07/2022

ድሬ በበአሉ ከታዘብናቸው መልካም ተግባራት ለመሰል ባለ ቅን ልቦች ምስጋናችን ይድረስ!!

Photos from Dire Transport's post 26/07/2022

እንኳን ለቁልቢ ገብርኤል የንግስ በአል አደረሳችሁ!!
የትራንስፖርት የቁጥጥር ባለሙያዎች እና ትራፊኮቻችን በበአሉ መንገዶች እንዳይጨናነቁ በማስተናበር ተግባር ላይ

Photos from Dire Transport's post 25/07/2022

ወቅቱ ዝናባማ በመሆኑ እና የተሽከርካሪ ፍሰቱ ስለሚጨምር አመታዊውን የቁልቢ ገብርኤል የንግስ በአል ለማክበር የሚመጡ እንግዶችም ሆነ ሌሎች አሽከርካሪዎች የትራፊክ አደጋዎች እንዳይከሰቱ ሁሉም በጥንቃቄ እና ፍጥነትን በመቀነስ እንዲያሽከረክሩ ጥሪ ቀረበ፡፡
የድሬደዋ አስተዳደር ትራንፖርት እና ሎጂስቲክ ባለስልጣን እና በድሬደዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት አመታዊውን የቁልቢ ገብርኤል የንግስ በአል በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ እና የጥንቃቄ መልእክቶቻቸው አስተላልፈዋል፡፡
ድሬደዋ መንገዶቹዋ አመታዊውን የቁልቢ ገብርኤል የንግስ በአል ለማክበር ወደ ከተማዋ በመጡ እንግዶች ተሞልተዋል፡፡
ታዲያ ይህንኑ ተከትሎ ወቅቱም ዝናባማ እንደመሆኑ የትራፊክ አደጋ እንዳይከሰት የከተማዋ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ ባለስልጣን እና የትራፊክ ቁጥጥር ቡድኑ በጋራ የቁጥጥር እና የማስተናበር ስራን እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ ይህን በአል በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ያስተላለፉት በድሬደዋ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ ባለስልጣን መንገድ ትራፊክ ደህንነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ም/ኮማንደር ጉልማ ታዬ ምእመናኑ በአሉን ሲያከብር ሊደርስ ከሚችል አደጋ ራሱን እንዲጠብቅ ጥሪ አስተላልፈው ለዚህም በመሰልበአላት ወቅት በከተማዋ የተሽከርካሪ ፍሰቱ እንደሚጨምር ከግምት በማስገባት ከትራንስፖርት እና ከትራፊክ አካላት የተውጣጣ ቡድን ከከተማዋ መግቢያ ደንገጎ ጀምሮ የከተማዋን ዋና ዋና መንገድ በመያዝ አደጋዎች እንዳይከሰቱ የቁጥጥር እና ክትትል ስራን እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
በተጨማሪም በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በድምፅ እና በበራሪ ፀሁፍ ግንዛቤ በመፍጠር በማስተማር ላይ እንገኛለንም ብለዋል፡፡
የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅ/መምሪያ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሻለቃ ይሄነው ሽፈራው በበኩላቸው በኦርቶዶክስ ተዋድ እምነት ተከታዮች ዘንድ ሚከበረውን አመታዊ የቁልቢ ገብርኤል የንግስ በአል በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን እንደከተማችን በርካታ ተሽከርካሪዎች ወደ ከተማዋ በመግባታቸው የመንገድ መጨናነቅ እንዳይኖርም ሆነ አደጋዎች እንዳይከሰቱ ሰፊ የጥንቃቄ ስራዎችን ለመስራት አባላት በተጠንቀቅ ከዋዜማው ጀምሮ እንደሚቆሙ ነው ያስታወቁት፡፡ በተለይ በመሰል በአላት ወቅት መጠጥ ጠጥቶ ከማሽከርከር መቆጠብ ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡
ኃላፊዎቹ የህግ አካላት ብቻ ተግባር ውጤት ሊያመጣ አይችልም ያሉ ሰሆን በተለይ ደግሞ አሽከርካሪዎች እና እግረኞች ህግን በማክበር በመንቀሳቀስ እና ከፍጥነት በላይ ባለማሽከርከር ነገን በጤና እንዲሻገሩ ጥሪ እናቀርባለን ብለዋል፡፡

Photos from Dire Transport's post 25/07/2022

ማሳሰቢያ
ለድሬደዋ አስተዳደር ታክሲ አሽከርካሪዎች እና ተገልጋዮች በሙሉ
በቅርቡ በአንዳንድ የታክሲ መዳረሻ መስመሮች ላይ ማሻሻያ መደረጉን ተከትሎ አብላጫው አሽከርካሪ በተቀመጠለት መስመር እና ታሪፍ ማህበረሰቡን በማገልገል ላይ ይገኛል ለዚህም ለመሰል ባለንብረቶች እና አሽከርካሪዎች ምስጋናችንን ለመግለፅ እንወዳለን፡፡ ይሁንና ጥቂት አሽከርካሪች ከሰሞኑ የተደረገውን ክለሳ አስመልክተው በታሪፍ አለመስራትን ጨምሮ በህብረተሰቡ ላይ ብዥታ በመፍጠር ላይ ይገኛሉ በመሆኑም መሰል አሽከርካሪዎችን በሚደርሰን መረጃ እርምጃ እየወሰድን ስንገኝ በታሪፉ አሁንም መሰል ችግሮች ሲያጋጥሙ ማህበረሰቡ ለተቆጣጣሪዎች አልያም ለትራፊክ ፖሊሶቻችን እንዲያሳውቅ ጥሪ እናቀርባለን፡፡
በነባሩ እና ማሻሻያ ያልተደረገባቸው መስመሮች እና አዲሶቹን ከዚህ በታች እናሳውቃለን
ድሬደዋ አስተዳደር የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ ባለስልጣን
የህዝብ እና ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት አደረጃጀት ስምሪት ዳይሬክቶሬት

Photos from Dire Transport's post 25/07/2022

እንኳን ደስ ያላችሁ!!
በድሬደዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በከፍተኛ የማእረግ እድገት ለተመረቃችሁ ሁሉ በድጋሚ እንኳን ደስ ያላችሁ ደስ ያለን ለማለት እወዳለሁ። በመምሪያው ክቡር ኮሚሽነር አለሙን ጨምሮ በተለያየ የሙያ ክፍል ያሉ አመራሮች እና ባለሙያዎች ለባለስልጣን መስሪያቤቱ መለወጥ እና ማደግ ለምታደርጉት ጥረት እያመሰገንኩ ይህ ህብረታችን ተጠናክሮ በቀጣይም ለተሻለ ለውጥ ለምናደርገው ትጋት የዛሬው የማእረግ በእጅጉ ያበረታችኋል እና ለናንተ የተሰማኝን ደስታ በራሴ እና በተቋሜ ስም ለመግለፅ እወዳለሁ።
ክብርት ወ/ሮ ሰአዳ አዋሌ
በድሬደዋ አስተዳደር የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ ባለስልጣን ስራ አስኪያጅ

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Dire Dawa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Sabiyan
Dire Dawa
1254