Abba Zenawi Amsalu
ሁሉ በርሱ ሆነ
ወለኩሎሙ እለ ኢየኀብሩ በቅድስት ቤተ ክርስቲያንከ ጉባኤ እንተ ሐዋርያት ሰቅል ውስተ ክሳውዲሆሙ ጋጋ ዘእሳት ወቦቱ ይሰሐቡ ወይብጽሑ ውስተ ዐቢይ ሰይል።
ዘኢይገኒ ለእግዚአብሔር ልዑል ፈቀደ ከመ ይግነይ ለጸላዒሁ።
ለክቡር እግዚአብሔር የማይገዛ ለታላቁ ኃጢአት ለሰይጣናት መገዛት ወደደ።
ተፈሣሕኩ በእግዚእነ ፈድፈደ እስመ ትኄልዩ ወትጽሕቁ ለትካዝየ እምቀዲሙ በከመ ትጽሕቁ ሊተ ዓዲ ወለእመ ይሰአነክሙ።
ወአኮ ዘእቤ በእንተ ዘኀጣእኩ እስመ አአምር ከመ የአክለኒ ዘብየ።
ግን አሁን ከጊዜ በኋላ ስለ እኔ እንደ ገና ልታስቡ ስለ ጀመራችሁ፥ በጌታ እጅግ ደስ ይለኛል፤ ጊዜ አጣችሁ እንጂ፥ ማሰብስ ታስቡ ነበር።
ይህን ስል ስለ ጉድለት አልልም፤ የምኖርበት ኑሮ ይበቃኛል ማለትን ተምሬአለሁና።
መዋረድንም አውቃለሁ መብዛትንም አውቃለሁ፤ በእያንዳንዱ ነገር በነገርም ሁሉ መጥገብንና መራብንም መብዛትንና መጉደልን ተምሬአለሁ::
እግዚአብሔር አምላክ ከስጋዊ ይልቅ ለዘለዓለማዊ ሕይወታች ይሳባል።
አንድ ነገር ከመቀበልቻን አስቀድሞ ያለኝ ይበቃኛል የሚለውን የመርካትን መርህ ካልተማርን እሱ ነገሮችን ሊሰጠን አይችልም።
ያለኝ ይበቃኛል ማለት ፈጽሞ የሚጎድሉን ነገሮች አይኖሩም ማለት አይደለም እግዚአብሔር ቢሰጠን የምንቀበል ነን እንጂ :: የክርስቲያን ደስታው(እርካታው) በውጫዊና ጊዜያዊ ደስታ በሁኔታ ላይ የተመሰረተ አይደለም ማለት ነው።
ታዲያ ያለኝ ይበቃኛል እግዚአብሔር ይመስገን የሚለውን ሃሳብ የማንቀበለው ለምን ይሆን ብለን ራሳችንን መጠየቅ ብንጀምር ችግሮቻችን በግልጥ ለማየት እንችላለን:: የብዙዎቻችን ያለኝ ይበቃል ማለት እርካታ እጦት የሚነሳው የተሰጡንን በርካታ ዉድ ስጦታዎቻችን አለመረዳትና የሉንም የምንላቸው ጥቂት ፍላጎታችንን አብዝተን መመልከታችን ነው:: እግዚአብሔር አምላክ በቸርነቱ እጹብ ድንቅ አድርጎ በመፍጠሩና በብዙ ሥጦታዎቹ ሳናመሰግን ጥቂት በሌሉን ነገሮች ላይ ትኩረት በማድረግና ከሌሎች ሰዎች ጋር ራሳችንን በማወዳደር መንፈሳዊ እርካታችንን እናጣለን::
በጣም ብዙ አማኞች እራሳቸውን ከሌሎች ምዕመናን ጋርራሳቸውን ያወዳድራሉ። እንዲሁ መምህራን ካህናት ዲያቆናት መዘማራን (መዘምራት)ስለ ስብከታችን ስለድምፃችን ማማር ተደራሽነት እና ታዋቂነት ራሳችንን እናነፃፅራለን። ታዲያ ራሳችንን በምናወዳድርበት ጊዜ ሁሉ እንበሳጫለን እንቀናናለን እንጠላለን ወ.ዘ.ተ ይህ ደግሞ የመንፈስ ዝለትን ያስከትላል::
ስለዚህ ራሳችንን ከሌሎች ጋር ማወዳደር ማቆምን መማር አለብን::
ሐዋርያው ቅድዱስ ጳውሎስ በፊልጵስዩስ መልእክቱ ፊልጵስዩስ 4:10 -12፤እንደዚህ ይላል “ ተፈሣሕኩ በእግዚእነ ፈድፈደ እስመ ትኄልዩ ወትጽሕቁ ለትካዝየ እምቀዲሙ በከመ ትጽሕቁ ሊተ ዓዲ ወለእመ ይሰአነክሙ።
ወአኮ ዘእቤ በእንተ ዘኀጣእኩ እስመ አአምር ከመ የአክለኒ ዘብየ።
ግን አሁን ከጊዜ በኋላ ስለ እኔ እንደ ገና ልታስቡ ስለ ጀመራችሁ፥ በጌታ እጅግ ደስ ይለኛል፤ ጊዜ አጣችሁ እንጂ፥ ማሰብስ ታስቡ ነበር።
ይህን ስል ስለ ጉድለት አልልም፤ የምኖርበት ኑሮ ይበቃኛል ማለትን ተምሬአለሁና።
መዋረድንም አውቃለሁ መብዛትንም አውቃለሁ፤ በእያንዳንዱ ነገር በነገርም ሁሉ መጥገብንና መራብንም መብዛትንና መጉደልን ተምሬአለሁ። ከቅዱስ ጳውሎስ ሃሳብ እንደምንረዳው ያለኝ ይበቃኛል ማለት ወይም እርካታ የሚመጣው በተፈጥሮ ሳይሆን የምንማረው ነው:: ይህን ካደረግን እግዚአብሔር ፍላጎታችንን ሁሉ እንደሚያሟላልን ቃል ገብቷል።
መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡- እስመ ለነሰ ተግባርነ ዐቢይ ውእቱ ፈሪሀ እግዚአብሔር። እስመ አልቦ ዘአምጻእነ ውስተ ዓለም ወአልቦ ዘንክል ነሢአ እምኔሁ
“ኑሮዬ ይበቃኛል ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤ ወደ ዓለም ምንም እንኳ አላመጣንምና አንዳችንም ልንወስድ አይቻለንም፤ ምግብና ልብስ ከኖረን ግን፥ እርሱ ይበቃናል”::
ያለኝ ይበቃኛል ብሎ መኖርን ለመማር ከታላላቅ ምስጢሮች አንዱ ያለህ ነገር የአንተ እንዳልሆነ መገንዘብ ነው።
የተሰጡን በጎ ስጦታዎች ሁሉ እግዚአብሔር አደራ የሰጠን የአገልግሎት መክሊቶቻችን ናቸው:: በምድር ላይ በምንቆይበት ጊዜ በጥንቃቄ ልንይዛቸውና ልናተርፍባቸው የተሰጡን ናቸው እንጂ የኛ አይደሉም:: በሌላው ስጦታና አገልግሎት እራስን ከሌላው ሰው ጋር እያወዳደሩ በገንዘቡ በስልጣኑ በተደማጪነቱ በአገልግሎቱ የእግዚአብሔር ይስጦታውን ብዛት ማድነቅ እንጂ መከፋት አይገባም::
1. እግዚአብሔር አምላክ ያለን ይበቃናል እንድንልና በተሰጠን ስጦታ አገልግለን እንድናተርፍ በቸርነቱ ያግዘን::
#GeezBible The Bible is God's Word. And there is salvation in no one else, for there is no other name under heaven given among men by which we must be saved (Acts 4:12). መጽሐፍ ቅዱስ በአማርኛና በትግርኛ
በመጀመሪያው ተአምር ብዙ ምርጥ ነገሮች በአንድ ጊዜ ተፈጽመዋል። የተከበረ ጋብቻ ተቀድሷልና፣ በሴቶች ላይ ያለው እርግማን ተወግዷልና (ከእንግዲህ በኀዘን ልጅ አይወልዱምና፣ አሁን ክርስቶስ የልደታችንን መጀመሪያ ባርኮታል)፣ የመድኃኒታችንም ክብር እንደ ፀሐይ ጨረሮች በራ። ከዚህም በላይ ደቀ መዛሙርቱ በእምነት የተረጋገጡት በተአምር ነው።
የታሪክ ዘገባው እንግዲህ እዚህ ላይ ያቆማል ነገር ግን ስለተባለው ነገር ያለውን ሌላውን አተያይ ልንመረምር እና በውስጡ ያለውን የሚያመለክት ልንል የሚገባን ይመስለኛል። የእግዚአብሔር ቃል ከሰማይ ወረደ እርሱ ራሱ እንደ ተናገረ ሙሽራ ሆኖ የሰውን ተፈጥሮ የራሱ አድርጎ የጥበብ መንፈሳዊ ዘርን እንዲያወጣ ይረዳው ዘንድ እና ስለዚህ ምክንያታዊ በሆነ መልኩ የሰው ተፈጥሮ ሙሽራይቱ አዳኝ ሙሽራ ይባላል። ቅዱሳን መጻሕፍት ቋንቋን ከሰው ነገር በመነሳት በላያችን ያለውን ትርጉም ስለሚሰጥ ነው። ጋብቻ በሦስተኛው ቀን ይፈጸማል, ማለትም, በዚህ ዓለም በመጨረሻው ዘመን: ቁጥር ሦስት መጀመሪያ መካከለኛ መጨረሻ ይሰጠናል. ዘመኑ ሁሉ እንዲሁ ይለካልና። ከዚህም ጋር በመስማማት ከነቢያት አንዱ፡- መትቶናል፥ ያጠግነናል የተባለውን እናያለን። ከሁለት ቀን በኋላ ያድነናል በሦስተኛውም ቀን ያስነሣናል በፊቱም እንኖራለን። ያን ጊዜ ጌታን ለማወቅ ከተከተልን እናውቃለን; መውጣቱ እንደ ማለዳ ተዘጋጅቷል። አፈር ነህ ወደ አፈርም ትመለሳለህ ብሎ ስለ አዳም መተላለፍ መታን ። በሙስናና በሞት የተመታውን በሦስተኛው ቀን አሰረው ይህም በመጀመሪያ ወይም በመካከል አይደለም ነገር ግን በመጨረሻው ዘመን ሰውን ስለ እኛ ሲፈጥር ተፈጥሮአችንን ሁሉ ፈጠረ, ከፍ ከፍ አደረገ. በራሱ ከሙታን. ስለዚህም እርሱ ላንቀላፉት በኩራት ተብሎ ተጠርቷል። ስለዚህ ጋብቻው የሚፈጸምበት ሦስተኛው ቀን ነው ሲል የመጨረሻውን ጊዜ ያመለክታል። ቦታውንም ይጠቅሳል; በቃና ዘገሊላ ነው ይላልና። መማር የሚወድ እንደ ገና ያስተውል፤ መሰብሰቢያው በኢየሩሳሌም አይደለምና፥ ነገር ግን በአሕዛብ አገር እንደ ነበረ ያለ ከይሁዳ ውጭ በዓሉ ይከበራል። ነቢዩ እንዳለ የአሕዛብ ገሊላ ናትና። የአይሁድ ምኩራብ ሙሽራውን ከሰማይ የናቀው፣ እናም የአሕዛብ ቤተክርስቲያን እርሱን እንደተቀበለችው፣ እና ያ ደግሞ በደስታ እንደተቀበለችው፣ እኔ ሙሉ በሙሉ ግልፅ ይመስለኛል። አዳኝ ወደ ጋብቻ የሚመጣው በራሱ ፈቃድ አይደለም; በብዙ የቅዱሳን ድምፅ ይጠራ ነበርና። ነገር ግን የወይን ጠጅ በዓላትን ከሸፈ; ሕጉ ምንም አልፈጸመውምና የሙሴ ጽሑፍ ፍጹም ደስታን ለማግኘት አልበቃም፤ ነገር ግን እኛን ለማዳን የተተከለው የመጠገን መጠን አልደረሰም። ስለዚህ ስለ እኛ ደግሞ። የወይን ጠጅ የላቸውም መባሉ እውነት ነበር። ቸር አምላክ ግን በመልካም ነገር እጦት ያደከመውን ተፈጥሮአችንን ቸል አይልም። ከፊተኛው የሚበልጥ የወይን ጠጅ አኖረ ፊደል ይገድላልና መንፈስ ግን ሕይወትን ይሰጣል። ህጉም በመልካም ነገር ፍፁምነት የለውም፣ ነገር ግን መለኮታዊው የወንጌል ትምህርት ሙሉ በረከትን ያመጣል። የበዓሉ ገዥ በወይኑ ይደነቃል፡ ለመለኮታዊ ክህነት የተሾሙት እና የመድኀኒታችን የክርስቶስ ቤት አደራ የተሰጣቸው እያንዳንዱ ሰው ከህግ በላይ በሆነው ትምህርቱ ይደነቃል ብዬ አስባለሁ። ነገር ግን ክርስቶስ አስቀድሞ እንዲሰጠው አዟል፤ ምክንያቱም እንደ ጳውሎስ ቃል፡— የሚደክም ገበሬ ከፍሬው አስቀድሞ ተካፋይ ሊሆን ይገባዋል። ሰሚው ደግሞሐዋርያው የሚለውን ይመልከት።
✝️ቅዳሜ ~ ቅዱሳት አንስት
(አንባብያን ከሰኞ-ቅዳሜ ያሉትን በዓላት ለምን በምን እንደተከበሩ በተከታታይ የጻፍኳቸውን ትመለከቱ ዘንድ ጋብዣችኋለሁ)
እንኳን አደረሳችሁ!
✍️ጌታችን በተነሣ በሰባተኛው ቀን ቅዱሳት አንስት መላእክት እንደተነሣ ነግረዋቸው ሂደው ለደቀ መዛሙርቱ የጌታችንን ትንሣኤ መናገራቸው ይታሰባል።
✔️"በሰንበት መጨረሻ መጀመሪያው ቀን ሲነጋ መግደላዊት ማርያምና ሁለተኛይቱ ማርያም መቃብሩን ሊያዩ መጡ(ማቴ፳፥፰፩/28፥1) እንዲል
አስቀድሞ ሲያገለግሉት የነበሩት ቅዱሳት አንስትና ሰባት አጋንንት ያወጣላት ማርያም መግደላዊት ለፍቅሩ ይሳሱ ነበርና ቅዳሜ ለእሑድ አጥቢያ ወደ መቃብሩ ሲመላለሱ አድረዋልና እንዲህ አለ።
✍️መጨረሻ ሰንበት ያለው ቀዳሚት ሰንበትን ነው። መጀመሪያው ቀን ያለው እሑድን ነው። እሑድ፣ አሐድ ማለት አንድ ወይም መጀመሪያ ማለት ነውና።
✔️"ሰንበትም ካለፈ በኋላ መግደላዊት ማርያም ፣ የያዕቆብ እናት ማርያም ፣ ሰሎሜም መጥተው ሊቀቡት ሽቱ ገዙ።(ማር፲፮፥፩/16፥1)
"ከሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን ያዘጋጁትን ሽቱ ይዘው ከእነርሱም ጋር አንዳንዶቹ ወደ መቃብሩ እጅግ ማልደው መጡ። (ሉቃ፳፬፥፩/24፥1)
"ከሳምንቱ በፊተኛው ቀን መግደላዊት ማርያም ገና ጨለማ ሳለ ወደ መቃብር መጣች።(፳፥፩/20፥1)
✍️ወንጌላውያን መጀመሪያ ፊተኛ እያሉ የሚነግሩን ጥንተ ዕለት የሆነውን እሑድን ነው።
የዕለተ እሑድ በኵረ በዓላትነትና ሰንበተ ክርስቲያንነት መሠረት የተጣለው ጌታችን የተነሣበት ዕለት ስለሆነ ነው።
✔️ከዚህ በላይ እንዳየነው ወንጌላውያን ሴቶች ወደ መቃብሩ በተናጠልም በአንድ ላይም መሄዳቸውን ነግረውናል።
ስለሆነም ቤተክርስቲያን ለክርስቶስ ያላቸውን ፍቅር የገለጡትን ቅዱሳት አንስት ጌታችን በተነሣ በሰባተኛው ቀን በማክበር ታስባቸዋለች።
↪️ቤተክርስቲያን እግዚአብሔርን ያገለገሉትን ቅዱሳን አበውን ፣ ቅዱሳት እማትን ውለታቸውን ሳትረሳ መታሰቢያቸውን ታከብራለች።
በቤተክርስቲያን እንዲታሰቡ መሆኑም እራሱ ባለቤቱ ቃለ ይገባላቸው በመሆኑ ነው።
"እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ ቃል ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ ይላልና፦
በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ።" እንዲል (ኢሳ፶፮፥፬-፭/56፥4-5)
🤲የቅዱሳት አንስት በረከታቸው አይለየን!
✍️ከዚህ ቀጥሎ በዚህ ዕለት ድጓው ከሚሠራው ቃለ እግዚአብሔር በከፊል እናያለን።
✝️እስመ ለዓለም
"አፀውተ ሲኦል አድለዉ ሎቱ ወይቤሉ ዝኬ ውእቱ ክርስቶስ ዘወረደ ኀቤነ ከመ ያንሥእ ኵሎ ሙታነ"
🔐ትርጉም
"የሲኦል ደጅ አጋፋሪዎች በር ዘጊዎች አደሉለት። ሙታንን ሁሉ ያስነሣ ዘንድ ወደ እኛ የወረደው ይህ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው አሉ።"
🌹የሲኦ ደጅ አጋፋሪዎች የተባሉ አጋንንት ናቸው። ክርስቶስ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ሲወርድ አይተው ደንግጠው ፈዘው መቅረታቸውንና በእርሱ ላይ ምንም ምን ማድረግ ያልተቻላቸው መሆኑን ለመግለጥ አደሉለት አለ።
🌹አንድም፦ እርሱ መሆኑን ሲያዩ በሲኦል በር ላይ የነበሩ አጋንንት ሊቃነ አጋንንት ኃይል አጥተዋልና እንዲህ አለ።
🌹አንድም፦በቁሙ አደሉለት።
✝️ዕዝል
"በ፪ሃሌታ አቅዲሙ ነገረ በደኃሪ መዋዕል ከመ ይትነሣእ ክርስቶስ አንስት አንከራ ወነገራ ከመ ተንሥአ እግዚእነ እሙታን"
🔐ትርጉም
"ክርስቶስ በኋለኛው ዘመን እንደሚነሣ አስቀድሞ ተናገረ።
ጌታችን ከሙታን ተለይቶ እንደ ተነሣ ሴቶች አድንቀው ተናገሩ።"
🌹ይህ ደግሞ ጌታችን እንደሚወርድ እንደሚወለድ እንደሚሞት እንደሚቀበር እንደሚነሣ አስቀድሞ በትንቢት መነገሩን ለማስረዳት ነው።
አንድም፦ በቁሙ ጌታችን አስቀድሞ ለሐዋርያት ከሦስት ቀናት በኋላ እንደሚነሣ ነግሯቸው ነበርና ያን ለማስረዳት ነው።
✝️ዘይእዜ
"አንስት አንከራ ትንሣኤሁ ወነገራ ለአርዳኢሁ (በሰላም) አንስት አንከራ ትንሣኤሁ ወነገራ ለአርዳኢሁ"
🔐ትርጉም
"ሴቶች አደነቁ ትንሣኤውንም ለደቀ መዛሙርቱ ነገሩ።"
🌹መላእክት እንደ ተነሣ ነግረዋቸው ሂደው ለደቀ መዛሙርቱ መንገራውን ነው የሚነግረን።
✝️ይትባረክ
"በከመ ጽሑፍ በወንጌል ዘይቤ ቃለ ሕይወት ዘለዓለም ብከ አንሥአ ለነ ቀርነ መድኃኒትነ"
🔐ትርጉም
"በወንጌል እንደ ተጻፈ የዘለዓለም የሕይወት ቃል አለህ(፮፥፷፰/6፥68) የምንድንበትን ቀንድ አስነሣልን(ሉቃ፩፥፷፱/1፥69)
✝️አቡን
"በ፬ሃሌታ እምድኅረ ተንሥአ እሙታን አስተርአዮን ቀዲሙ ለአንስት ለማርያም ወላዲተ አምላክ ወለማርያም መግደላዊት ለሣራ ወለሰሎሜ ወለኵሎን ቅዱሳት አንስት"
🔐ትርጉም
"ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ በኋላ አስቀድሞ ለሴቶች ማለትም ለማርያም ወላዲተ አምላክ ፣ ለመግደላዊት ማርያም ፣ ለሣራ፣ ለሰሎሜ እና ለሁሉም ቅዱሳት አንስት ታያቸው።
🌹ጌታችን ከሙታን እንደተነሣ አስቀድሞ ለሴቶች እንደታያቸው ወንጌል ይነግረናልና እሱን ነው ሊቁ የሚነግረን።
የሊቁ በረከት ይደርብን!
የነገ ሰው ይበለን!
መምህር ዳንኤል አለባቸው
የሐዲሳት ትርጓሜ መምህርና የሊቅ ደቀ መዝሙር
Clicca qui per richiedere la tua inserzione sponsorizzata.
Digitare
Contatta l'azienda
Sito Web
Indirizzo
Via Di Scandicci
Florence
50143