Caydaruus
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Caydaruus, Health/Beauty, Jijiga.
02/04/2025
01/04/2025
የኢድ አልፈጥር ረመዳን በዓልን አስመልክቶ በአዲስ አበባ ስታዲዮም የተደረገው የኢድ ሶላት ኃይማኖታዊ ስርዓቱን በጠበቀና በድምቀት መከበሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
***
1446ኛው የኢድ አልፈጥር ረመዳን በዓል በድምቀት እየተከበረ ይገኛል፡፡ በዓሉን አስመልክቶ በርካታ የእምነቱ ተከታዮች በአዲስ አበባ ስታዲየም እና በስታዲየሙ አካባቢ በሚገኙ አውራ ጎዳናዎች እንዲሁም በልዩ ልዩ መስኪዶች የደረጉት የኢድ ሶላት ኃይማኖታዊ ስርዓቱን ጠብቆ በድምቀትና በሠላም መከናወኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ ከኢድ ሶላቱ ጋር ተያይዞ ለተሽከርካሪ ዝግ የነበሩ መንገዶች ተከፍተው አገልግሎት እየሰጡ መሆኑንም ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል፡፡
የኢድ ሶላቱ በታቀደው መሰረት በሠላም እንዲከናወን ላደረጉ ታዳሚዎች፣ የኃይማኖቱ መሪዎች፣ ከፀጥታ አካሉ ጎን በመቆም የማስተባበር ስራ ሲሰሩ ለነበሩ ወጣቶችና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ ለመላው የፀጥታ አካላት የአዲስ አበባ ፖሊስ ምስጋናውን አቅርቦ ለመላው የእምነቱ ተከታዮች በዓሉ የፍቅርና የሠላም እንዲሆንላቸው መልካም ምኞቱን በድጋሚ ገልጿል፡፡
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!”
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Jijiga