Getehun Girma
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Getehun Girma, Health/Beauty, Adama, London.
01/07/2026
በሀረሪ ክልል ከ15 ሺህ በላይ ኩነቶች በዲጂታል ሥርዓት ተመዝግበዋል
++++++++++++++
| በሀረሪ ክልል በበጀት አመቱ ከ15 ሺህ በላይ ኩነቶች በዲጂታል ሥርዓት መመዝገባቸውን የክልሉ ወሳኝ ኩነትና ምዝገባ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡
የኤጀንሲው ኃላፊ አቶ ሳዳም መሀመድ ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፣ በበጀት ዓመቱ በዲጂታል ቴክኖሎጂ የተደገፈ ፈጣን አገልግሎት በመስጠት ከ15 ሺህ በላይ ኩነቶች በዲጂታል ተመዝግበዋል፡፡
በበጀት አመቱ 12 ሺህ 700 ኩነቶችን ለመመዝገብ መታቀዱን ያስታወሱት ኃላፊው፣ከእቅድ በላይ መከናወኑን ጠቁመዋል።
በዚህም መሰረት ከተመዘገቡት ኩነቶች መካከል 13 ሺህ 712 የልደት ምዝገባ፣ 880 የጋብቻ፣ 46 ፍቺ፣ 983 የሞት፣ አራት የጉዲፈቻ ምዝገባዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።
ከ2015 ጀምሮ በሁሉም ወረዳዎች የሚሰጡ የወሳኝ ኩነት ምዝገባዎች በዲጂታል አሰራር እየተተገበሩ እንደሚገኝ በመግለጽ፣የዲጂታል ምዝገባው ከመጀመሩ በፊት የተከናወኑ ምዝገባዎችን ወደ ዲጂታል የመቀየር ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
ኤጀንሲው ከወረዳዎች በተጨማሪ በጤና ተቋማት የልደትና ሞት ምዝገባን በአንድ ማዕከል እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸው፣ ምዝገባው ሙሉ በሙሉ በዲጂታል የተደገፈ መሆኑ የተጣራ የጤናና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት እንደሚያስችል አስረድተዋል፡፡
ቅንጅታዊ አሰራሩን በማጎልበት በጤና ተቋማት የኩነት ምዝገባ አገልግሎትን ለማስፋት እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው፣ዜጎች እያንዳንዱን ኩነት በወቅቱ በማስመዝገብ የዜግነት ግዴታቸውን ሊወጡ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
በማርቆስ በላይ
#ሀረሪ #ወሳኝኩነት #ልደት #ሞት #ጋብቻ
01/07/2026
የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ «መደመር» መጽሐፍ በቻይንኛ ተትርጉሞ፤ በቅርቡ ለንባብ ይበቃል!
በ2010 ዓ.ም የነበረውን ሀገራዊ ለውጥ ተከትሎ የኢትዮጵያ የነገ ጉዞ ፍኖተ-ካርታ ሆኖ የተወለደውና በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የተጻፈው የ«መደመር» መጽሐፍ፣ ኦፊሴላዊ የቻይንኛ ቋንቋ ትርጉም ሥራው በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፤ በቅርቡም ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለንባብ ሊበቃ መሆኑ ተረጋገጧል።
ባለፉት አሥርት ዓመታት ከአፍሪካ አህጉር ፈልቀው ወደ ዓለም መድረክ ከተሻገሩ ጥቂት አገር በቀል ፍልስፍናዎች መካከል ግንባር ቀደሙ የሆነው «መደመር»፣ አሁን ላይ ተደራሽነቱና ይህን የኢትዮጵያ አገር በቀል የሆነው የመደመር ፍልስፍና በርካቶች በትኩረት የሚመለከቱት አጀንዳ እየሆነ ነው። ቻይና የትርጉም ሥራውን እያጠናቀቀች ባለችበት በዚህ ወቅት፣ መጽሐፉ ከዚህ ቀደም በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ እና በእንግሊዝኛ ካለው ተደራሽነት በተጨማሪ በቅርቡ በአረብኛ እና በፓኪስታን የኡርዱ ቋንቋዎች ተተርጉሞ በደማቅ ሁኔታ መመረቁ ይታወሳል። አሁን ደግሞ በቢሊዮኖች የሚነገርለትን የቻይናን መድረክ በይፋ ለመቀላቀል የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ይገኛል።
ይህ የ«መደመር» መጽሐፍ ወደ ቻይንኛ ቋንቋ መተርጎም እና አሁን ላይ ሀያል ከሆኑ አገራ መካከል የምትጠቀሰውን ቻይናን ትኩረት ማግኘቱ ከመጽሃፍ ትርጉም ሥራ ባለፈ በርካታ ስትራቴጂካዊ እና ፖለቲካዊ እንድምታዎችን ይዟል፡፡ እንደ ቻይና ዓይነት እጅግ የዳበረ፣ የረጅም ዘመን የፖለቲካ ፍልስፍና ታሪክ ያላት እና ከማኦ ዜዱንግ እስከ ዴንግ ዚያኦፒንግ፣ አሁን ደግሞ እስከ ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ የዘለቀ የራሷ የርዕዮተ-ዓለም መስመር ያላት ሀገር፣ "መደመር"ን ኦፊሴላዊ በሆነ መንገድ ወደ ራሷ ቋንቋ መተርጎሟ፤ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ተጽዕኖ ፈጣሪና ትኩረት ሳቢ ፍልስፍና ማበርከት መቻሏን ማረጋገጫ ነው ። ኢትዮጵያ ባለፉት ዘመናት ከውጭ የሚመጡ ርዕዮተ-ዓለሞችን (Capitalism/Socialism) ስታስተናግድ የኖረችበትን የታሪክ ምዕራፍ በመቀየር፣ አሁን ግን የራሷን አገር በቀል ፍልስፍና ወደ ውጭ የምትልክ ሀገር ለመሆኗ ትልቅ ማሳያ ነው መደመር መጽሃፍ ።
መጽሐፉ አፍሪካን፣ መካከለኛው ምስራቅን (በአረብኛ)፣ ደቡብ እስያን (በኡርዱ) እና አሁን ደግሞ ምስራቅ እስያን (በቻይንኛ) ተደራሽ ማድረጉ፣ ፍልስፍናው ከተወለደበት የኢትዮጵያ ምድር ተሻግሮ አህጉራትንና የተለያዩ ባህሎችን የማስተሳሰርና የማቀራረብ ትልቅ የዲፕሎማሲ አቅም እንዳለውም ማሳያ ነው ።
የመደመር መጸሃፍ የቻይንኛ ትርጉም በቅርቡ ይጠብቁ!
01/07/2026
01/07/2026
በሀረሪ ክልል ከ199 ሺህ በላይ ዜጎች የፋይዳ ብሄራዊ መታወቂያ ወስደዋል፦ የክልሉ ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ
***************************
በሀረሪ ክልል በ2018 በጀት ዓመት 200 ሺህ ዜጎችን የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ እስከ ሰኔ ወር ድረስ 199,268 ዜጎች መታወቂያውን መውሰዳቸውን የክልሉ ወሳኝ ኩነት ምዝገባና ኤጀንሲ ሀላፊ አቶ ሳዳም መሀመድ ገልጸዋል።
ይህም የዕቅዱን 99 በመቶ በላይ ማሳካት የተቻለ ሲሆን ምዝገባው ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በአጠቃላይ በክልሉ ከ336ሺ በላይ ዜጎች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ባለቤት መሆን ችለዋል ብለዋል።
በክልሉ የሚገኙ የ6ኛ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ለፈተና በሚቀመጡበት ወቅት ብሄራዊ መታወቂያው ግዴታ በመሆኑ እነዚህ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ መታወቂያውን እንዲወስዱ መደረጉንም ገልጸዋል።
በገጠር አካባቢዎች ያለውን ተደራሽነት ይበልጥ ለማስፋትም ከኢትዮ ቴሌኮም እና ከፖስታ አገልግሎት ጋር በመተባበር የምዝገባ ሂደቶችን በመያዝ ሰፊ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ አቶ ሳዳም ጠቁመዋል።
የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የማንነት መደራረብንና ህገ-ወጥ አሰራሮችን በማስቀረት ረገድ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳ እንዳለው ሀላፊው ገልጸው በተለይም በኦንላይንና በሞባይል ባንኪንግ የሚፈጸሙ የሌብነትና የማጭበርበር ወንጀሎችን ለመከላከል አሁን ላይ ባንኮች አዲስ አካውንት ለመክፈትም ሆነ የቀደሙ ደንበኞችን መረጃ ከብሄራዊ መታወቂያው ጋር ለማስተሳሰር የፋይዳ መታወቂያን እንደ ቅድመ-ሁኔታ እየተጠቀሙበት ይገኛሉ ብለዋል።
የሀገሪቱን የ2030 የዲጂታል ስትራቴጂ ግብ ለማሳካት፣ በቀጣይም በክልሉ የሚገኙ ሁሉም ተቋማት አገልግሎት ለመስጠት መታወቂያውን እንደ አስገዳጅ ቅድመ-ሁኔታ እንዲጠቀሙበት የሚደረግ መሆኑ አቶ ሳዳም መሀመድ አመላክተዋል።
በቤተልሄም ደሴ
24.10.18
ተጨማሪ መረጃ በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ይከታተሉን።
ቲክቶክ፡ https://www.tiktok.com/
ዩቲዩብ :
https://www.youtube.com/
ቴሌግራም:
https://t.me/hararimassmediaagency
01/07/2026
የብዝሃ ዘርፍ ሪፎርሙ የቱሪዝሙን የኢኮኖሚ አበርክቶ አሳድጓል -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
የብዝሃ ዘርፍ ሪፎርሙ ለቱሪዝም መስክ የኢኮኖሚ አበርክቶ ማደግ ትልቅ ሚና መጫወቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኤንቢሲ ኢትዮጵያ ጋር ቱሪዝም አዲሱ የኢኮኖሚ ሞተር በሚል ርዕስ ቆይታ አድርገዋል።
መንግስታቸው የጀመረው የብዙሃ-ዘርፍ (Multi-sectoral) የኢኮኖሚ ሪፎርም በአሁኑ ወቅት በአስደናቂ ሁኔታ ውጤት እያስመዘገበ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
በግብርናው ዘርፍ በስንዴ፣ በቡና፣ በሩዝ እንዲሁም በፍራፍሬ ልማት የተገኙ ውጤቶች ለሀገር ውስጥ ምርታማነት ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑን ጠቁመዋል።
ከዚህም በተጨማሪ እንደ ሌማት ትሩፋት ያሉ ኢኒሼቲቮች፣ የቴክኖሎጂ ሪፎርሞች፣ የመሶብ ፕሮጀክት እና የአምስት ሚሊየን ኮደሮች የስልጠና መርሃ-ግብር ለጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) እድገት የበኩላቸውን ጉልህ ድርሻ እየተወጡ መሆኑን አስገንዝበዋል።
በኢንዱስትሪ እና በማዕድን ዘርፎች የተመዘገቡት ስኬቶችም የኢኮኖሚ ማሻሻያው አካል መሆናቸውን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ሀገሪቱ ከእነዚህ ዘርፎች በርካታ ቢሊየን ዶላሮችን እያገኘች መሆኑን አመልክተዋል።
የተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች በየበኩላቸው እያበረከቱት ባለው ሁለንተናዊ ድርሻ ምክንያት የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በተከታታይ እያደገ መሆኑን ገልጸው፤ በተያዘው በጀት ዓመት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የ 10 ነጥብ 2 በመቶ እድገት ያስመዘግባል ተብሎ እንደሚጠበቅ አስታውቀዋል።
የቱሪዝም ዘርፍን በተመለከተ በዘንድሮው ዓመት ከ1 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ የውጭ ሀገር ጎብኚዎች ኢትዮጵያን የጎበኙ ሲሆን፤ ይህም ቁጥር ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ100 ሺህ በላይ፣ ከካቻምናው አንጻር ደግሞ የ300 ሺህ የጎብኚዎች ጭማሪ ማሳየቱን አብራርተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም የውጭ ቱሪስት ፍሰቱና የተገኘው ገቢ እያደገ ቢሆንም፤ ገና የሚፈለገው ደረጃ ላይ ባይደርስም የታየው ለውጥ ግን እጅግ ተስፋ ሰጪና በግልጽ የሚታይ መሆኑን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ የኮንፈረንስ ቱሪዝም ማዕከል በመሆኗ በበጀት ዓመቱ 204 ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶችን እና ታላላቅ ሁነቶችን ማስተናገዷን ገልጸው፤ ይህም ሀገሪቱ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተሰሚነት ከማሳደጉም በላይ የኮንፈረንስ ቱሪዝም ስበት ማዕከል እየሆነች መምጣቷን ማረጋገጫ ነው ብለዋል።
በሰው ኃይል ልማት፣ በቱሪስቶች ፍሰት፣ በገቢ አሰባሰብ እና በአዋጪነት ረገድ የቱሪዝም ዘርፍ ለመንግስት የሪፎርም ስራዎች ፈጣንና አዎንታዊ ምላሽ እየሰጠ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አመልክተዋል።
በተለያዩ ጊዜያት ያጋጠሙ ፈተናዎች ቢኖሩም፤ ቱሪዝም ለብሄራዊ ኢኮኖሚው ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝና ዘርፉን እንደ አንዱ የኢኮኖሚ ምሰሶ አድርጎ መምረጥና መዋዕለ ንዋይ ማፍሰሱ ፍጹም ትክክለኛ እርምጃ እንደነበር በተከናወኑት ስኬታማ ስራዎች ማረጋገጥ ተችሏል ብለዋል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Adama
London