beza braid
beza braid
15/04/2025
01/08/2024
➤ለዋናው የአድዋ ጦርነት በር የከፈተው ቀዳሚው የኢትዮጵያ ሰራዊት ድል በ #አምባ #አላጌ ግንባር፣
ታህሳስ 4 ቀን 1888 ዓ.ም ዋናው የዳግማዊ #ምኒልክ ጦር ከ #ቢትሞ ተጉዞ #አላማጣ ላይ ሰፈረ፡፡ በዚህም ቀን የንጉሠ ነገሥቱ ድንኳን ከተተከለ በኋላ የራስ #መንገሻ መልእክተኛ ከአላጌ ደብዳቤ ይዞ መጣ፡፡ ደብዳቤ የያዘው ጎልማሳ መልእክተኛ ለምን ጉዳይ እንደመጣ ሲጠየቅም፣ በአላጌ ያለው የኢጣሊያ ጦር አለቀ፣ መድፉም ነፍጡም ተማረከ፣ ይህንኑ መልእክት እንዳደርስ ከራሶች ተልኬ የመጣሁ ነኝ በማለት መለሰ፡፡ ይህንን ወሬ አስቀድመው የሰሙት ሰዎችም ወዮ ወዮ እኛ ዘምተን ሳንዋጋ ጦርነቱ ሊያልቅብን ነው እያሉ ተናደዱ፡፡
ከዚህ በኋላ መልእክተኛው ደብዳቤውን ይዞ ወደ ንጉሠ ነገሥቱ ድንኳን በመግባት ወሬውን እንደሚከተለው ተናገረ፣
የኢጣሊያ ጦር የአላጌን አምባ በመያዝ መድፉን አልቦና ነፍጡን አሰልፎ ተቀምጦ ነበር፡፡ እኛም ቦታው የከፋ ስለነበር የምንጓዝበትን ሌላ አማራጭ መንገድ በመምከር #ራስ #መኮንን በሚጓዙበት በኩል ፊታውራሪ ገበየሁ አብሮ እንዲጓዝ አዘነው ነበር፡፡ እሱም 11 ሰአት ሲሆን በታዘዘበት ሳይተያይ ጦሩን አሰልፎ በሚጓዝበት ጊዜ ከኢጣሊያ ጦር ጥበቃዎች ጋር ተገናኝቶ ተታኮሰ፡፡ #ፊታውራሪ #ገበየሁም ከሹማምንቱ ጋር ሆኖ ይህ ጦራችን እንዲህ እንዳማረበት ለጌታችን አልጋ መሞት ይገባናል ብሎ ሲናገር ጭፍራው አንድ ጊዜ ወደ ውጊያ ገባ፡፡
የፊታውራሪ ገበየሁ ጦር 5ቱን የጣሊያን የአላጌ ምሽግ እንደናደው ተኩሱ ከነራስ መኮንን የጦር ሰፈር ተሰማ፡፡ ራስ መኮንንና ሹማምንቱ የነፊታውራሪ ገበየሁ ጦር ውጊያ እንደገጠመ እንደተረዱ ሁሉም ከየድንኳናቸው ታጥቀውና ተሰልፈው ወጡ፡፡ #ሹም #አጋሜ ተስፋዬ የሚባለው የትግራዩ ገዢ የራስ መንገሻ ሎሌ ግን ተራራውና ምሽጉ አደገኛ መሆኑን በመግለጽ ጦሩ ወደዛ እንዳይጓዝ በምኒልክ አምላክ በማለት ተማጠነ፡፡ ይሁን እንጂ ልመናውን ችላ በማለት መጀመሪያ #ቀኛዝማች #ታፈሰ ቀጥሎም #ፊታውራሪ #ተክሌ ቀድመው ሄደው ከጦሩ ደረሱ፡፡ ራስ መኮንን፣ #ራስ #ወሌ እና ራስ #ቢትወደድ #መንገሻም እኛ እዚህ ተቀምጠን የምኒልክን አሽከር ገበየሁን እናስገድላለንን ብለው ጦራቸውን እያሰለፉ ሄዱ፡፡
ቦታው እንኳን ለከብት ለእግረኛም በጣም አደገኛ ገደል ቢሆንም የኢትዮጵያ ጦር የመድፉንም የነፍጡንም ተኩስ ከቁብ ሳይቆጥር እጅ ለእጅ እየተያያዘ ገደሉን እየተቆናጠጠ ወጥቶ እጹብ ድንቅ ተብሎ የተመሰገነ ውጊያ በማድረግ በተራራው የመሸገውን የኢጣሊያን ጦር ፈጀው፡፡ ፊታውራሪ ገበየሁም ታሞ ስለነበር መሳሪያ ሳይዝ ዘንግ ብቻ ይዞ በበቅሎ ተቀምጦ አይዞህ ጥይት ያለቀብህም በጎራዴ በለው እያለ ሲያዋጋ ዋለ፡፡ በአላጌ ተራራ የኢጣሊያ ጦር ዋና አዋጊ የነበረው ሜጀር ቶዞሊም እሸሻለው ብሎ መንገድ ቢጀምርም የኢትዮጵያ ሰው ፈጣን ነውና ለማምለጥ ሳይቻለው ቀርቶ እሱም ተገደለ፡፡
ነገር ግን ፊታውራሪ ገበየሁና ቀኛዝማች ታፈሰ ሳይታዘዙ በመዋጋታቸው አስረናቸዋል በማለት ራሶች የላኩትን መልእክት ጃንሆይ #ምኒልክ ካዳመጡ በኋላ እኔም መጣሁ እግዚአብሔር ሁል ጊዜ ቀኙን ለኛ ያድርገው በማለት መልእክተኛውን ሸልመው ሰደዱት፡፡ በዛንም ጊዜ ሰዉ ሁሉ ፊታውራሪ ገበየሁን ከፍ ከፍ በማድረግ ገበየሁ - ጎበዝ አየሁ በማለት አሞገሰው፡፡
“የአድዋን ሥላሴ ጠላት አረከሰው፣ ገበየሁ በሞቴ ግባና ቀድሰው” የተባለላቸው ፊታውራሪ ገበየሁ በቀጣይ በተደረገ ውጊያ በታላቅ ጀግንነት በክብር ወድቀዋል፡፡ ፎቶግራፋቸውን ማግኘት ስላልተቻለ እሳቸውን በመተካት “ገበየሁ ቢሞት ተተካ #ባልቻ፣ መድፍ አገላባጭ ብቻ ለብቻ” የተባለላቸውን የሌላኛውን ታላቅ የአድዋ ጀግና የደጃች ባልቻ አባ #ነፍሶ ፎቶግራፍ ከዚህ በታች ተያይዟል፡፡
ባረጀ እድሜያቸው በ1927/1928 ዓ.ም በተነሳው ከአሶሼትድ ፕሬስ ታሪካዊ አርካይቭ ከተገኘው ፎቶግራፍ የሚታዩት ደጃዝማች ባልቻ ከ40 አመት በኋላም ለ2ኛ ጊዜ ኢትዮጵያን በቅኝ ለመግዛት ከመጣው የፋሽስት ጦር ጋር በእርጅና እድሜያቸው ተፋልመው በክብር ወድቀዋል፡፡ ክብር ለአርበኞቻችን!
◆ምንጭ፣ ታሪክ ዘመን ዘ ዳግማዊ ምኒልክ፣ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ፣ በጸሓፌ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴ (ከ1837 እስከ 1905 ዓ.ም የኖሩ)፣ አርቲስቲክ ማተሚ ቤት 1959 ዓ.ም፣ ገጽ 238-241
This is my new page welcome to beza braid
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
St6 1df
Stoke-on-Trent
ST6 1DF
Opening Hours
| Monday | 9am - 5pm |
| Tuesday | 9am - 5pm |
| Wednesday | 9am - 5pm |
| Thursday | 9am - 5pm |
| Friday | 9am - 5pm |