Alsae degefe
Alsae degefe
09/05/2023
+ ማርያምን በማመን የሚያክላት ማነው? +
ኤልሳቤጥ ለድንግሊቱ ያቀረበችውን ምስጋና ‘የጌታዬ እናት’ ብላ ጀምራ ‘ያመነች ብፅዕት’ ብላ ፈጸመችው፡፡ ‘ከጌታ ዘንድ የነገሩሽ ቃል ይፈጸማልና ያመንሽ ብፅዕት ነሽ’ ‘ወብፅዕት አንቲ እንተ ተአምኒ ከመ ይከውን ቃለ ዘነገሩኪ እምኀበ እግዚአብሔር’ ሉቃ. ፩፥፵፭ ኤልሳቤጥ የእመቤታችንን እምነት አደነቀች፡፡
በእርግጥም ከእመቤታችን የሚበልጥ እምነት ያለው ማነው? የእምነት አርበኞች ሁሉ ከያሉበት ቢመጡ በፊትዋ ሊቆሙ የማይቻላቸው የእምነትን ተራራ ወጥታ የምትጠብቅ ብፅዕት እመቤታችን ናት፡፡
አቤል ከቃየን የሚበልጥ መሥዋዕት በእምነት ለእግዚአብሔር አቀረበ ፣ ድንግሊቱ ግን ‘እነሆኝ’
ብላ ራስዋን ለእግዚአብሔር አቀረበች፡፡
ሄኖክ ሞትን እንዳያይ በእምነት ተወሰደ ፣ ድንግል ግን
በእምነትዋ ሞትን የሚገድለውን ወለደች፡፡ ኖኅ ቤተሰቦቹን ለማዳን በእምነት መርከብን አዘጋጀ ፤ ድንግል ማርያም ግን እግዚአብሔር ዓለሙን ያድን ዘንድ ራስዋን መርከብ አድርጋ ሠጠች፡፡ ሣራ ዕድሜዋ ካለፈ በኋላ ዘርን ለመፅነስ ኃይልን በእምነት አገኘች ፣ ድንግል ማርያም ግን ያለ ወንድ ዘር በድንግልና ለመፅነስ በእምነት ኃይልን አገኘች፡፡
አብርሃም ይስሐቅን እግዚአብሔር ከሙታን ያስነሣዋል ብሎ በእምነት አቀረበ ድንግል ግን ልጅዋን እግዚአብሔርነቱ ከሞት ያስነሣዋል ብላ
ሞቱን በዝምታ አይታለች፡፡ ሙሴ ከተወለደ በኋላ ወላጆቹ በእምነት ሦስት ወር ሸሸጉት ንጉሥንም አልፈሩም ድንግል ማርያም ግን ልጅዋን በእምነት ሦስት ዓመት ሸሸገችው ሔሮድስንም አልፈራችም፡፡
ሙሴ ባልወለደው ፈርዖን የፈርዖን የልጅ ልጅ ተብሎ እየተጠራ እናቱ ዮካብድ ልጅዋን እናትም ገረድም ሆና በእምነት አሳደገችው፡፡ ክርስቶስም ባልወለደው ዮሴፍ የዮሴፍ ልጅ ተብሎ እየተጠራ ድንግል ማርያም እናትም ገረድም ሆና በእምነትዋ አሳደገችው፡፡ ‘ተፈስሒ ኦ ማርያም እም ወአመት’ ‘እናትና ገረድ ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ’ እንዲል፡፡ ሁሉን እንዳንተርክ ጊዜ ያጥርብናል እንጂ የሁሉም በእምነት የተመሰከረላቸው ቅዱሳን የእምነት ተጋድሎ ቢደመር ያመነችውን ብፅዕት እምነት አያህልም፡፡ ዕብ. ፲፩፥፬-፳፫
ኤልሳቤጥ ድንግል ማርያምን ‘ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልከው የነገሩሽን ቃል ይፈጸማል ብለሽ የምታምኚ ብፅዕት ነሽ’ ብላ አደነቀቻት፡ ፡ የኤልሳቤጥ ባል ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ መጥቶ የነገረውን ቃል አላምን ብሎ ‘ቃሌን ስላላመንህ ዲዳ ትሆናለህ’ ተብሎ ተረግሞ ዲዳና ደንቆሮ ሆኖ በቤት ተቀምጦአል፡፡ ስለዚህ አለማመን የሚያስከፍለውን ዋጋ በባልዋ ያየችው ኤልሳቤጥ የድንግሊቱን እምነት አደነቀች፡፡ ዘካርያስ አላምንም ያለው ሚስትህ ካረጀች በኋላ ትፀንሳለች ሲባል ነበረ፡፡ ድንግል ማርያም ግን ታይቶ ተሰምቶ በማያውቅ ከተፈጥሮ ውጪ በሆነ መንገድ ትፀንሻለሽ ተብላ ያመነች ብፅዕት ናት፡፡
ድንግል ማርያም ያመነችው ለማመን ቀላል የሆነ ነገርን አልነበረም፡፡ አምላክ ሰው ይሆናል ብሎ ማመን የመጀመሪያው ፈተና ነው፡፡ እንኳንስ ገና ሳይፈጸም ከተፈጸመም በኋላ ለማመን የሚቸግራቸው ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ ስለዚህ አምላክ ሰው ሆኖ ይገለጣል
ብላ መቀበልዋ የመጀመሪያው እምነትዋ ነው፡፡
ሁለተኛው ደግሞ ሰው የሚሆነውን አምላክ አንቺ ትወልጂአዋለሽ ስትባል መቀበልዋ ሲሆን
ከሁሉ ከባዱ ደግሞ ያለ ወንድ ዘር በድንግልናሽ ሳለሽ ትወልጂዋለሽ ስትባል ማመንዋ ነው፡፡ እግዚአብሔር ምንም ነገርን በማንም ሰው ላይ ለማድረግ የሚሳነው ነገር ባይኖርም ያንን ነገር ለማከናወን ግን እምነትን ከሰው ዘንድ ይፈልጋል፡፡ ‘ብርቱ የሚሆን ታላቅ ሥራን’ ለድንግሊቱ እንዲያደርግም ብርቱ የሆነ እምነት በእርስዋ ዘንድ ተገኝቶ ነበር፡፡
ካለመኖር ወደ መኖር ወደ መኖር (እምኀበ አልቦ ኀበ ቦ) ፣ ከሌለ ወዳለ ነገር (እምኀበ ኢምንት ኀበ ምንት) ማምጣት የሚቻለው ልዑል እግዚአብሔር አንድን ነገር ያለ አንዳች መነሻ ሊያደርግ ይቻለዋል፡፡
‘እንበለ እሳት አንደደ ወዘእንበለ ማይ አብረደ’ እንዲል እግዚአብሔር ያለ እሳት ማንደድ ፣ ያለ ውኃ ማብረድ ፣ ያለ ብዕር መፃፍ ፣ ያለ ቀስት መንደፍ ይችላል፡፡
ድንግሊቱን ያለ ዘር መውለድ እንድትችል እንዳደረገ አንተንም በሕይወትህ ውስጥ ያለ እግር እንድትሔድ ፣ ያለ ክንፍ እንድትበር ፣ ያለ ድምፅ እንድጮኽ ፣ ያለ ሥልጣን እንድታዝ ፣ ያለ ምግብ እንድትጠግብ ፣ ያለ ውኃ እንድትረካ ማድረግ ይቻለዋል፡፡ እርሱ አንዳች ነገርን ያለ አንዳች ነገር እንዲያደርግልህ ግን እንደ ድንግሊቱ ‘እንደ ቃልህ ይሁንልኝ’ ብለህ በእምነት መቀበል አለብህ፡፡
ድንግሊቱ ግን ድንቅን ነገር በእርስዋ እንዲሠራባት ‘ከጌታ ዘንድ የነገሯትን ያመነች ብፅዕት ነች’
እመቤታችን ጌታን የፀነሰችበትና የወለደችበት ሁኔታም ትልቅ እምነት የሚጠይቅ ነበር፡፡ በፀነሰችበት ወራት በሆድዋ ውስጥ ተወስኖ ያለው በዓለም ሁሉ የሞላው አምላክ መሆኑን ማሰብ ለድንግሊቱ እጅግ ከባድ ሊሆን የሚችል ነገር ነበር፡፡
በወለደችው ጊዜም የወለደችው ዓለም
ሳይፈጠር የነበረውን አምላክ መሆኑን ማመንስ ምንኛ ከባድ ነው? ከአጠገብዋ ሳለ በሁሉ የሞላውን አምላክ እያየችው ቢሆንም ድንግሊቱ
መርምራ ልትደርስበት አልቻለችም፡፡
‘በሆዷ የተሸከመችው ማርያምም
አየሁት ልረዳው አልቻልሁም አለች’ ‘ማርያምኒ ትቤ እንተ ፆረቶ በከርሣ ርኢክዎ ወስእንኩ ጠይቆቶ’ እንዲል፡፡ (ቅዱስ ያሬድ ወርቱዐ ሃይማኖት)
የታቀፈችው አፉን ያልፈታ የማይናገር ሕፃን ቢሆንም እርሱ ግን በቃልነቱ ዓለምን የፈጠረ ነው፡፡ ‘ማርያም መናገር የማይችል ዝምተኛ ሕፃንን አቀፈች ፣ በእርሱ ውስጥ ግን የዓለም ሁሉ ቋንቋ ተሸሽጎ ነበር (St. Ephrem the Syrian, Hymns on the Nativity, Desert Fathers Series Vol. 5 III)
‘እናቱ ብትሆንም ስለ እርሱ በእርግጠኝነት ሁሉን አታውቅም ነበር፡፡ በማሕፀንዋ የፀነሰችው ካልመረመረችው ማን ሊመረምረው ይችላል’ ይላል ማር ኤፍሬም (St. Ephrem the Syrian, Hymns on the Nativity, Desert Fathers Series Vol. 5 HymnXVIII)
‘አንደበትሽ ያመሰገነ እንጂ ያልተመራመረ ፣ አፍሽም የዘመረ እንጂ ያልተከራከረ ድንግል ሆይ የተባረክሽ ነሽ’ ካላትም በኋላ ቅዱስ ኤፍሬም በድንግሊቱ ቦታ ሆኖ እንዲህ ሲል ይቀኛል ፦
‘ድንግሊቱን እፀንስ ዘንድ የሠጠኝ ማን ነው? ይህንን አንድ ሲሆን የበዛ ፣ ታናሽ ሲሆን ታላቅ የሆነ ፣ ከእኔ ጋር ሲሆን በሁሉ የሞላ ሕፃን የሠጠኝ ማን ነው?
በእኔ [ማሕፀን] ውስጥ እያለህ ከእኔም ውጪ በሁሉ ቦታ ነበርህ ፣ በወለድሁህ ጊዜም ረቂቅ አምላክነትነህም ከእኔ ውስጥ አልወጣም። በእኔ ውስጥ ነህ ፣ ከእኔም ውጪ ነህ! ይህ ነገር ለእኔ ለእናትህን ያስደነቀኛል።
የሚታየው ሰውነህን በፊቴ ባየሁ ጊዜ የማይታየው አምላክነትህን በሕሊናዬ አየዋለሁ። ቅዱስ ሆይ በሚታየው ሰውነትህ ውስጥ አዳምን አየዋለሁ ፣ በማይታየው መለኮትህ ውስጥ ደግሞ በአንተ ሕልው ሆኖ የሚኖረውን እግዚአብሔር አብን አየዋለሁ’
ድንግል ማርያም በሆድዋ ውስጥ ፅንስ ሆኖ የሚንቀሳቀሰው ከአምላካዊ ዙፋኑ ያልተለየ ፈጣሪ መሆኑንና ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ሳይለይ በእርስዋ ውስጥ ሳለ ዓለምን እያስተዳደረ መሆኑን ማመንዋ ትልቅ እምነት የሚጠይቅ ነበር፡፡ ይህ በእርግጥ ከሕሊና በላይ ነው፡፡
‘ሁሉን የሚገዛው ኃይል እንዴት በማሕፀን ውስጥ አደረ? በማሕፀንዋ ውስጥ ሳለ የዓለም ልጓም በእጁ ተይዞ ነበር፡፡ እናቱም ፈቃዱን ለመፈጸም ትጠባበቅ ነበር፡፡ ፀሐይ ወደ ማሕፀንዋ ገባ፡፡ ከእናቱ የቀደመ ሕፃንን ያየ ማን ነው?’ ይላል ቅዱስ ኤፍሬም፡፡
ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊም እንዲህ ሲል ያብራራል፦
‘ወአምነት ዘእንበለ ተኀሥሦ ከመ ውእቱ ቃለ አብ አምላክ ቃል ሥግው ዘውእቱ እመለኮተ አብ ሥግው በፈቃዱ ወኢትዌለጥ እምሕላዌ ዕበየ መለኮቱ ዘውእቱ አሐዱ ምስለ አብ ወመንፈስ ቅዱስ’
‘ድንግል ወንድ ሳታውቅ የፀነሰችውን ሊዋሐደው በፈጠረው ሥጋ ወለደችው እርሱ ከአብ ባሕርይ የተገኘና በፈቃዱ ሰው የሆነ እንደሆነ ከጌትነቱ ባሕርይ የማይለወጥ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ የሆነ እርሱ እንደሆነ ያለ ጥርጥር አመነች’ (ሃይማኖተ አበው ፤ ዘቅዱስ አትናቴዎስ 28፡19-20 293)
ከወለደችውም በኋላ ፈጣሪዋን እንደ ሕፃን ሲያለቅስ ስታይ እምነትዋ አለመናወጹ ምንኛ ድንቅ ነው?
የአምላክዋን ዕንባ እየጠረገች ‘ዕንባዎችን ሁሉ ከዓይን ላይ ያብሳል’ የተባለለት የሁላችን የዕንባችን
ሰፍነግ የሆነ ጌታ እንደሆነ አምናለች፡፡ በጨርቅ ጠቅልላ እያለበሰችው ተራሮችና ሜዳዎችን በአበባ የሚያለብሳቸው እርሱ እንደሆነ አልተጠራጠረችም፡፡
‘ከማርያም ወተትን ሲጠባ የፍጥረቱን ጥም የሚያረካው ግን እርሱ ነበር፡፡ እርሱ በማርያም እቅፍ ውስጥ ቢተኛም ፍጥረታት ሁሉ ደግሞ በእርሱ እቅፍ ውስጥ ነበሩ’ (St. Ephrem the Syrian, Desert Fathers series, Vol. 5 Hymns on the Nativity, III)
ድንግሊቱ ወተትን እንደ ሕፃናት በለመናት ጊዜም ከድንግልናዊ ወተትዋ ስታጠባው የፍጥረቱ መጋቢ መሆኑን አለመጠራጠርዋ እንዴት ይደንቃል?
ቅዱስ ኤፍሬም እንዲህ ይላል :-
አንተ ምንጭ ሆይ ለአንተ ለማጠጣት የጡቶችን ምንጭ እንዴት ልከፍታቸው ይቻለኛል? ሁሉን ከገበታህ የምትመግብ ሆይ እኔ አንተን ልመግብህ እንዴት ይቻለኛል? የክብርን ነጸብራቅ የተጎናፀፍከው ሆይ እንደምን በጨርቅ ልጠቀልልህ እችላለሁ?
የልደት መዝሙራቱን ‘እሹሩሩ’ (lullaby) ብሎ የሰየመው ቅዱስ ኤፍሬም ድንግሊቱ የሚያለቅስ ልጅዋን በምን ዓይነት እሹሩሩታ ምን ብላ ልታባብለው ትችል እንደነበር እያሰበ በመደነቅ ይዘምራል፡፡
‘እርስዋ ለልጅዋ የዘመረችውን የማባበል ዝማሬ የሚመስል ዝማሬ የለም፡፡ ከእርስዋ ዝማሬውን ተውሳ ልጅዋን ልታባብል የምትችል እናትስ ማን ናት? ልጅዋ ፈጣሪ የሆነ ሌላ እናትስ ከየት ትገኛለች?’ በማለት ይጀምራል፡፡ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ መላእክት የሚዘምሩለትን አምላክ ለማባበል በእቅፍዋ የያዘችው ድንግል ማርያምን ሁኔታ ወደር እንደሌለውም እንዲህ ሲል ያራቅቃል :-
‘የድንግል ማርያምን የማባበል ቃል የሚመስል እሹሩሩ የለም፡፡ የእስራኤልን ልጆች ያባበሉ የልያና የራሔል የላባና የዘለፋ የማባበል ቃል ምድራዊ እሹሩሩ ነው፡፡ ድንግል ማርያም ያቀፈችው ሕፃን ሰማያዊ ነውና እርሱን እንዴት ባለ ዝማሬ አባብላ ታስተኛው ይሆን?’’ እያለ ይጨነቃል፡፡
የድንግሊቱን አንደበት አንደበት አድርጎም እንዲህ ሲል ይቀኛል :-
"ልጄ ሆይ አባትህ ዳዊት የመዝሙሩን ሀብት በመርከብ ጭኖ ወደ እኔ ወደብ አሁን ያራግፍ፡፡ እርሱ የሳባ ነገሥታት እጅ መንሻ ያቀርባሉ ብሎ ዘምሮልህ ነበር ፤ እኔ ግን እጅ መንሻን ሲያቀርቡልህ ያየሁ ነኝ’
‘ለአንተ እንዴት ያለ የማባበል ዜማን ላዜምልህ እችላለሁ? እንደማንኛውም ሕፃን ለአንተ እሹሩሩ ብዬ እንዳልዘምርልህ እንደ ማንኛውም ሰው ተራ ልደትን የተወለድህ አይደለህም፡፡ ፅንሰትህ አዲስ ነው ፤ ልደትህም ተአምር ነው፡፡ በመንፈስ ካልሆነ ለአንተ ሊዘምር የሚችል ማን ነው?’ ይላል፡፡
በሌላ መዝሙሩም ላይ ሶርያዊው ወርቅ እንዲህ ይላል:-
‘ታናሺቱ ርግብ ጥንታዊውን ንሥር ተሸከመችው፡፡ ታቅፋውም እንዲህ ስትል ዘመረችለት ፦
በታናሽ ጎጆ ውስጥ ያለኸው ባለጠጋ ልጄ ሆይ ጥዑም በገና የሆንኸው አንተ እንደ ሕፃን ዝም ብለህ ልታድግ ወደድህ፡፡ ንዝረቱ ኪሩቤልን በሚያንቀሳቅስ በገና እንድዘምርልህ ፍቀድልኝ፡፡
ልጄ ሆይ ቤትህ ከሁሉ በላይ ከፍ ያለ ነው፡፡ እኔን ቤትህ ልታደርገኝ ግን ወደድህ፡፡ ሰማይ ክብርህን ይሸከም ዘንድ አይቻለውም፡፡ ከፍጥረታት ሁሉ ምስኪንዋ እኔ ግን ተሸክሜሃለሁ፡፡ ሕዝቅኤል ይምጣና
በጉልበቴ ላይ ሆነህ ይይህ፡፡ መጥቶ ይስገድልህና በኪሩቤል ሠረገላ ላይ ከፍ ከፍ ብለህ ያየህ አንተን እንደሆነ ይመስክር’ (St. Ephrem the Syrian , Harp of Spirit, Sebastian Broock)
ድንግል ማርያም ልጅዋን የምትጠራበት የሚበቃ ስም አጥታ ስትጨነቅም የኤፍራጥስ ወንዝ በብዕሩ ያያታል :-
‘ማን ብዬ ብጠራህ ይሻለኛል? ከእኛ ጋር የነበርህ ፤ ለእኛም እንግዳ የሆንህ ነህ፡፡ ልጄ ብዬ ልጥራህ? ወንድሜ ልበልህ? ሙሽራዬስ ብዬ ልጥራህ? ጌታዬስ ልበልህ? ከዳዊት ቤት እንደመሆኔ እኅትህ ነኝ፡፡ ስለፀነስሁህ እናትህ ነኝ ፤ ስለንጽሕናህ ሙሽራህ ነኝ ፤ መድኃኒቴ ነህና ባሪያህና ልጅህ ነኝ’ ይላል፡፡
እመቤታችን ጌታን ባሳደገችበት ወቅት ሁሉ ትልቅ እምነት የሚሻ ውጣ ውረድን አሳልፋለች፡፡ የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ ‘ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ’ ባለው ግዜ ድንግሊቱ እንድትሰደድ የተነገራት ቅፅበት በራሱ እምነትንና መታዘዝን የሚፈታተን ነገር ነበር፡፡
እርስዋ ግን ‘የተነገረኝ አምላክን እንድወልድ እንጂ ከተወለድሁበት ሀገር እንድሰደድ አልነበረም፡፡ ከሔሮድስ ለመሸሽ ግብፅ ድረስ መሔድ ለምን አስፈለገ?’ ብላ ልትጠይቅ ትችል ነበር፡፡
ብዙ ሰዎች ‘እነሆኝ’ ብለው እግዚአብሔርን ይቀበሉትና መከራ ሲመጣባቸው ‘በዙፋንህ የለህም’ እስከማለት ይደርሳሉ፡፡ ድንግሊቱ ግን መከራ እምነትዋን አላናወጸውም፡ ፡ ልጅዋን ከሔሮድስ ይዛው ስትሸሽ እርሱ ኃይል አምላክ መሆኑን አልተጠራጠረችም፡፡
ለሰብአ ሰገል ‘እንድሰግድለት መጥታችሁ ንገሩኝ’ ብሎ አሳቢ መስሎ ሐሰትን የተናገረውና የሰይጣን መሣሪያ የሆነው የሐዲስ ኪዳኑ እባብ ሔሮድስ ሠራዊቱን ‘ከኋላዋ እንደወንዝ ሲያፈስስባት’ አይታ እምነትዋ አልተናወጸም፡፡ ማቴ. ፪፥፰ ፤ ራእ. ፲፪፥፰
‘እስራኤልን በኤርትራ ባሕር ዳርቻ ፈርዖን ከነሠራዊቱ እንዳይደርስባቸው የደመና ዐምድ አቁመህ የከለልካቸው አንተ አይደለህምን? ስደት ከምወጣ ሔሮድስ እንዳይደርስብኝ ዙሪያዬን በእሳትና በደመና የማታጥርልኝ ለምንድን ነው?’ አላለችም፡፡
ስደት ወጥታ በግብፅ በረሃ እንደ ወፍ ስትንከራተት የፀሐዩ ሙቀት ፣ የአሸዋው ግለት ፣ ረሃቡና ጥሙ ሲጸናባት ፣ ጌታን አንድ ጊዜ በጀርባዋ ፣ አንድ ጊዜ በጎንዋ በማዘል በደከመች ጊዜ ‘አምላክ መሆንህ ለዚህ ቀን ካልሆነ ለመቼ ነው? ለምን ተአምርህን አትገልጥም? እንዲህ ከምንደክም በአምላካዊ ኃይልህ በነፋስ ተጭነን ፣ በደመና ተሳፍረን ፣ በእሳት ሠረገላ እየጋለብን ለምን ቶሎ አንደርስም? በፀሐይ ግለት ከምንቃጠል በደመና የማትጋርደን ስለምንድን ነው? እስራኤልን መና አውርደህ የመገብህ ሆይ መና ከሰማይ አውርድ እንጂ ፣ በጥም ከምንሠቃይ ከዓለት ላይ ውኃን አታፈልቅምን?’ ብላ ፈጣሪዋን አልተፈታተነችም፡፡
‘ጌታ ራሱ ምልክት ይሠጣችኋል ፤ እነሆ ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች’ እንደሚል ከታቀፈችው ሕፃን የበለጠ ሌላ ምልክትን አልፈለገችም፡፡ ኢሳ. ፯፥፲፬
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ :-
‘ወሶበሂ ወለደቶ ዐቀበ ድንግልናሃ ዘእንበለ ርኲስ፡ ከመ በፅንሳ መንክር ትኩን መራሂተ ለሃይማኖት ዐባይ’ ‘ድንቅ በሆነ ፅንስዋ ለታላቁ ሃይማኖት መሪ ትሆን ዘንድ ከወለደችም በኋላ ያለመለወጥ በድንግልና አጸናት’ እንዳለ ድንግል ማርያም ለብዙዎች ማመን ምክንያት የሆነ ታላቅ እምነት ያላት መራሂተ ሃይማኖት (የሃይማኖት መሪ) ናት፡፡(ሃይማኖተ አበው ፤ ዘቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ፷፮፥፴፪ )
እርስዋ አምላክ ሰው ይሆናል ፣ ከእኔ በድንግልና ይወለዳል ብላ ማመን መቻልዋ በስሙ ለምናምን ሁሉ የእምነታችን መሠረት ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ‘ወደ ማርያም ከመጡት ... ብዙዎች በእርሱ አመኑ’ ተብሎ ከተጻፈላት ከአልዓዛር እኅት ማርያም በላይ የእመቤታችን እምነት ለክርስቲያኖች ሁሉ መሠረተ ሃይማኖት ነው፡፡ ዮሐ. ፲፬፥፵፭
‘በሐዋርያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል’ ተብሎ የተነገረላቸው የእምነታችን አእማዶች የሆኑት የጌታችን ደቀ መዛሙርትም እምነታቸው ባመነችው ብፅዕት ምክንያት የመጣ እንደነበረ አስተውለነው ይሆን? ኤፌ. ፪፥፳
ደቀ መዛሙርቱ በጌታ ስለማመናቸው የተጻፈው የመጀመሪያው ቃል ‘ኢየሱስ ይህን የምልክቶች መጀመሪያ በገሊላ ቃና አደረገ፤ ክብሩንም ገለጠ፥ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ’ የሚል ነው፡፡ ዮሐ. ፪፥፲፩ በዚህ ሰርግ ቤት ድንግል ማርያም የነበረች ቢሆንም ‘ማርያምም በእርሱ አመነች’ የሚል ቃል አልተጻፈም፡፡ የቃናውን ተአምር ተከትሎ ያመኑት አዳዲስ አማኞች የሰርግ ቤቱ ንዑሰ ክርስቲያን ደቀ መዛሙርቱ ነበሩ፡፡ ድንግል ማርያም ግን በልጅዋ ሁሉን ቻይነት ከማንም ቀድማ ስለምታምን ውኃ ወይን እስኪሆን ማየት አላስፈለጋትም፡፡
ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንዳለ :-
‘ወባሕቱ አእመረት ከመ በጽላሎተ አብ ፀነሰቶ ወበኃይለ ልዑል ወለደቶ ወሰአለቶ በእንተ ወይን’ ‘ነገር ግን በአብ ጥላ እንደ ፀነሰችው በልዑል ኃይልም እንደወለደችው ታውቃለችና ስለ ወይን ማለደችው’ ድንግሊቱ ክርስቶስ ውኃን ወይን ከማድረጉ በፊት ድንግልዋን ሳይነካ እናት ሲያደርጋት አይታለች፡፡ ስለዚህ አምላክ ሰው ሲሆን ያየች ድንግል ውኃ ወይን ሲሆን አይታ ልትደነቅና እንደ አዲስ ልታምን አትችልም፡፡
እመቤታችንን አምላክን ለመውለድ ክብር ያበቃት ‘ይሁንልኝ’ ብላ የተቀበለችበት እምነትዋ ነበር፡፡ ከሁሉ በላይ የምናመሰግናትም ጌታን ፀንሳ ከመውለድዋ በላይ ለዚያ ክብር ላበቃት እምነትዋም ነው፡፡ ‘መቼም አንዴ ወልዳዋለችና እናመስግናት’ ብሎ የሚያስብ ሰው እመቤታችን አምላክ ባደረበት ሥጋዋ ብቻ ሳይሆን እምነትን በተሞላች ነፍስዋ ጌታን ያከበረች መሆንዋን ያላወቀ ሰው ነው፡፡
አንዲት ሴት ወደ ጌታችን መጥታ :-
‘የተሸከመችህ ማኅፀንና የጠባሃቸው ጡቶች ብፁዓን ናቸው አለችው’ አለችው፡፡ ጌታችን ‘አዎን፥ ብፁዓንስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚጠብቁት ናቸው አለ’ ሉቃ. ፲፩፥፳፯
ሴቲቱ ለጌታ እናት ያቀረበችውን ምስጋና ክርስቶስ በመጀመሪያ ‘አዎን’ ብሎ ተቀበለው፡፡ ‘ቃላችሁ አዎን አዎን ወይም አይደለም አይደለም ይሁን’ ብሎ የተናገረው ጌታ ‘አዎን’ ብሎ መናገሩ ትልቅ የማጽናት ንግግር ነው፡፡ ማቴ. ፭፥፴፯
ሆኖም ለእናቱ ማሕፀንና ጡቶች የቀረበውን የወንጌል መልክዓ ማርያም ምስጋና በአዎንታ ቢቀበለውም የሚበልጠው ነገር ግን ምን እንደሆነ ግን ጨምሮ ተናገረ፡፡ ሴቲቱ ድንግል ማርያምን ያመሰገነቻት ጌታን በማሕፀንዋ መሸከምዋ እና ጡቶችዋን በማጥባትዋ ብቻ ነበር፡፡ እርግጥ ድንግሊቱ ለፀነሰችበት ማሕፀን እና ፈጣሪዋን ለመገበችባቸው ጡቶችዋ ምስጋና እናቀርባለን፡፡ ሆኖም ጌታን ለመፅነስና ለማጥባት ያበቃት ከእግዚአብሔር ዘንድ የተነገራትን ቃል ሰምታ ማመንዋና በልብዋ መጠበቅዋ ነው፡፡
ኤልሳቤጥ ለድንግል ምስጋና ስታቀርብም ጌታን ስለፀነሰች ከማመስገን ይልቅ ‘ከጌታ የነገሩሽ ቃል ይፈጸማልና ያመንሽ ብፅዕት ነሽ’ ያለችውም እመቤታችን ለመውለድ የሚያበቃት እምነትዋ ታላቅ በመሆኑ ነው፡፡
ሊቁ አውግስጢኖስ ‘ማርያም ቡርክት የሆነችው ጌታን ከመፅነስዋ በፊት በእርሱ በማመንዋ ነበር፡፡ ‘የተሸከመችህ ማሕፀን የተመሰገነች ናት’ ሲባልም ‘ይልቅስ ብፁዓን ቃሌን ሰምተው የሚጠብቁት ናቸው’ ስለዚህ ነው፡፡ በሥጋ ዘመዶቹ የሆኑትና በእርሱ ያላመኑት ሰዎች ጥቅማቸው ምንድን ነው? ድንግል ማርያም በልብዋ በእምነት ባትፀንሰው ኖሮም በሥጋዋ ለመፅነስ ባልበቃች ነበር’ ብሏል፡፡ (St. Augstine, Holy Virginity 3, Anicent Christian Commentaries on Scripture, NT III)
ለክርስቲያን ሁሉ ተስፋውም ይህ ነው፡፡ መልአኩ ሳትፀንስ በፊት ‘ጌታ ከአንቺ ጋር ነው’ እንዳላት ድንግል ማርያም ጌታን በማሕፀንዋ ለመፅነስ ያበቃት አስቀድሞ በእምነት በልብዋ ፀንሳው ስለነበረ ነው፡፡ ጌታ በሥጋ የተወለደው አንድ ጊዜ ነውና እሱን በሥጋ የመፅነስ ዕድል ከድንግሊቱ በቀር ለማንኛዋም ሴት ሊደርሳት አይችልም፡፡ ሆኖም አንድ ተጨማሪ ዕድል ግን ለሴቶች ሁሉ ተሠጥቶአል፡፡
አባ መቃራ ለአንዲት መነኩሲት እንዲህ ሲል እንደነገራት ፦
‘ይደሉኬ ላዕሌኪ ኦ እኅት ከመ ትጹሪዮ ለእግዚእ
በልብኪ በከመ ጾረቶ እግዝእትነ ማርያም በከርሣ’ ‘እኅት ሆይ እመቤታችን ማርያም በማሕፀንዋ እንደተሸከመችው አንቺም ጌታን በልብሽ ትሸከሚው ዘንድ ይገባሻል’ (መጽሐፈ መነኮሳት ፤ ፊልክስዩስ ፤ ተስእሎ ፹)
እመቤታችን ጌታን በእምነት በመፅነስ ያገኘችውን ብፅዓን ክርስቲያኖች ሁሉ በእርሱ በማመን ያገኙታል፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም ይህን አንቀጽ በተረጎመበት ሥፍራ ፦
‘የተሸከመችህ ማሕፀን የተመሰገነች ናት ይላል፡፡ ክርስቶስ ከፀነሰችው ድንግል በረከትን እየወሰደ በእርሱ ለሚያምኑበት ሁሉ ያድላቸዋል፡፡ ይህ በረከት አስቀድሞ ከድንግል ማርያም ጋር ብቻ የነበረ በረከት ነበረ፡፡ አሁን ግን ከሚያምኑበት ሁሉ ጋር ለዘላለም ይኖራል፡፡ ብፁዓንስ ቃሉን ሰምተው የሚጠብቁት ናቸው የተባለውም ለዚህ ነው’ በማለት ያመነችው ብፅዕት ድንግል ማርያም ለምእመናን ሁሉ የበረከት ምንጭ መሆንዋን አስረድቷል፡፡ (St. Ephraim the Syrian, Commentary on Tatian’s Diatessaron 11.10)
ቅዱስ ባስልዮስም ክርስቲያኖች ሁሉ የክርስቶስን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ከመቀበላቸው በፊት እንዲጸልዩት በደረሰው የውዳሴ አምላክ ጸሎት ላይ ድንግል ማርያምን እንዲህ ይላታል :-
‘ከንጹሐን ይልቅ ንጽሕት የኢየሱስ ክርስቶስ እናት ሆይ ባንቺ የተፀነሰን አምላክ ዛሬ የምቀበለው ነኝ፡፡ አንቺ የኢየሱስ ክርስቶስ እናት እንድትሆኚ በሰው ሁሉ የደረሰ የአዳም ኃጢአት ስንኳ አልደረሰብሽም፡፡ እኔ ግን ኃጢአት የሠራሁ ስሆን ያንቺን ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስን ልቀበል ወደ ቍርባን እቀርባለሁ፡፡
መሓሪት እናት ሆይ ክፋቴ ብዙ ነውና እርሱን
ስቀበል እንዲምረኝ እያዘንሽ አማልጂኝ፡፡
የእኔ መቀበል ክቡር ልጅሽን ማዋረድ መናቅ እንዳይሆን እርሱን ልጅሽን በምትቀበይበት ጊዜ የተደረገን የአንቺን መዘጋጀት ያንቺን ትሕትና ያንቺን ንጽሕና ስለ እኔ ፈንታ እንድታቀርቢልኝ እለምናለሁ’ (ቅዱስ ባስልዮስ ፤ ውዳሴ አምላክ ፤ ዘአርብ ቁጥር 2 305)
ይህ ከአባቶቻችን የተማርነው ወደ አመነችው ብፅዕት
የምናቀርበው ይህ ዓይነቱን ጸሎት ነው፡፡ የእርስዋን ወደር የሌለው እምነትና ቅድስና ባየን ጊዜ ከበረከትዋ ቆርሳ ሠጠን ዘንድ እንማጸናታለን፡፡ እርስዋ ለእርሱ ማደሪያው የሆነችለትን አምላክ በሕይወታችን እንዲያድር እየናፈቅን እንለምናታለን፡፡
ድንግል ሆይ ወደ አንቺ መጥቶ ጸጋን የተሞላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ያለሽ መልአክ ዛሬም ወደ እኔ ይምጣ፡፡ ኃጢአት ያደቀቃት በኀዘን የተዋጠች ነፍሴን ከጸጋ የተራቆትሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ይበላት፡፡ ጌታ በእኔ ልብ እንዳይፀነስ ‘ያለ ኃጢአት መኖርን ስለማላውቅ እንዴት ይሆንልኛል?’ ብልም ወደ አንቺ የመጣው መንፈስ ቅዱስ ወደ እኔ በምሕረት ይምጣ፡፡ በእስራኤል ልጆች ሠፈር መና እንደወረደ የልጅሽ ምሕረት በእኔ ላይ ይውረድ፡፡
አንቺን ድንግልናን ከማጣት እንደ ጋረደሽ እኔን ከኃጢአት ይጋርደኝ፡፡ አንቺን አምላክን ለመውለድ ያጸናሽ አብ እኔን ልጅሽን በማመን ያጽናኝ፡፡ አንቺ በማሕፀንሽ ዘጠኝ ወር የፀነስሽውን ጌታ እኔ ለደቂቃዎች እንኳን በልቤ እንድፀንሰው ፍቀጂልኝ፡፡ የፀነስሁትን የኃጢአት ሃሳብ ከልቤ አውጥተሽ በሕሊናዬ ልጅሽ እንዲያድር ለምኚልኝ፡፡ ጌታን በእጆችሽ መሃል የያዝሽው ሆይ አንቺ ጌታን ለዓመታት ታቀፈሽው ነበር፡፡ እኔ ግን ለአንድ ቀን እንኳን ሰውነቴ ከኃጢአት አርፎ እሱን ብቻ ታቅፌ እንድውል ፍቀጂልኝ፡፡
እርግጥ ነው ወደ እኔ ልጅሽን ይዘሽ ስትመጪ እንደ ቤተልሔም የእንግዶች ማደሪያ የእኔም ልብ የብዙ እንግዳ ኃጢአቶች ማደሪያ ነውና ልጅሽን ለማስተኛት ቦታ የለኝም ብዬ የልቤን በር ልዘጋብሽ እችላለሁ፡፡
በሩን ብዘጋውም ግን ልጅሽ እንደሆነ ‘በደጅ ቆሞ ማንኳኳት’ እንደማይሰለቸው አውቃለሁ፡፡ ራእ.፫፥፳
እኔ ፈቅጄ ባልከፍትለትም እንኳን የድንግልናሽን ማኅተም ሳይከፍት እንደተወለደ የእኔን የተዘጋም
ልብ ሳይከፍተው መግባት አይሳነውም፡፡ ስለዚህ ዐመፄና እምቢታዬን ቸል ብለሽ ለልጅሽ ማደሪያ አድርጊኝ፡፡ አንቺ እርሱን ከወለድሽ ወዲያ በታተመ ድንግልና ጸንተሽ እንደኖርሽ ለልጅሽ ማደሪያ ሆኜ ለሌላ የኃጢአት ፅንስ ዳግም ማደሪያ እንዳልሆን ነፍሴን አትሚልኝ፡፡
የወለድሽው መድኃኒት እኔን ዙፋኑ አድርጎ ቢቀመጥ ሰዎች በእኔ እቅፍ ስላለ ብቻ በእኔ ምክንያት እንደ ሰብአ ሰገል እንደሚሰግዱለት በአንቺ ሲሆን አይቻለሁና ሰዎች በእኔ ምግባር ምክንያት ፈጣሪን
መስደብ ትተው እጅ መንሻ ያቅርቡለት፡፡ ለልጅሽ በቀረቡ ሥጦታዎች ተከብቤ ከአንቺም ጋር ፦ ‘ጌታ ሆይ ለአንተ የሚሰግዱልህ ሰዎች ዙሪያዬን ከበቡኝ ፤ ለአንተ በቀረቡ ሥጦታዎችም ዙሪያዬን ታጠርኩ’
ብዬ ላመስግነው፡፡ (St. Ephrem the Syrian, Hymns on the Nativity, Desert Fathers Series Vol. 5 Hymn X)
ድንግል ሆይ አንቺን ያሳደደሽ ሔሮድስ እኔን የማያሳድደኝ ጌታ በእቅፌ ስለሌለ ነው፡፡ እኔ በልቤ ያነገሥሁት ‘የተወለደውን የአይሁድ ንጉሥ’ ስላልሆነ ሔሮድስ ከእኔ ጋር ጠብ የለውም፡፡ የሔሮድስን ሥልጣን አደጋ ላይ የሚጥል ንጉሠ ሰላም በእኔ እቅፍ የለም፡፡
አሁን ግን ፍቀጂልኝና ሔሮድስን ማስደሰት ትቼ ልጅሽን በልቤ ልቀበለው፡፡ የልቤን ክርስቶስ ሔሮድስ እንዳይገድልብኝ እኔም እንደ አንቺ ልሰደድ፡፡ እሱን አቅፌ መከራ ቢደርስብኝ እንኳን ጽናት እንደማገኝ በአንቺ አይቻለሁና የልጅሽን ፍቅር በልቤ አኑሪልኝ፡፡ ለሦስት ቀናት ከፊትሽ ዞር ቢል ፍለጋ የወጣሽዋ ድንግል ሆይ ከእኔ ሕይወት ልጅሽ ከተሠወረ ቆይቶአልና ያለ እርሱ መሰንበት የማልችል የፍቅሩ ምርኮኛ አድርጊኝ፡፡
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ግንቦት 1 2015 ዓ.ም.
ከ"ብርሃን እናት" መጽሐፍ ለግንቦት ልደታ ዝክር የተቆረሰ
25/11/2022
04/11/2022
ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከዓመታት በፊት አንድ ቤተ ክርስቲያን መሠረቱ:: ይህንን የጥቁሮች ቤተ ክርስቲያን በሥራቸው ለማድረግ ብዙ የእምነት ተቋማት መረባረብ ጀመሩ:: የሮማ ካቶሊክ ፣ የአንግሊካን ወዘተ በብዙ ቁጥር የተሰባሰቡትን ደቡብ አፍሪካውያን ለመማረክ ያላደረጉት ጥረት አልነበረም::
ምእመናኑ ግን ለማንም እጅ አልሠጡም:: ለሚጠይቃቸው ሁሉ መልሳቸው አንድ ነበረ::
"እኛ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ነን"
በኢትዮጵያ ስም ለመሰብሰባቸው ምክንያቱ "ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች" የሚለው የንጉሥ ዳዊት መዝሙርና የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ታሪክ ነበረ:: ምንም እንኳን ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሕጋዊ እውቅና ባይሠጣቸውም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን በፍቅር እየጠበቁ ተሰብስበው መጽሐፍ ቅዱስን መማራቸውን ቀጠሉ::
ድንገት ግን የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ ላይ ለመካፈል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የካሪቢያን ሊቀ ጳጳስ የነበሩትና ቦብ ማርሌይን (ብርሃነ ሥላሴ) ጨምሮ በሺህዎች የሚቆጠሩ ጃማይካዊያንን በማጥመቅ የሚታወቁት ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ ወደ ደቡብ አፍሪካ ይመጣሉ:: ይህንን የሰሙት የደቡብ አፍሪካ ምእመናን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ልጆችዋን ትሰብስበን ብለው ብፁዕነታቸውን ይጠይቃሉ:: በዚህ ልባቸው የተነካው አቡነ ይስሐቅም ከምእመናኑ ጋር ሰንብተው በቂ ትምህርት ከሠጡ በኋላ ከመካከላቸው በዕድሜ የበሰሉትንና በበጎ ሥራቸው የተመሰገኑትን በሐዋርያዊው ትውፊት መሠረት ክህነት ሾመው ሕዝቡን ቀድሰው አቁርበው ተመለሱ:: በዚህም የደቡብ አፍሪካውያን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተወለደች::
በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ዘመነ ፕትርክና ደግሞ ቅዱስነታቸው ሥፍራውን በአካል ተገኝተው ምእመናኑን በመጎብኘትና በመደገፍ ከልጆቻቸውም ዲያቆናትን በመሾም የተተከለችውን ቤተ ክርስቲያን የተንከባከቡአት ሲሆን በሥፍራው በሊቀ ጵጵስና ተሹመው ባገለገሉት በብፁዕ አቡነ ያዕቆብም የምእመናኑና የካህናቱ ቁጥር በዝቶ ቅዳሴ በራሳቸው እስከመቀደስና ምሥጢራትን ሁሉ እስከመፈጸም ደርሰዋል:: "ይስሐቅ ተከለ ያዕቆብ አጠጣ እግዚአብሔር ያሳድግ ነበረ" ነው ነገሩ::
ደቡብ አፍሪካውያኑ ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እቅፍ እስኪገቡ ድረስ እጅግ ብዙ ዋጋ ከፍለዋል:: በወቅቱ ብዙ ዋጋ ከከፈሉ ሰዎች መካከል ፋዘር ዴሊዛ አንዱ ናቸው:: በደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያዎቹ ካህናት ውስጥ አንጋፋ የሆኑት ፋዘር ዴሊዛ ከገንዘብ ሥጦታ ማባበያ እስከ ግድያ ሙከራ ድረስ ታግሠው ቤተ ክርስቲያንዋን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እንድትሆን ያስቻሉ ብርቱ ካህን ነበሩ:: እኚህ ውድ የቤተ ክርስቲያን አባት በዚህ ሳምንት ወደ አምላካቸው እንደተጠሩ ሰማሁ::
በደቡብ አፍሪካ በአገልግሎት ላይ በቆየሁ ጊዜ ከፋዘር ዴሊዛ ጋር የማይረሳ ጊዜ አሳልፌያለሁ:: ፋዘር ዴሊዛ እጅግ ጨዋታ አዋቂ ፣ በጣም የሰላ አእምሮ ያላቸው ፣ ጸሎተኛና ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚቆጩና የሚቆረቆሩ አባት ነበሩ:: የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች የደቡብ አፍሪካ ምእመናንን በመንከባከብና በማስተማር ዙሪያ ብዙ ዕዳ እንዳለብን አበክረው ይናገሩ ነበር::
የጆሃንስበርግ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ጉባኤ አገልግዬ ስጨርስ ፋዘር ዴሊዛ "የዛሬው ትምህርት ምን ነበር?" ብለው አስጨንቀው ሙሉ ትምህርቱን በትርጉም ያስደግሙኝ ነበር:: ሰምተውት የማያውቁትን ነገር ሲሰሙ "ይሄን እስካሁን መስማት አልነበረብኝም? እናንተ እኮ ትጠየቃላችሁ" ይሉ ነበር::
ፋዘር ደሊዛ ከግሪካዊትዋ የመጻሕፍት ወዳጅ ጋር ያስተዋወቁኝን ቅጽበትም አልረሳውም:: አንድ ጠዋት የEastern Orthodx book store በGoogle map ላይ ፈልጌ አገኘሁ አልኳቸው:: እሳቸው ግን "ጊዜህን አታቃጥል" አሉና ዝም አሉ:: አልሰማ ብዬ ስንከራተት ውዬ የተባለው ሥፍራ ስደርስ አቧራ የቃመ የተዘጋ ቤት ሆኖ አገኘሁት:: በማግስቱ ሳገኛቸው ፈገግ እያሉ "የሔድክበት ተሳካልህ" አሉኝ::
እየተበሳጨሁ ነገርኳቸው:: እሳቸውም እየሳቁ "ነገርኩህ እኮ ከእኔ ይልቅ ጉግልን እንዴት ታምናለህ?" አሉ::
ከሳምንት በኋላ በጠዋት መጥተው ቀሰቀሱኝ:: (ተቀስቅሶ መነሣት እንደማልወድ ደጋግሜ ብነግራቸውም ፋዘር ዴሊዛ አልሰሙኝም:: "እባክዎን አያንኳኩ" ብዬ ቃል አስገብቻቸው እሺ ብለው በማግሥቱ መጥተው ሞቅ ባለድምፅ በር ላይ "እእህህህምምምም እህህህምምም" ብለው የቀሰቀሱኝን አልረሳውም:: ተበሳጭቼ ስጠይቃቸው "አያንኳኩ ነውያልከኝ አላንኳኳሁም" ብለው ሳልፈልግ አስቀውኛል:)
ያን ቀን በጠዋት ቀስቅሰው አንዲት ግሪካዊት ጋር አስተዋወቁኝ:: በቤትዋ ብዙ መጻሕፍት የምትሰበስብ ነበረች:: በግዢም በሥጦታም ብዙ ነገር አገኘሁ:: መጻሕፍት ጭነን ስንወጣ ፋዘር ዴሊዛ "Who ya gonna believe, Me or your Google map?" ብለው ቀለዱ::
ፋዘር ዴሊዛ ገንዘብ የሚያጠራቅሙባት ትንሽ ሳጥን ነበረቻቸው:: ለምን እንደሆነ ጠየቅኳቸው:: የክህነት አባታቸውን የአቡነ ይስሐቅን መቃብር የመጎብኘት እቅድ እንዳላቸው ነገሩኝ:: እኔም ትንሽ አዋጣሁ:: ከደቡብ አፍሪካ መልስ በወራት ልዩነቶች ይደውሉልኝ ነበር:: እኚህ ድንቅ አባት በክብር አርፈዋል:: መቃብራቸውን ለማየት ያልተሳካላካቸው መንፈሳዊ አባታቸውን አቡነ ይስሐቅንም በአጸደ ነፍስ ያገኙአቸዋል:: ዕረፍተ ነፍስ ይሥጥልን:: ለመንፈሳዊ ልጆቻቸው ሁሉ መጽናናትን ያድልልን::
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጥቅምት 2015 ዓ.ም.
አዲስ አበባ ፤ ኢትዮጵያ
ፎቶ:- 2006 ዓ.ም. ከአባታችን ጋር የተነሣሁት ነው::
31/10/2022
🍂ከሽፍቶቹም አንዱ #ጌታችንን በራሱ ተሸክሞ እንደሸኛቸው +
እንዲሁም ጌታችን የተሰበረ ሰይፉን እንደቀድሞ እንዳደረገለት
የሚናገር ተአምር ፤ ከስዕሉ ጋር ተስማምቶ የቀረበ
+ ________ + + + ________+
ያደረገው ተአምር ይህ ነው ። ይህ ተአምር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከግብፅ አገር ስለመውጣቱና በጐዳና በበረኃ ወንበዴዎች ባገኙት ጊዜ ያደረገው ልዩ ልዩ ተአምር ነው ።
እንደዚሁም ሁሉ ለኛ የቸርነቱን ምልክት ያድርግ በዕውነት ለዘላለሙ።
🍂+
፤ ከዚህም በኋላ በምድረ ግብፅ የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ ተገልጾ ተነሥ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ፍልስጥዔም ምድር ተመለስ ። እነሆ ሕፃኑን ሊገድለው የሚፈልገው ንጉሠ ሄሮድስ ሞቷልና አለው።
🍂+
ዮሴፍም የእግዚአብሔር መልአክ እንደነገረው ሕፃኑንና እናቱን ይዞ ወደ ፍልስጥዔም አገር ለመሄድ ተነሣ፤ በጐዳና ሲሄዱ ሁለት ወንበዴዎች አገኙዋቸውና አስፈራሯቸው ። አንደኛው ወንበዴ ግን ልቡ ራራና ሕፃኑን ከእናቱ ክንድ ወስዶ ዓይኖቹን ጐንጮቹን እጅ ነሣቸው።
🍂+
ንጽሕት ድንግል የምትሆንም ለእመቤታችንም ገንዘባችሁን እንዳንቀማችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ በተባለ በዚህ ሕፃን ስም ቃል እንገባለን አላት ። ዳግመኛም ጓደኞቹን ከነዚህ ሰዎች ገንዘብ የሚደርሳችሁን ለኔ ተዉልኝ ። በዚህ ፈንታ እኔ ከሌላው ድርሻዬ እከፍላችኋለሁ አላቸው።
🍂+
ዮሴፍም ሕፃኑንና እናቱን ይዞ ሲጓዝ ወንበዴው በፊት ለፊት እየሄደ መንገድ ይመራቸው ነበር። በዚህም ያ ጊዜ ያ ወንበዴ በእንቅፋት ሲሰነካከል ሰይፉ ከድንጋይ ላይ ወደቀና ከሦስት ቦታ ላይ ተቆራረጠ ። ሕፃኑም ጥጦስ ሆይ ፤ የሰይፍህን ስብርባሪ ሰብስበህ አምጣ አለውና መንበዴው ጥጦስም ስብርባሪውን ሰብስቦ ሰጠው። በዚህም ጊዜ ሕፃኑ ጌታ ኢየሱስ ከርስቶስ ስብርባሪውን አገጣጠመና እንደቀድሞ አድርጐ ሰጠው።
🍂+
ወንበዴውም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰበረውን ሰይፍ ቀድሞ እንደነበረ አድርጎ ስለ ሰጠውና አስቀድሞ የማያውቀውን ስሙን አውቆ በስሙ ጥጦስ ብሎ ስለጠራው ፈጽሞ አደነቀ ። አመስግኖም ሰገደለት ። ይልቁንም አምላክነቱን ተረድቶ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በአንተ ዕምነት ጸንተው ከሚኖሩ እንደ አንዱ አድርገኝ በማለት ማለደ።
🍂+
ዮሴፍም ወንበዴውን እየሸኘው የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እጅ ይዞ በወንበዴው እራስ ላይ ጫነው ። ወንበዴውም ተጐንብሶ አቤቱ ጌታየ ሆይ በኔ ላይ ቸርነትህን አሳድረህ ባርከኝ አለው። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም መልሶ አዳምን ቀድመኸው ወደ ገነት እንድትገባ ዕውነት እልሃለሁ ቁልፉም ከአብ ዘንድ ይሰጥሃል አለው።
🍂+
ከወንበዴዎቹ አንዱም ይህን አነጋገር ሰምቶ ሳቀበት ተቀጸጸበበትም ፤ይህን ባለ ዘመኑ ሁሉ የሰው ደም ሲያፈስ የኖረ ወንበዴ ከአዳም ቀድሞ በገነት ይገባል ። መክፈቻውም ይሰጠዋል ማለቱ በዕውነት ከደቂቀ ነቢያት ወገን ቢሆን ነውን ብሎ ዘበተበት ።
🍂+
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም ሲስቅ ተመልከቶ ዳክርስ ሆይ ከጥጦስ ጋር የዘለዓለም ሕይወትን አትወርስም የጌታህንና የፈጣሪህን ቃል አላመንህምና አለው ። ወንበዴውም ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አነጋገርና ስሙን ሳያውቅ ስሙን ሲጠራው በመስማቱ በጣም ተደነቀ፥ በሃሳቡም ይህ ሕፃን ሥውሩን ነገር ያውቅ ዘንድ ሥልጣን ወይም ዕውቀት ከምን ተሰጠው በውነት ከደቂቀ ነቢያት ወገን እነደሆነ ልረዳ እፈልጋለሁ አለ
🍂+
የተማረ የሆነ የወንበዴዎች አለቃም መልሶ በዕውነት የዓለም መድኃኒት ክርስቶስ የተባለ ይህ ሕፃን ነው ። እናቱም ይህቺ ድንግል ናት አለው ። ከዚህም በኋላ ተለያይተው ወደየበዓታቸው ሄዱ ። ዮሴፍ ግን ሕፃኑንና እናቱን ይዞ ወደ ናዝሬት ሄደ ። የሰማይና የምድር አምላክ በመጣ ጊዜ ናዝራዊ ይባላል ሲል ነቢዩ የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ ግድ አለውና።
🍂+
ግብጻዊው ነቢይም እግዚአብሔር በኋለኛው ዘመን በናዝሬት በተገለጸ ጊዜ መንግሥትን ፤ ክህነትን ትንቢትንም ከእሥራኤል ልጆች ወስዶ ገንዘብ ያደርጋል ፤ እነሱን ግን በዓለም ላይ ይበትናቸዋል ። ከዚያም ተመልሰው በቀደመ ሥርዓታቸው ጸንተው ሊኖሩ አይችሉም ብሏልና።
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም ናዝሬት ገብተው በተቀመጡበት ጊዜ ታላላቅ ተአምራትን ማድረግ ጀመረ ።
/ ተአምረ ኢየሱስ /
_________________________
🍂 ይቅርታው ቸርነቱ ለዘላለሙ በዕውነት 🍂
🙏 ለሁላችን ይደረግልን ። 🙏
ሠዓሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እንደሚገባ አድርገው
እንዲህ ሥለውታል :
Kesis Amare Kibret
ሠዐሊ ዲ/ን ጌታባለው አማረ
t.me/deacongetabalewamare
30/10/2022
በአዲሱ ኪዳን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከበሮ ሲሰራ በምሳሌ ነው ይኸውም ምሳሌ ጌታችን እኛን ለማዳን የከፈለውን ዋጋ የደረሰበትን እትራት በጥቂቱም ቢሆን ገላጭ እንዲሆን ተደርጎ ነው ።
30/10/2022
https://www.facebook.com/100018732784016/posts/1114441669190249/
+ ጌታ ሆይ ይህን ውኃ ሥጠኝ +
ሳምራዊትዋ ሴት በጠራራ ፀሐይ ውኃ ልትቀዳ እንስራዋን ይዛ ከጉድጓድ አጠገብ ተቀምጣለች፡፡ በጠዋት ወይም በማታ ውኃ መቅዳት ስትልችል ፀሐይ አናት በሚበሳበት በስድስት ሰዓት መምጣት እንዴት ልትመርጥ ቻለች? ከጎረቤቶችዋ ጋር እየተጫወተች አብራ ቀድታ መመለስ አትችልም ነበር? ብቻዋን ለመቅዳት ለምን ፈለገች? ከሰው ፀሐይ ያስመረጣት ምንድነው? ዝርዝሩን እርስዋ ናት የምታውቀው፡፡
አምስት ባሎች የነበሩዋት እና አሁንም ባልዋ ካልሆነ ሰው ጋር የምትኖር ሴት መሆንዋ ግን ተጽፎአል፡፡ ለብዙ ወንዶች ሚስት በሆነች ቁጥር ስለራስዋ የሚኖራት ግምት እየወረደ መምጣቱ አይቀርም፡፡ በተደጋጋሚ አልሳካ ባላት ትዳር ምክንያት ልብዋ እየቆሰለ ተስፋ እየቆረጠች ሁሉን ነገር እየጠላች መምጣትዋ አይቀርም፡፡ እርስዋ ስላልተሳካው ትዳርዋና አሁንም ባልዋ ካልሆነ ሰው ጋር ስለመኖርዋ ሰዎች የሚያወሩት ግን ብዙ ነው፡፡ የእርስዋን ሕመም ሳይረዳ እንደ ርካሽ የሚቆጥራት ፣ ዝሙተኛ አድርጎ የሚያስባት ፣ ዕድለ ቢስ አድርጎ የሚፈርጃት በንቀት በአሽሙር ባለ አምስት ባሎች አድርጎ የሚነቁራት ሰው አይጠፋም፡፡ በግልጥ ባይነግሯትም በአስተያየት በአነጋገር የሚያሳቅቋት አይጠፉም፡፡ ስለዚህ ከሰው አፍ ፀሐይ ይሻለኛል ብላ መጣች፡፡ ሰዎች በነገር ከሚጠብሱኝ በፀሐይ ብትጠብሰኝ ይሻለኛል ብላ በበረሃማው ምድረ በዳ በአጉል ሰዓት ይህች ተስፋ ያጣች ምስኪን ውኃ ልትቀዳ ሔደች፡፡
“ኢየሱስም በሰማርያ ሊያልፍ ግድ ሆነበት” እርግጥ ነው ከይሁዳ ወደ ገሊላ ለመሔድ በሰማርያ ማለፍን መልክዓ ምድሩ ያስገድዳል፡፡ ክርስቶስ ግን ግድ የሆነበት በመልክዐ ምድሩ ብቻ አልነበረም፡፡ የጠፋውን የሰው ልጅ ሊያድን የመጣው መድኃኒት እርሱ ነውና አንዲትን በፀሐይ የምትለበለብ ነፍስ ፍለጋ ሊሔድ ግድ ሆነበት፡፡ ከሰው ሸሽታ ምድረ በዳ የመረጠችውን ተስፋ የቆረጠች ሴት የአሕዛብ ተስፋ ክርስቶስ ሊፈልጋት ተገኘ፡፡
ወደ እርስዋ ቀርቦ ውኃ አጠጪኝ አላት ፤ አባ ጊዮርጊስ ‘’አንተ የሕይወት ውኃ ስትሆን ከሳምራዊትዋ ሴት ውኃን ለመንህ ‘’ እንዳለ የሕይወት ውኃ ክርስቶስ ውኃ ለመናት፡፡ እርሱ የተጠማው ውኃ ሳይሆን የእርስዋን ነፍስ ነበረ፡፡
እርስዋም አንተ አይሁዳዊ ስትሆን ሳምራዊት ከምሆን ከእኔ ውኃ ትለምናለህ? አለችው፡፡ እንዲህ ነው ነገሩ፡፡ የቆሰለች ነፍስ ስለ ዘር ታወራለች፡፡ ተስፋ የቆረጠች ነፍስ የዘር ጉዳይ ሲሆን ልሳንዋ ይከፈታል፡፡ ውኃ ለማጠጣት ዘር መጠየቅን ምን አመጣው፡፡ ውኃው አይሁዳዊ ነው? ወይንስ ሳምራዊ? ውኃ ጠማኝ የሚል ሁሉ ውኃ ይገባዋል እንጂ ዘሩ አይጠየቅም፡፡ እርስዋ ግን ጠየቀችው፡፡ በእርግጥ ይህች ሳምራዊት ሴት ይህን ጥያቄ የጠየቀችው ክርስቶስ መሆኑን ከማወቅዋ በፊት ነበር፡፡ ክርስቶስ መሆኑን ካወቀች በኋላ ግን ስለ አይሁዳዊነትና ስለ ሳምራዊነት ስትናገር አልተሰማችም፡፡ ‘’አንተ አማራ ስትሆን ጉራጌ ከምሆን ከእኔ ውኃ ለምን ትለምናለህ?’’ ‘’አንቺ ኦሮሞ ስትሆኚ ትግሬ ከምሆን ከእኔ እንዴት ውኃ ትለምኛለሽ?’’ በሚል ጥያቄ ሀገሩን ያጨናነቁተ ክርስቶስን ያወቁ ክርስቲያኖች መሆናቸው ግን ልብን የሚሰብር እውነታ ነው፡፡ በዚህ ጠባያችን እንደ ክርስቲያን ሳንኖር እንደ ክርስቲያን ልንሞት መሆኑ ምንኛ ያሳዝናል?
ጌታችን የሴቲቱን የዘር ጥያቄ እንዳልሰማ አለፈውና ‘’ውኃ አጠጪኝ የሚልሽ ማን መሆኑን ብታውቂ የሕይወትን ውኃ እንዲሰጥሽ ትለምኚው ነበር’’ አላት፡፡ አሁንም የተጠማው የእርስዋን መመለስ ነውና እርስዋ ያነሳችውን ርእስ ሳያነሳ የውኃ ጥያቄውን ቀጠለ፡፡ ውኃን የፈጠረ ጌታ የሴቲቱን በተሰበረ ልብ የሚፈስስ ዕንባ ተጠምቶ ውኃ ለመናት፡፡
‘’ጌታ ሆይ መቅጃ የለህም ጉድጓዱ ጥልቅ ነው’’ አለችው፡፡ እንዴት ያለ ንግግር ነው፡፡ የነፍስዋን መመለስ ለተጠማው ጌታ ይህ ምላሽ እንዴት ከባድ ነው?
እውነት ጌታ መቅጃ የለውም? እውነትስ ጉድጓዱ ጥልቅ ነው? አዎ ልክ ነው የለውም፡፡
ጌታ ሆይ መቅጃ የለህም ፤ ጉድጓዱም ትልቅ ነው፡፡ ብዙ ተስፋ የቆረጡ ነፍሳትን ፣ ወደ አንተ መመለስ የሚሹ አንተም የተጠማሃቸው ነፍሳት በጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ ወድቀዋል፡፡ የገቡበት አዘቅት ጥልቅ ነው ፤ በጥላቻ ፣ በክፋት ፣ በብዙ ተስፋ ማጣት ጉድጓድ ውስጥ የገቡ አንተ የተጠማሃቸው ነፍሳት ብዙ ናችው፡፡ ነገር ግን ሳምራዊትዋ እንዳለችው ከጉድጓዱ ማውጫ መቅጃ የለህም፡፡ ካለህ እስቲ ንገረን፡፡ ሕዝብህን ከጉድጓድ ውስጥ የሚያወጣ የአንተን ፈቃድ የሚፈጽምልህ አገልጋይ አለህ? ሁሉም ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ የቀረ አይደለምን? ራሱ መቅጃ የሚፈልግ መቅጃማ ሞልቶሃል? እንደ ኢሳይያስ ዘመን ‘’ማንን እልካለሁ’’ ብለህ ብትጣራ ይሻልሃል እንጂ መቅጃስ የለህም፡፡ ወይ ሱራፊን ልከህ በእሳት ፍሕም ተኩሰህ ካላነጻኸን በቀር መቅጃ የለህም፡፡
ሴቲቱ የያዕቆብን አምላክ ክርስቶስን ‘አንተ ከያዕቆብ ትበልጣለህ?’’ አለችው፡፡ ተስፋ የቆረጠ ሰው ንግግሩ ሻካራ ነው፡፡ ‘’አንተ ከማን ትበልጣልህ? ከእገሌ ተሽለህ ነው?’’ የሚሉ ቃላት ነፍሱ የቆሰለ ሰው ንግግሮች ናቸው፡፡ ክርስቶስ አላስቀየማትም፡፡ አመል ያሳጣት የተመረረችበት ኑሮዋ እንደሆነ ያውቃል፡፡ “የተጎዱ ሰዎች ሰውን ይጎዳሉ” (hurt people hurt people) እንደሚባለው መጉዳትዋ ከመጎዳት ነውና ክብሬን ላስጠብቅ ሳይል ታገሳት፡፡ ባል የለኝም ስትል እንኳን ‘’እውነት ተናገርሽ’’ አሁን ያለው ባልዋ ባለመሆኑ እንዲህ እንዳለች አድርጎ ከሐሰትዋ ውስጥ እውነት አወጣላት፡፡
የተቀጠቀጠ ሸንበቆ የማትሰብረው የሚጤስ ጧፍ የማታጠፋው ትሑት አምላካችን ሆይ ክፉ ንግግሮቻችን የሚፈልቁት ከክፉ አኗኗራችን ነውና እባክህን እኛንም ታገሰን፡፡ ኢትዮጰያውያን ተሳዳቢዎች ፣ ዘረኞች ፣ ነውረኞች ያደረገን የተበላሸ ሕይወታችን ነውና ይቅር በለን፡፡ በመጥፎ ንግግሮቻችን የምናሳዝንህ ፣ በእርስ በእርስ መበላላት የምናስከፋህ ሳምራዊትዋ ሴት ባሎች እንደተፈራረቁባት ብዙ ፖለቲከኞች ተፈራርቀውብን ፣ ትዳር አልሳካ ብሎን ነውና እርስዋን እንደታግስህ ታገሰን፡፡
ሴቲቱን ጌታ ታግሶ የጎደላትን ሞላላት፡፡ ‘’እኔ ከምሠጠው ውኃ የሚጠጣ ለዘላለም አይጠማም ‘’ አላት፡፡ እርስዋም ‘ጌታ ሆይ እንዳልጠማ ውኃም ልጠጣ ወደዚህ እንዳልመጣ ይህን ውኃ ስጠኝ’’ አለችው፡፡ ይህ ውኃ ‘የሕይወት ውኃ እኔ ነኝ’’ ያለው ክርስቶስ ራሱ ነው፡፡ ሴቲቱም እርሱ መሆኑን ስታውቅ እንስራዋን ጣለች፡፡ እርሱን ካገኘች በኋላ እንደማትጠማ እርግጠኛ ነበረች፡፡
ወዳጄ ሆይ እንደ ሳምራዊትዋ ሴት መመላለስ የሰለቸህ መንገድ የለም? ስትጠጣው አሁንም ጨምር የሚያሰኝህ የማይቆርጥ ጥም የለህም? ልትቀዳ የምትመላለስበት ጉድጓድስ የለም? ሁለተኛ አልሔድም ብለህ ዝተህ የምሔድበት ቦታ የለም? ሁለተኛ አልጠጣውም ብለህ የምትጠጣው ሁሌ የሚጠማህ ውኃ ምንድር ነው?
ሁሌ የሚጠማህ መላቀቅ እየፈለግህ ያልተውከው ፣ ዞረህ የምትሔድበት ፣ ታጥቦ ጭቃ ፣ አድሮ ቃሪያ ፣ ከርሞ ጥጃ የሆንህበት ልማድ የለህም? ክርስቶስ ቦታውንም ውኃውንም ያውቀዋል፡፡ ከዚህ መገላገል ከፈለግህ እንደ ሳምራዊትዋ ሴት እንዲህ በለው፦
‘ጌታ ሆይ እንዳልጠማ ውኃም ልጠጣ ወደዚህ እንዳልመጣ ይህን ውኃ ስጠኝ’’
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
መስከረም 28/ 2012 ዓ ም
ሜልቦርን አውስትራሊያ ተጻፈ
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ዘንድ ጸልዩ! ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like እና Share ያድርጉ
FB: https://www.facebook.com/officialHenokhaile/
Telegram: https://t.me/deaconhenokhaile
Instagram: https://www.instagram.com/p/CBnMF0nnhcQ/?igshid=549jvl607bv4
Youtube: https://www.youtube.com/channel/UCOaVsWC05aUjeqIEW3fWj7g
30/10/2022
ጥቅምት ፳ትሑቱና ታዛዡ አባት አባ ዮሐንስ ሐፂር አረፈ።
በአንዲት ቀን አባ ባይሞይ የደረቀ ዕንጨት አግኝቶ ወስዶ ለአባ ዮሐንስ ሰጠውና "ይህን ዕንጨት ትከለው እስከሚበቅልና እስከሚያአፈራ ድረስ ውኃን አጠጣው" አለው።አባ ዮሐንስም ለአባቱ ታዛዥ በመሆን ተቀብሎ ወስዶ ተከለው በየቀኑም ሁለት ሁለት ጊዜ ያጠጣዋል።ውኃውም ዐሥራ ሁለት ምዕራፍ ያህል የራቀ ነው።
ከሦስት ዓመትም በኋላ ያ ዕንጨት አቈጥቁጦ በቀለ።ታላቅም ዛፍ ሁኖ አበቦ ጣፋጭ ፍሬን አፈራ።አባ ባይሞይም ከፍሬው ለቅዱሳን አረጋውያን ወሰደላቸውና"የታዛዡንና የትሑቱን ፍሬ እነሆ ብሉ"አላቸው።እነርሱም ይህን ድንቅ ተአምር አይተው አደነቁ።ለመምህሮቻቸው ለሚታዘዙ እንደዚህ ያለ ጸጋ የሚሠጥ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት።
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
28/10/2022
👉 "በውስጡ የሰማይና የምድር ካርታን በመያዙ ከኹሉም ሕዋሳት የሰው ጣት ይገርመኛል። የጠቢባን ጣቶች ጥበብን ያስቀምጡበታል። የጠበኛ ጣቶች ግን የክፋት ድንጋይን ለወንድማቸው ይጨብጡበታል፤ በጽሑፉቸውም ሰውን ይረግሙበታል፣ ይሰድቡበታል"
👉 "አዋቂ ስትኾን ተፈጥሮን ትሰማለህ። ጠቢብ ስትኾን ግን ተፈጥሮ እራሷ አንተን ትሰማሃለች። ዐዋቂዎች በዩንቨርስ ውስጥ እንዳሉ ያውቃሉ። ጠቢባን ግን ዩኒቨርስ በእነርሱ ውስጥም እንዳለች ይረዳሉ"
👉 የዋዘኞች ጆሮ ሐሜትን፣ ስድብን፣ የሰውን ውድቀት መስማት ቀለቧ ነው። የዐዋቂዎች ጆሮ ግን እውነትን፣ ጥበብን፣ የሰዎችን ትንሣኤ መስማት ያስደስታታልና ብቻዋን ለትንሣኤ መድረስን ፈጣሪዋ ያድላታል"
(መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ)
💥ኢትዮጵያ ካሏት ከብራና፣ ከጥቅል በመቀጠል የሚታወቀው ብዙዎች ነገራት በአንድ ላይ አካትቶ ከያዘው "ሥንሡል" ጋር💥
👉 (የሥዕላትና የጠልሰም ዐዋቂዋ ሠዐሊት ሃይማኖት ከሠራችውና ካላት ክምችት ውስጥ ስጎበኝ አሳይታኝ ለማስታወሻ ይዤው ተነሣሁ)
25/10/2022
ጣሪያው ክፍት ሆኖ እንዴት ዝናብ አያስገባም? ዛሬ ምሽት 3፡00 በዶንኪ ትዩብ ይጠብቁን!
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
الرياض, السعودية
Riyadh
12211