nuredin al-mesqany

nuredin al-mesqany

Share

it's me nuredin.I am psychiatric proffesional at somali region fiq hospital.thankyou for following me

20/10/2023

እራስን ማጥፋት!!

ሰሞኑ አንዲት ኢትዮፕያዊት እራስዋን ካጠፋች በሁአላ የብዙ ሰው መነጋገርያ ሆናለች:: አንድ ሰው አራሱን ሊያጠፋ በአንድ ቀን እንደማይነሳ ጥናቶች ያመለክታሉ:: ከዛ በፊት በተደጋጋሚ እራስን የማጥፋት ሃሳብ ማሰብ ፣ ከዝያም ይህንን ሃሳብ እንደቀልድም ቢሆን ማንጸባረቅ ፣ ቀድመው ይመጡና በመቀጠል ቤተሰብና ጓደኞችን መሰናበት ፣ እራስን ማጥፍያ መንገዶችን መምረጥ እና ማዘጋጀት ፣ ከዝያም መሞከር::
እነዚህ ሂደቶች ብዙ የቅርብ ሰዎቻችን ከማጣታችን በፊት የምናስተውላቸው ነገሮች ናቸው::

ስለዚህ እነዚህ ምልክቶች በሰዎች ላይ በምናይ ጊዜ በመጀመርያ ለዚህ ያደረሰአቸው ችግር ምን እንደሆን አውቀን ለመረዳት እና ችግራቸውንም ለመረዳት መሞከር ከዝያ በመቀጠል በፍጥነት የህክምና አገልግሎት ወደሚገኝበት ማድረስ ከኛ የጠበቃል::

አስተውሉ እራስን የማጥፋት ሃሳብ ወይም ሙከራ አንዱ የአዕምሮ ህመሞች ዋና እና አስደንጋጭ ምልክት ነው::
Follow nuredin al-mesqany

21/07/2023

ጉራጌ ክልል ቢሆን ባይሆን..ምስራቅ ጉራጌ ዞን ቢመሰረት ባይመሰረት ...I don't care

21/07/2023
20/07/2023

ለኮምቦልቻ ሙስሊሞች
~
የአሕባሽ ቡድን የኮምቦልቻን ገፅታ ክፉኛ አጠልሽቷል። ይህንን መርዝ ነቅሎ በመጣል ላይ ያልተገደበ ርብርብ ማድረግ ያስፈልጋል። የዚህ ቆሻሻ አንጃ ተውሳክ የበከላቸውን ወይም ለጥርጣሬ ያጋለጣቸውን ወንድሞች ባልተቆጠበ ትምህርት ማከም ይገባል። መስጂዶችን በሒክማና በትጋት በመጠቀም ህብረተሰቡን ማንቃት ይገባል።
ይሄ ቡድን ጎዳና ላይ ወጥቶ ባደባባይ ሙስሊሞችን ከእስልምና እያወጣ እያወጀ ዞሮ ሌሎችን በኸዋ -ሪጅነት የሚወነጅል አይኑን በጨው ያጠበ አንጃ ነው። ይሄ ቡድን ከአመት በፊት ወሎ ተሁለደሬ ላይ መስጂድ አቃጥሎ ሲጨፍር ነበር። ባለፈው አመት ሆለታ ላይ የመስጂድ ኢማም ገድሏል። ሰሞኑን በኮምቦልቻ መስጂድ ውስጥ ኢማም ደብድቧል። ሙስሊሞችን ለማስመታት እነ አባይ ፀሐዬን ሲቀሰቅስ የነበረ ቡድን ነው። ይሄ ቀብር ለቀብር የሚልከስከስ ሙታን አምላኪ ነቀ'ርሳ ቡድን በአመለካከት የማይመስሉትን ሙስሊሞች ነፍስ ለመንጠቅ የማያመነታ የለየለት ፅንፈኛ አንጃ ነው። ሙስሊሞችን የእሳት፣ እነ መለስ ዜናዊን ግን የጀነት የሚያደርግ ለጥቅሙ ሲል የትኛውንም ቅጥፈት ለመናገርም ለመፈፀምም አይኑን የማያሸ አው'ሬ ስለሆነ ስሩን በመንቀል ላይ ጠንካራ ስራ መስራት ያስፈልጋል።

Ibnu Munewor
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

20/07/2023

የአህባሾች ቅዠት በጀግናው Ibnu munewor ሲፈታ-----------

16/07/2023

ከመጠን በላይ የመነቃቃትና ትኩረት የማጣት ህመም ምንድን ነው?
ይህ በሽታ አንጎልን (አዕምሮን ) የሚያጠቃ ሆኖ የትኩረት ችሎታ ማጣትንና ከመጠን በላይ መነቃቃትን የሚያስከትል የአዕምሮ ህመም ነው፡፡ በሽታው በህፃንነት ጊዜ በብዛት የሚታይ ቢሆንም የሚያጠቃው ህፃናትን ብቻ አይደለም፡፡ በቂ የህክምና ክትትል ካልተደረገለት ይህ በሽታ እስከ ወጣትነትና የጎልማሳነት ጊዜ ድረስ አብሮ ሊኖር ይችላል፡፡
የዚህ በሽታ መንስኤ ምንድነው?
የሚከተሉት ሁኔታዎች ትኩረት የማጣትና ከመጠን በላይ የመነቃቃት እድልን የሚያሰፉ ሁኔታዎች እንደሆኑ ይታሰባሉ፡፡
• በዘር የመጣ ከሆነ እና
• እናቶች በእርግዝና ወቅት ሲጋራ ያጨሱና አልኮል ይጠጡ ከነበረ በልጁ ላይ የመከሰት ዕድሉ ይጨምራል፡፡
የበሽታው አይነቶቹ እና ምልክቶቹ ምን ምን ናቸው?
ይህ የአዕምሮ እክል ሶስት አይነቶች ሲኖሩት ሶስቱም የየራሳቸው ምልክቶች አሏቸው፡-
1. ትኩረት ማጣት የሚስተዋልበት እክል
• ለጥቃቅን መረጃዎች ትኩረት መስጠት አለመቻል ወይም በትምህርት ነክ ወይም በሌሎች ስራዎች ላይ በግዴለሽነት ተራ ስህተቶችን መፈፀም
• በአንድ ስራ ወይም ጨዋታ ላይ ማተኮር አለመቻል
• በሚያናግሯቸው ወቅት የሚያዳምጡ አለመምሰል
• ትእዛዝን እስከ መጨረሻው አለመከተልና የትምህርት፣ የቤት ውስጥ ወይም የስራ ቦታ ሃላፊነትን አለመወጣት
• ስራዎችን ማቀናጀት አለመቻል
• የተራዘመ ትኩረትን በሚጠይቁ ስራዎች ላይ አለመሳተፍ፣ እንደዚህ ያሉ ስራዎችን መጥላት ወይም ዳተኛ መሆን
• ለስራ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን መርሳት
• በቀላሉ ትኩረት ማጣት
• በእለት ተእለት ክንዋኔዎቻቸው ላይ ዝንጉ መሆን፡፡
2.ከመጠን በላይ መነቃቃት የሚስተዋልበት እክል
• እጅን ወይም እግርን ሳያውቁ በብዛት ማወዛወዝ ወይም በተቀመጡበት መቁነጥነጥ
• መቀመጥ ባለባቸው ጊዜ ተቀምጦ መቆየት አለመቻል
• ረጋ ማለት በሚጠበቅባቸው አጋጣሚዎች ከልክ በላይ መቁነጥነጥና እርጋታ ማጣት
• ረጋ ብሎ መዝናናት አለመቻል
• ከመጠን በላይ ማውራት
• ጥያቄ በሚቀርብላቸው ጊዜ ሰምተው ሳይጨርሱ መልስ መስጠት
• ተራ መጠበቅ አለመቻል
• ሌሎች ሰዎችን ማወክ ወይም ማደናቀፍ
3.ከላይ የተጠቀሱት ሁለቱን ያጣመረ እክል
የዚህ ዓይነቱ እክል ምልክቶች ከላይ በተራ ቁጥር1 እና 2 ስር የተገለፁት በሙሉ ወይም በከፊል ናቸው፡፡
ማስታወሻ፡-ሁሉም ህፃናት ትኩረት ሊያጡ ወይም ከመጠን በላይ ሊነቃቁ ወይም ደመነፍሳዊ ሊሆኑ መቻላቸው የሚታወቅ ነው፡፡ ነገር ግን ሆኖም ትኩረት የሚያሳጣ፣ ከመጠን በላይ የሚያነቃቃ/ኤዲ ኤችኤ/ያለባቸው ህፃናት ላይ እነዚህ ምልክቶች በተደጋጋሚ እና በከፍተኛ ደረጃ የሚታዩ ናቸው፡፡
በሽታውን እንዴት መቆጣጠር ይቻላል?
• የስነ ልቦና ህክምና፤ትምህርት እና ሥልጠና ማግኘት
• ከወላጆች፣አሳዳጊዎችና መምህራኖች ክትትል እና መመሪያ ማግኘት
• የተረጋጋና አስደሳች ህይወት እንዲኖሩ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፡፡
ሙያዊ ህክምና እና እገዛ ማግኘት የሚገባው መቼ ነው?
አንድ ልጅ ከመጠን በላይ የመቅበዝበዝና ትኩረት የማጣት እክል ካለበትና የትምህርት አቀባበል ችግር ካለበት ወይም ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች በተደጋጋሚ በእለታዊ እንቅስቃሴዎቹ ውስጥ የሚታዩበት ከሆነ ሙያዊ ድጋፍ ለማግኘት ወደ ሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች መውሰድና የህክምና እርዳታ ማግኘት ይኖርበታል፡፡

15/07/2023

የኑሮ ነገር 1999 እስካሁን ግን እየኖሩ ይሆን እነዚህ ሰዎች??

14/07/2023

አላህ ሆይ! 💚
ወደሷ እንደምትመልሰው እርግጠኛ ሆና የሙሳ እናት ልጇን ባሕር ላይ የጣለችበትን የቂን(እምነት) ለኔም ረዝቀኝ🤲

13/07/2023

አህባሾች አላህ በቦታ የለም ቢሉም እንኳን ቁርኣን ሲያነቡ በግዳቸው ٱلرَّحۡمَٰنُ عَلَى ٱلۡعَرۡشِ ٱسۡتَوَىٰ "አረሕማን ከዐርሹ ላይ ከፍ አለ" ይላሉ። አላህ ሲያስገድድ እንዲህ ነው።

12/07/2023

አንድ መልእክት ለዱዓት
~
በደዕዋ ላይ ላይ ከሚታዩ መሰናክሎች ውስጥ አንዱ የዱዓት አለመጣጣም ነው። ለዚህ አለመጣጣም ቀዳማዊ ምክንያት የዱዓት ነፍሲያን መከተል ነው። ለሌላ መትረፋቸው ቀርቶ ጭራሽ ሸክም መሆን። ወንድሜ! ይሄ ህዝብ ሞልቶ የተትረፈረፈ ብዙ አጀንዳ አለው። የግላችንን አመል አደባባይ እያመጣን ሌላ በሽታ አንደርብበት።
በሚያሳዝን ሁኔታ ግን አብዛኞቻችን በነፍሲያ የተተበተብን ሆነናል። "ህዝባችን ደዕዋ የተጠማ ነው፣ ደዕዋውን ለማሰናከል አድብተው የሚጠብቁ ሴረኞች ስላሉ በጥንቃቄ ተጓዙ" የሚል አደራ የተሰጣቸው ኡስታዞች አመላቸውን መግራትን እንደ ሸንፈት፣ የሌሎችን ጥንቃቄ እንደ ፍርሃት እየቆጠሩ ጅምር ስራዎችን በታትነው፣ ደዕዋውን አጠልሽተው ያርፋሉ። ብዙ ቦታዎች ላይ የሚያጋጥም ፈተና ነው። በሚያሳዝን ሁኔታ በእንዲህ አይነት ሁኔታ ላይ ከሚታዩት ውስጥ ከፊሎቹ ከእድሜ አንፃር የወጣትነትን ግለት የተሻግሩ መሆናቸው ነው።
በሌላ በኩል ደግሞ በስልት ራስን መኮፈስ፣ ራስን ልዩ አድርጎ ማየት፣ ሌሎችን መናቅና ማጣጣል፣ ሌሎችን በማጣጣል የራስን ስም መገንባት ላይ መጠመድ ብዙዎቻችን ዘንድ ያለ በሽታ ነው። ወንድማለም! ራስህን ልዩ አድርገህ አትመልከት። የእውነት የደዕዋ ጉዳይ የሚያሳሳብህ ከሆንክ ደዕዋ ላይ ያሉ ወንድሞችህን እንደ አጋሮችህ፣ አጋዦችህ እንጂ እንደ ተቀናቃኝ ከመመልከት ውጣ። ሌሎችን በማጣጣል ራስን የመቆለል ቆሻ ሻ በሽታን ከልብህ አውጣ። ሁሌም ትህትናን ተላበስ። ራስህን ዝቅ አድርግ። በሆነ ነገር ከሌሎች እንደምትሻል ከተሰማህ ሌሎቹ በሌላ ነገር ካንተ እንደሚሻሉ አስብ። ሰበር ብትል የእውነትም አንተ ጋር የሌለ ብዙ መልካም ነገር ሌሎች ላይ ታገኛለህ። ራስህን በሚገባ ግራ።
በተለይ ክፍለ ሃገር ላይ ያላችሁ ዱዓቶች ከልብ አስቡበት። ደዕዋ ላይ ላሉ ወንድሞች ሞራል እንጂ ውጋት አንሁን። በዚህ ዘመን በደዕዋው ዘርፍ ላይ ያለው ምቀኝነትና ክፋት በዱንያ ጉዳዮች ላይ ከሚታየው በሽታ በጣም የራቀና የባሰ ነው። ይሄ ብንደብቀው እንኳ የማይደበቅ አሳፋሪ ግን በገሃድ የሚታይ ነውር ነው። በግል ጉዳይ በሆነ ወንድሙ ላይ ያቄመው ሁላ በደዕዋ ሽፋን ላንቃው እስኪበጠስ እየጮኸ ህዝብ ማደናገር በጣም የተለመደ ሆኗል። ወንድሜ በዚህ ዘመን ያለው እንቅፋት ብዛት በርብርብ ለመጋፈጥ እንኳ የሚፈትን ነው። ትብብሩ ቢቀር አንዱ ሌላውን ከደዕዋ መስክ ለማውጣት አለፍ ሲልም ለማጥፋት መነሳት ግን ለደዕዋው እዳ መሆን፣ ተያይዞ መክሰም ነው የሚያስከትለው። ከፍትጊያው መጨረሻ ደግሞ የሚያተርፈው ሌላ ነው። ስለዚህ ከወንድምህ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘህ ክፍተቶችን #እየተራረምክ ተደጋግፈህ ለመጓዝ ሞክር። ይሄ ካልሆነልህ ከነ ድክመቱ እያስታመሙ የሆነን ቀዳዳ እንዲሸፍን መተው የተሻለ ሊያተርፍ ይችላል። ልትሰብረው ወይም ከደዕዋው ዘርፍ አሽቀንጥረህ ልታስወጣው ከመነሳትህ፣ ልቡ ባንተ እንዲያዝን ከማድረግህ በፊት ደግመህ ደጋግመህ አስብበት።

"እኔስ ብዬሽ ነበር የዓይኔ ጉድፍ አውጪ
መዋጥ ይዘሽ መጣሽ ዓይኔን ልታወጪ!"

እንዲል አታድርገው።
ማሳሰቢያ፦
የማወራው ሱና ላይ (ተመሳሳይ መስመር ላይ) እንዳሉ ለሚያምኑ ዱዓት ነው።
=
Ibnu Munewor
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me//IbnuMunewor

nuredin al-mesqany it's me nuredin.I am psychiatric proffesional at somali region fiq hospital.thankyou for following me

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Jijiga?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address


Jijiga