Kebrom kahsay

Kebrom kahsay

Share

learn about businise
and poletical of ethiopa

discuse with our people

09/02/2023
16/06/2020

ይነበብ.,..... ሼር

✅✅ ያለፈ ነገር አይቀዪርም ፣ ላወቀበት ሰው ግን ያለፈው #ለወደፊቱ የራሱ የሆነ ትምህርት አለው ፣ ካለፈው ነገርህ ተማር እንጅ በፍፁም አታማርር ፣ ማማረር ነገህን በጎ አያደርገውም የሰዎች ሃሳብ የአንተን ማንነት አይገልፅም ፣ ማንነትህ አንተ ውስጥ ነው ያለው ፣ መልካም አድርግ ሌላውን እርሳው የሁሉም ሰው የህይወት መንገድ (ጉዞ) ይለያያል ፣ ጊዜው በደረሰ ሰው ሁኔታ አትቅና ለሁሉም ጊዜ አለው ።
:
✅✅ መኪና ገዛ ብለህ "እኔስ" አትበል ጊዜህ ሲደርስ መኪናዎች ወይም ‘ፕሌን’ ትገዛለህ ፣ ያውም ለመኖር አስፈላጊ ከሆነ ፣ ደግሞም እንዴት እንደገዛው የት ታውቃለህ ? ተወው በራስህ ላይ አተኩር ፣ ያለህ ነገር በቂ ነው ። በሰዎች ደስታ ደስ ይበልህ ፣ ክፉ አትመኝ ፣ በሃዘናቸውም አብረህ እዘን ሲያዝኑ አትደሰት ፣ ሰው ከሆንክ የሰው ነገር ይሰማህ ፣ ይህ ማለት ግን ተንኮል እየሰሩ ከሚደሰቱ ሰዎች ተደሰት ማለት አይደለም ። ሰው እያስከፋ ብሎም እየገደለ የሚደሰት አለ ፣ አንተ ከተጎዳው ሰው ጋ ሁን ፣ አስተውል ።
:
✅✅ ጊዜ የማይፈውሰውና የማይቀይረው ነገር የለም ፣ አንተም ጊዜው ይቀይርህ ዘንድ ፍቀድለት ፣ በተሰጠህ ጊዜ ለመልካም ነገር ሱሰኛ ሁን ። የስራ ጉዳይ ውስጥህ የሚችለውና የሚያምንበት ተሰጥኦ ምን አለህ ? ምን አይነት ስራ መስራት ትችላለህ ? አስተውል ጓደኛህን አትመልከት ፣ ትለያያላችሁ ፤ አለማችን በትምህርት ብቻ ወይም በጥበባት ብቻ ወይም በተወሰኑ ዘርፎች አይደለችም እየኖረች ያለችው ፣ በጣም ብዙ ነገሮች ናቸው እየደገፏት ያቆሟት ፤ አንተም ጥቂትም ብትሆን ያለህን ችሎታ አውጣው ፣ ቁፋሮ ነው ወይስ ቾክ ይዞ ማስተማር ነው ወይስ መምከር መገሰፅ ምንድነው? ቆንጆ ሽሮ ወጥ እየሰሩ መሸጥ ነው ፣ የድንጋይ ቅርፅ (ኮብልስቶን) እየሰሩ መኖር ነው ፣ ምንድነው ??? እባክህ ፈልገው አጎልብተው ጀምረው ፣ "ምን ይሻለኛል ?" እያልክ ጊዜህ እንዳያልቅ ፣ በእርግጥ ጊዜህ ሳይሆን አንተ ነህ የምታልቀው ።
:
✅✅ አስተውል ፣ መልካም ነገር ሁሉ ከፈጣሪ መጥፎ ነገር ሁሉ ደግሞ ከሰይጣን አይደለም ፣ ፈጣሪ መጥፎን ወደ መልካም የመቀዪር ብቃት አለው ። ሰይጣንም ያጠፋህ ዘንድ መልካም የሚመስል ነገር ሊያዘጋጅልህ ይችላል ፣ አስተውል ። መልካም ማሰብና መልካም መሆን መልካም ነገር እንዲገጥምህ ማመቻቸት ነው ፣ መጥፎነት ከአንተ ይራቅ ፣ ለአንተም ሆነ ለሰዎች ጉዳት እንጅ ጥቅም የለውም ።
:
✅✅ የሰራኸውና የምትሰራው ነገር የሆነ ጊዜ ላይ ዞሮ ያገኝሃል ፣ መጥፎ ከሰራህ እንደስራህ ፣ መልካም ከሰራህም እንደዚያው ይገጥምሃል ። "ሰው የዘራውን ያጭዳል" የሚለውን አስታውስ ፣ ክፉ ነገር እየዘራህ መልካም ነገር አትጠብቅ ፣ ራስህን አትሸውድ ። ጤፍ ዘርተህ ባቄላ አትጠብቅ ። ጤፍ የዘራ ገበሬ ጤፍ እንደሚያጭድ ሁሉ ፣ አንተም የዘራኸውን በእጥፍ ታጭዳለህ ።
:
✅✅ ለራስህ ስትል መልካም ሁን ፣ በጎውንም አስብ ። ለራስ ማሰብ ማስተዋል እንጅ ራስ ወዳድነት አይደለም ። ራሱን የማይወድ ሰው ሌላውን አይወድም ። አትፍረድ ፣ የመፍረድ ሃላፊነት በፍፁም የለህም ። ፍርድ የፈጣሪ ነው ፣ ለመፍረድ እንከን አልባ መሆን ያስፈልጋል ፣ ፍጥረት ሁሉ ፍጥረት በመሆኑ ብቻ እንከን አለበት ፣ ጎደሎ አለበት ። የተሻለ ሀሳብ አለኝ ብለህ ካሰብክና ከቻልክ ምከር ካልሆነ ዝም በል ።
:
✅✅ ከጓደኛህ መልካም የሆነውን ነገሩን አውጣለት ፣ አበረታታው ፣ እንደማይጠቅም አትንገረው ፣ ለሀዘኑ ሳይሆን ለደስታው ምክንያት ሁን ፣ ለስኬቱ እንጅ ለውድቀቱ መንስኤ አትሁን ። መልካም ጓደኛ ከፈጣሪ የሚሰጥ ጸጋ ነው ። መልካም ጓደኛ ፣ የማይቀና አሳቢና መካሪ ፣ ከእኔ ይልቅ ለአንተ የሚል ካለህ አንተ ተባርከሃል ታድለሃል ። ከሌለህ ደግሞ አንተ ራስህ መልካም በመሆን ጀምር ፣ ባህሪህንና ስራህን አይተው ይመጣሉ ።
:
✅✅ ያለ መጠን ማሰብ ጭንቀትን ፣ ሀዘንን ያስከትላል ። ከአቅምህ ከምትችለው በላይ አታስብ ፣ መመለስ በማትችለው ነገር ላይ አትወጠር ፣ የተመለሱ ነገሮችህ ላይ ትኩረት አታድርግ ። አንዳንድ መልሶች በድጋሚ ጥያቄወች ሆነው እንደሚመጡ አትዘንጋ ። ባልገባን ሳይሆን በገባን ነገር ላይ እናተኩር ።
:
✅✅ ደግነት ዋጋ አያስከፍልም ነፃ ነው ፣ "ያስከፍላል" ብለህ ካሰብክም ምላሹ እጥፍ እንደሚሆንልህ አትዘንጋ ። ደግ ሁኑ ፣ ደግ ሆነው የተጎዱ የሉም ፣ ቢኖሩም ከጉዳታቸው ይልቅ በረከታቸው ሰላማቸው ልክ የለውም ።
:
✅✅ ደስታህንና ሰላምህን የሆነ ሰው ወይም ነገር ላይ አታስቀምጥ ፣ ያ ነገር ወይም ሰው ከአጠገብህ ሲርቅ ወይም ሲጠፋ ደስታህም አብሮ ይጠፋል ። ደስታና ሰላም በአንተ ውስጥ ናቸው ። በራስህ በአፈጣጠርህ ደስ ይበልህ ፣ ውለህ በመግባትህ ደስ ይበልህ ። በአለህ ትንሽ ነገር ደስ ይበልህ ።
:
✅✅ ለፍቅር ለመውደድ እንጅ ለጥላቻ ለዛቻ ለምቀኝነት ጊዜ አይኑርህ ። በመውደድ የተጠመደ ሰው ለመጥላት ጊዜ የለውም ። እድሜህን በተመለከተ ፣ የፈጣሪ ፈቃድ ከሆነ ካለፈው ከተቃጠለው ጊዜህ ይልቅ ወደፊት የምትኖረው ብዙ ነው ። ዋናው ደግሞ የኖርክበት የእድሜ ብዛት ሳይሆን በኖርክበት ዘመን ያሳዪኸው መልካምነትና የሰራኸው ደግነት ነው ።
:
✅✅ የኖሩበት እድሜ ትንሹም ቢሆን በቂ ነው ይባላል ። የማቱሳላ እድሜው እንጅ የሰራው ስራ አይታወቅም ፣ "ኖሮ ሞተ" ብቻ ከመባል ፈጣሪ አምላክ ይጠብቅህ ። መኖርህ ሰዎችን ካልጠቀመ መሞትህ ላይጎዳቸው ይችላል ። መኖር መጥቀም መጠቃቀም ነው ።
:
✅✅ የምናማርረው የተሰጠንንና የሆነልንን ’ረስተን ፣ ያልጎደለን ነገር ላይ "ጎደለን" ብለን በጥያቄ ስለምንሞላ ነው ፣ ባለው ነገር አመስጋኝ የሆነ ይጨመርለታል ። በማማረር መባረክ የለም ። ሰላምና ጤና ፣ ከመልካም አስተሳሰብና በጎ ህሊና ጋር ምንጊዜም ከዘመንህ አይለዪ ።

#እናመሰግናለን

ለወዳጅወ ሼር ያድርጉ

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Riyadh?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address


Riyadh