Maki Makida
Maki beauty studio Dallas
08/20/2026
እግዚአብሔር ይመስገን። መቼ ትመጫለሽ ? የመድረክ ስራዬ በዳላስ ቴክሳስ ኦገስት ፈርስት ኮር ቲያትር ውስጥ ካቀረብኩ በህዋላ በብዙ ሰው ጥያቄ ሊደገም ነው። መቼ ትመጫለሽ ከእውነት የተቀዱ ስምንት የስነጽሁፍ ስራዎቼን በልዩ አቀራረብ የማቀርብበት መድረክ የፊቲችን November 14 በዘኮር ቴያትር ቅዳሜ ምሽት በልዩ ሁኔታ ይቀርባል። ትኬቱን የምታገኙበት ሊንክን ይኸው Maki Returns to Dallas – By Popular Demand https://www.eventbrite.com/e/maki-returns-to-dallas-by-popular-demand-tickets-1998384794716?utm-campaign=social&utm-content=attendeeshare&utm-medium=discovery&utm-term=listing&utm-source=wsa&aff=ebdsshwebmobile
እዚያው እንገናኝ
በቀጣይ
ሂውስተን ለማቅረብ ዝግጅቴን እየጨረስኩ ነው። እግዚአብሔር ይመስገን 🙏

መዝሙር 118፥24
“እግዚአብሔር ያደረገው ቀን ይህ ነው፤ በእርሱ ደስ ይበለን፣ ሐሴትም እናድርግ።”
ምስጋና
ኦገስት 1 ቀን በዳላስ፣ ቴክሳስ፣ The Core Theatre ውስጥ ያቀረብኩት “መቼ ትመጫለሽ?” የመድረክ ትዕይንት በተሳካ ሁኔታ ስለተጠናቀቀ፣ ከሁሉ በፊት ክብርና ምስጋናዬን ለእግዚአብሔር አቀርባለሁ።
ከዚያ በመቀጠል፣ ለዚህ ስኬት አስተዋጽኦ ያደረጋችሁ ሁላችሁም ከልብ አመሰግናለሁ።
የመድረክ አጋፋሪዬ የነበርከው ወንድሜ ገጣሚ አበባው መላኩ፣ ከልብ አመሰግንሃለሁ።
DJ Natay፣ Dynamic Studio – Mike (ካሜራ)፣ Dalol Production (ቪዲዮ)፣ ድምፃዊ ግርማ ተፈራ፣ ላይት ለሠራህልኝ ያሬድ፣ ሁላችሁንም ለትጋታችሁ እና ለሙያዊ አገልግሎታችሁ ከልብ አመሰግናለሁ።
ከተለያዩ ስቴቶች ተጉዛችሁ ከጎኔ ለነበራችሁ ሁሉ ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። በተለይ ከፖርትላንድ መጥተህ ሳምንቱን ሙሉ ከጎኔ ለቆምክ ጎቤ ስምረት እና ዶል ኡመር በጣም አመሰግናለሁ።
የምሽቱ ትልቁ ስጦታ ግን እናንተ ተመልካቾቼ ናችሁ። አዳራሹ ሙሉ በሙሉ ተሞልቶ፣ አንዳንዶቻችሁ መቀመጫ በማጣታችሁ ቆማችሁ ትዕይንቱን ስትከታተሉ ያሳያችሁኝን ፍቅር ፈጽሞ አልረሳውም።
በአዳራሹ መሞላት ምክንያት መግባት ሳትችሉ ለተመለሳችሁ ወዳጆቼ ከልብ ይቅርታ። የሰጣችሁኝ ፍቅርና የቀረበው ጥያቄ በቅርቡ ይህንን ትዕይንት በዳላስ እንደገና እንዳቀርበው አበረታቶኛል፤ በቅርቡ እንገናኛለን።
ለዚህ ዝግጅት ቀንና ሌሊት ያልተለየች ዋርዳ ሁሴን፣ ያደረግሽውን ድካም በቃላት መግለጽ አይቻለኝም። ኑሪልኝ!
ጥበበ ሰለሞ�
መቼ ትመጫለሽ ?
ዛሬ🏃🏽♀️🏃🏽♀️🏃🏽♀️🏃🏽♀️
ለሁሉ ዘመን አለው፤ ከሰማይም በታች ለነገር ሁሉ ጊዜ አለው።” (መክብብ 3፥1)
07/27/2026
🎂 ዛሬ ልደቴ ነው! 🎉
ለሕይወት ስጦታ፣ ለጤና፣ ለፍቅር፣ ለጥበቃ እና እስከዛሬ ለመራኝ ለቸሩ እግዚአብሔር ምስጋና ይሁን። 🙏🏽
“ይህች እግዚአብሔር ያደረጋት ቀን ናት፤ ሐሤትን እናድርግባት፥ ደስም ይበለን።”
— መዝሙር 118፥24
አዲሱ የሕይወቴ ዓመት በእግዚአብሔር ጸጋ፣ በረከት፣ ሰላም፣ ጤና እና መልካም ፍሬ የተሞላ ይሁንልኝ። ያለፈውን ሁሉ በምስጋና፣ የሚመጣውንም በእምነት እቀበላለሁ። 🤍✨
#ልደቴ #ምስጋና #እግዚአብሔርይመስገን
07/17/2026
ኦገስት ፈርስት – እንገናኝ! | August 1st ኦ✨
ውድ ወዳጆቼ፣ ከረጅም ጊዜ በኋላ እንደገና ወደምወደው መድረክ ስመለስ በታላቅ ደስታ እጠብቃችኋለሁ። ❤️
ይህ ሾው መዝናኛ ብቻ አይደለም፤
የሕይወት ተሞክሮ፣ የሳቅና የእንባ ታሪክ፣ የትግል፣ የተስፋ እና እንደገና የመነሳት መልዕክት ነው። ✨
በዚህ ልዩ ምሽት ታሪክ፣ ሙዚቃ፣ ስሜት እና የማይረሳ የጋራ ቆይታ ይጠብቃችኋል።
ቤተሰቦቻችሁን፣ ወዳጆቻችሁን እና የምትወዷቸውን ሰዎች ይዛችሁ ኑ፤ አብረን የማይረሳ ምሽት እንፍጠር። ❤️
🎉 መግቢያ በነፃ ነው!
ምንም የመግቢያ ክፍያ አይኖርም።
ሁላችሁም በደስታ እንድትገኙ በፍቅር እጋብዛችኋለሁ። ❤️
📅 ቀን: ቅዳሜ፣ ኦገስት 1, 2026
🕕 ሰዓት: 6:00 PM
📍 ቦታ: The Core Theatre
518 W Arapaho Rd, Unit 115
Richardson, TX 75080
ቦታዎን አሁኑኑ ያስይዙ፤ ይህን መልዕክትም ለወዳጆችዎ በማጋራት ለሌሎችም ያድርሱ።
እጠብቃችኋለሁ… እዛው እንገናኝ! ❤️
USA
ሰላም ዳላስች የፊታችን ቅዳሜ የተወዳጅዋ ገጣሚ ሜሮን ጌትነት “ሌላ እውነት የለኝም “የተሰኘው የግጥም መፅሀፍዋ የፊታችን ቅዳሜ March 21 ከቀኑ 4-pm ጀምሮ በልዩ ዝግጅት ደምቆ ይጠብቆታል በእውነት እንዳትቀሩ
bookclub
03/16/2026
ሰላም ዳላሶች ሁላችሁም በክብር ተጋብዛችኋል። የተወዳጅዋ ገጣሚ ሜሮን ጌትነት “ሌላ እውነት የለኝም “የተሰኘው የግጥም መፅሀፍዋ የፊታችን ቅዳሜ እራስዋ ገጣሚዋ በተገኘችበት መድረክ በልዩ ዝግጅት ደምቆ ይጠብቆታል በእውነት እንዳትቀሩ
bookclub
02/11/2026
ተራ በተራ መሄድን ደጋጎቹ ሰዎች እያስለመዱን ነው። እኔማ ተኝቼ በተነሳው ቁጥር ስልኬን ለማየት ሁሉ መሳቀቅ ጀምሬያለሁ። ብዙ መርዶዎች በስልኬ ስለሚደርሱኝ። አማን አንተ ባለ ግሩም ትህትና ደግ ሰው አክባሪ ከEBS ቴሌቪዥን ጋር በነበረኝ የስራ ኮንትራቶች በተለይም “ያልተኖረ ልጅነት “ለተሰኘው ዶክመንተሪዬ ለነበረህ እገዛ አድናቆትና አክብሮት አመሰግናለሁ እንክዋን አላልኩህም ምክንያቱም እኔ የማውቀው አብረን ድጋሚ እንደምንሰራ ፣ድጋሚ እንደምንገናኝ፣ቢሮህ መጥቼ ቁጭ ብዬ የማወራህ ስለመሰለኝ ነው ደህና ሁን አንተ የደግነት ልክ። እግዚአብሔር አፅናኝ መንፈሱን ለባለቤቱ ማክዳ እና ለመላው ቤተሰቡ ለ EBS ቴሌቪዥን ባልደረቦች ይላክላችሁ 🙏
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Dallas, TX